✅የኢትዮጵያ ነገሥታት የሥልጣን ተዋረድ !!
1️⃣. ሊቀመኳስ:- ከንጉሡ የማይለዩና ተሰሚነት ያላቸው ባለሥልጣኖች ናቸው፡፡
2️⃣. በጅሮንድ፦ ለግምጃ ቤት ኃላፊና ለእጅ ባለሙያዎች አለቃ የሚሰጥ የቤተመንግስት ሹመት ነው።
3️⃣ ባላምባራስ፦ ማለት በጥንቱ ዘመን ኢትዮጵያኖች ይጠቀሙበት የነበረው የብላታ ዝቅ የሚል የማዕረግ አይነት ሲሆን ማዕረጉም ከሻምበል እኩል ነው፡፡
ባላምባራስ በወታደራዊ መስክ የምሽግ ፣የከተማ ግንብ፣ወይም የጦር ሰፈሩ አዛዥ ማዕረግ ነው ::
4️⃣. ብላታ፦ ብላታ የሚሰኘው በስሩ አምስት ባላምባራሶች ሲኖሩት ነው፡፡
✅️ ፭. ግራዝማች፦ ሌተናንት ኮሎኔል ወይም የግራ መኮንን (ዘማች) ሲሆን የንጉሠ ነገሥቱን፣ የራሱን፣ የደጃዝማቹን ወይም ፊታውራሪውን አንድ ጦር ሊመራ ይችላል፡፡
5️⃣. ቀኛዝማች፦ ኮሎኔል ሲሆን የአንድ ክፍለ ጦር አዛዥ ነው። ዘማች ማለት መኮንን ማለት ነው። ቀኛዝማች ማለት የቀኝ መኮንን ወይም የቀኝ ዘማች ነው።
6️⃣ ፊት አውራሪ:- ፊታውራሪ ሜጀር
ጀነራል ሲሆን ራሱን የቻለ የአንድ ጦር ወይም የንጉሠ ነገሥቱ ክፍለጦር አዛዥ ነው። ፊት-አውራሪ በስሩ አምስት ቀኝአዝማች እና ግራዝማች ይኖሩታል፡፡ (ሌላ ትርጉሙ የግንባር ቀደም ጦር አዛዥ ማለት ነው።)
7️⃣. ደጃዝማች፦ ደጃዝማች ሙሉ ጀነራል ወይም ሌተናል ጀነራል ሲሆን የግል ጦሩ ወይም የንጉሠ ነገሥቱ ወይም የንጉሡ ወይም የአንድ ራስ ክፍለ ጦር አዛዥ ነው። ደጃዝማች በስሩ አምስት ፊታውራሪዎች አሉት ::
8️⃣. ራስ:- ራስ ፊልድ ማርሻል ሲሆን የራሱ ግዛት ጦር ወይም የንጉሠ ነገሥቱ ወይም የንጉሡ አንድ ጦር ጠቅላይ አዛዥ ነው፡፡ ራስ በስሩ አምስት ደጃዝማቾች አሉት ::
9️⃣. ራስ ልዑል:- ራስ ልዑል የሚሰኘው በስሩ አምስት ራሶች ሲኖሩት ነው፡፡
1️⃣0️⃣. ልዑል:- ልዑል የሚሰኘው በስሩ አምስት ራስ ልዑሎች ሲኖሩት ነው ።
1️⃣1️⃣ ንጉሥ፦ ንጉሥ የሚሰኘው በስሩ ልዑልዎች ያሉት ሆኖ በራሱ ግዛት ጦር ጠቅላይ አዛዥ ነው፡፡
1️⃣2️⃣. ንጉሠ ነገሥት፡- ንጉሠ ነገሥት የሚሰኘው በስሩ ንጉሦች ሲኖሩት ነው፡፡ ንጉሠ ነገሥት የአገሪቱ ግዛት ጦር ጠቅላይ አዛዥ ነው፡፡
አንብብበው ከወደዱት 👍ይጫኑ
@Amazing_fact_433