የበቀደሟ ልጅ ደወለችለት።
ሰፈሩ መጥታለች። ደነገጠ።
ሊዪቅፋት ሲሞክር ሸሸችው።
"ይቅርታ በለኝ" አለችው
"ይቅርታ "
"ድገመው"
"ይቅርታ"
"ድገመው "
"ይቅርታ "
ፀጥ አለች። ከትንሽ ፋታ በኋላ ደገመው
"ይቅርታ" አላት
"በቃ በቃ ስትደጋግመው እየቀለድክ ነው ሚመስለኝ"
"እሺ " ብሎ ጸጥ አለ።
"ምን እያሰብክ ነው"
ግራ ገባው። አሰበ
"አላጠፋሁም እኮ ላንቺ ስል ነው ይቅርታ ያልኩትም ብላት" ትሄዳለች
"ይቅርታ ልልሽ ነበር ብላትም ደጋገምከው ከልብህ አይደለም መሰለኝ ብላ ትሄዳለች"
"ቆይ ምን አርጌሽ ነው ብላትም ጭራሽ ያደረከውንም አታቅም ብላ " ትሄዳለች
"ፀጥ ብላትም ንቀት ነው ብላ ትሄዳለች"
ዝም አለ።
"እኔ ቆሜ እየተናደድኩ ጭራሽ ታስባለህ ንቀት መሆኑ ነው"
ሄደች.. .. ..
በቆመበት ቀረ።
መኪኖች እንደአደባባይ ይዞሩት ጀመር።
አንድ እብድ በጥቅስና በመፈክር መሐል ያለ ወረቀት ለጥፎ አየው።
ወረቀቱ
"ባንተ በኩል ሲያለፍ ያገኘኸውን ሰው
" እኔ ጋ ነው የመጣኸው" ብለህ ለማቆየት አትሞክር።"
~ ~ ~ ~ ~ ~
ኤልያስ ሽታኹን