ባለወርቃማው እጅ ደም ለጋሽ: ዛሬ አሸለበ
👇🏾
አንድ ሺህ አንድ መቶ ጊዜ ደም በመለገስ ከ2.4 ሚሊየን በላይ ህጻናቶችን ህይወት የታደገው አውስትራሊያዊ ጀግና
ጀምስ ሀሪሰን ይባላል
👇🏾
የ14 አመት ታዳጊ እያለ ደረቱ ላይ በተሰራለት ቀዶ ጥገና የተነሳ የደም ልገሳ ያስፈልገው ነበርና ሌሎች ሰዎች በሰጡት ደም ህይወቱ ተረፈች
የዚያን ቀን "እድሜዬ ሲፈቅድ ደም እለግሳለሁ" ሲል ቃል ገባ
እድሜው 18 ሲሆን ደም መለገስ ጀመረ
ከተወሰነ ልገሳ በኃላ ሀኪሞች የሀሪሰን ደም አንቲ-ዲ/Anti-D የተባለ በመርፌ የሚሰጥ መድሃኒት ለመስራት እንደሚያስችል አረጋገጡ
..........
አንቲ-ዲ (በቀላሉ ለማስረዳት) እናቶች የራሳቸው ሰውነት በሚያመነጨው በሽታ ተከላካይ ንጥረ ነገር የተነሳ በሚፈጠር ሂደት በቀጣይ በሚወልዱት ልጅ ላይ የሞት አደጋ እንዳይከሰት የሚረዳ እና ርሄሰስ ከሚባል ህመም የሚከላከል መድሀኒት ነው
በ2018 ዓ.ም የመጨረሻውን የደም ልገሳ ያደረገው የ81 አመቱ አዛውንት ጀምስ ሀሪሰን ለ60 ተከታታይ አመታቶች ከአንድ ሺህ አንድ መቶ ጊዜ በላይ ደም ለግሶ 3 ሚሊየን የአንቲ-ዲ በመርፌ የሚሰጡ መድሀኒቶች እንዲመረቱ አስችሏል
በዚህም ከ2 ሚሊየን በላይ እናቶች መድሀኒቱን ተጠቅመው ከ2.4 ሚሊየን በላይ ልጆችን ከሞት አትርፈዋል
"በእነዚህ አመታቶች ውስጥ 2.4 ሚሊየን ህጻናትን ህይወት መታደግ ተችሏል -የእርሱ ደም የተለየ ነው እጁንም የወርቅ እጅ ብለነዋል" ሲሉ የአውስራሊያ የቀይ መስቀል የደም ባንክ ባለሙያ ይናገራሉ
ከ81 አመት በላይ እድሜ የሆነ ሰው ደም እንዳይለግስ በሚከለክለው የአውስትራሊያ ህግ መሰረት ሀሪሰን የመጨረሻ ደም ልገሳውን ያደረገ ሲሆን የአውስትራልያ ከፍተኛ የጀብዱ ሜዳልያም ተሸላሚ ሆኗል
👇🏾
ዛሬ አረፈ : የሰላም እረፍት ይሁንልህ !!!
🙌🏼❤️