🔥 "እናሲዝ"" አለቺኝ የማርያም ጣቷን ዘርግታ "እናሲዝ" አልኳት አስያዝን ካሸነፈች አዝያት ልዞር ተስማማን
🌟 የሆነ ቀን ቀጥሬያት ተገናኝተን እያወራን "እዩዬ" አለቺኝ የያዘችውን ትንሽ ሻይ ያለበትን ብርጭቆ በሁለት እጇ እያሽከረከረች፥መጨነቋ ፊቷ ላይ ያስታውቃል።
የምትለውን ነገር ሳትለው አስጨነቀኝ "ወዬ እናትዬ" አልኳት
"አንዳንዴ ጓደኞች ሆነን በቀረን ብዬ የምመኝበት ጊዜ እየበዛ ነው" አለቺኝ ሰውነቴ ቅዝቅዝ አለ "ምነው እናቴ ያጎደልኩት ነገር አለ" አልኳት ይሄ ነው የምትለኝ ነገር ቢኖር እና ማስተካከል ብችል ብዬ
💥 "አያይ በፍፁም እንደሱ አይደለም... በቃ ጓደኛሞች እያለን የነበረንን ነፃነት እወደዋለሁ... ቅርበታችን... ምንም አለመደባበቃችንን... ሳቃችን... ቀልዶቻችን መተፋፈር አልነበረውም አሁን ግን ተመልከተን... ድሮ አፈር መስለን እንዳልተገናኘን አሁን ልብሳችንን ፀጉራችንን ስንጠበብበት ያናድድኛል። እንደድሮ ነፃ አይደለንም አሁን ቃላት መርጠን ነው የምናወራው ተቆጥበን ነው የምንስቀው። ..."
"ስለዚህ...?!" አልኳት ድምፄ ከጠበኩት በላይ ሻክሮ ምክንያቱም ከተናገረችው አንዱም ስህተት የለውም
🌟 "እዩዬ እንዳሰብከው አይደለም የእውነት አሁን ያለንን ነገር እወደዋለሁ ግን ደሞ ውልብ ሲልብኝ ጓደኝነታችን ይናፍቀኛል" አለች እጆቼን ይዛ
አየኋት... አይኖቿን አየኋቸው... እንዳልከፋበት ፈርታለች "እዩ አላስደበርኩህማ በእማማ ሞት" አለቺኝ "ብትሞክሪ ራሱ ልታስከፊኝ አትቺይም" አልኳት "ለምን ያን ያህልማ ሰነፍ አይደለሁም" አለች እየፈገገች "ተፈጥሮሽ አይደለም ማንንም በተለይ እኔን ማስከፋት አትቺይም አልኳት"
"እናሲዝ"" አለቺኝ የማርያም ጣቷን ዘርግታ "እናሲዝ" አልኳት አስያዝን ካሸነፈች አዝያት ልዞር ተስማማን
ከዛ ግን ተመኘሁ ሁሉም እንደኛ ጉድለቶቹን ፊትለፊት መነጋገር ቢችል ብዬ ምናልባት ብዙ ፀቦች ፍቺዎች ይቀንሳሉ።
Nani እንደፃፈችው✍