✅ናድያ ናዲም ትባላለች ትውልዷ አፍጋኒስታን ሲሆን አባቷ እሷ ገና የአስራ አንድ ዓመት ልጅ ሳለች ነው በታሊባን ታጣቂዎች የተገደለባት። የናዲያ እና ቀሪ ቤተሰቤቿም አማራጭ የሌለው ምርጫ ስደት ሆነ።
ዴንማርክ ምትባል አውሮፓዊት ሀገር የአስራ አንድ ቋንቋዎች ተናጋሪዋን ናዲያን ናዲምን ብዙዎች ከትውልድ ቀዬአቸው ራቅ ሲሉ ሚሰማቸውን አይነት ስሜት እንዳያድርባት እቅፍ ድግፍ አድርጋ ተቀበለቻት። በነገራችን ላይ ሰው ሀገር ስንገኝ... ቢነዱትም አህያ ቢጭኑትም ፈረስ ከሀገሩ የወጣ ሀገሩ እስኪመለስ፣ መቸገር በሀገር እና መሰል እንጉርጉሮዎችን በትዝታ መልኩ የኋሊት እንደሚያብሰለስለን ልብ ይለዋል። የናዲያ እጣ ፈንታ ግን ከዚህ ተለየና ሴትነቷ ሳይበግራት በራሷ ብርቱ ጥረት ዓለም ላይ በጣም ተፈላጊ የሁለት ጥምር ሙያዎች ባለቤት ሆነች።
1. ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋነት:- ናዲያ ሀገረ ዴንማርክን ወክላ ዘጠና ዘጠኝ ጊዜ በመሰለፍ ሁለት መቶ ጎሎችን ከመረብ ያዋህደች ሲሆን ለማንችስተር ሲቲ እና ፒ.ኤስ.ጂን ለመሳሰሉ ዝነኛ የእግር ኳስ ክለቦች አስር ቁጥር ማልያን አጥልቃ በዋንጫ የታገዘ ስኬታማ ጊዜን አሳልፋለች።
ጤና እና ብርቱ ሴት:- የናዲያ የሜዳ ላይ አብዶዎቿ ከህሊና ሳይጠፉ በህክምናው ዘርፍም ተከስታ ዶክትሬት ዲግሪግሪዋን በመጫን ከጎል አነፍናፊነት ወደ ነብስ አድንነት በመሸጋገር ሌላኛዋን ናዲያን በሌላ ገጽታ አሳይታለች።
@Amazing_fact_433