የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር እና አዲስ አመራሮች በዩኒቨርሲቲው ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ ተወያዩ
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር አመራሮች ቀደም ሲል ያሉ አሠራሮች፣ ተሞክሮዎች፣ ተግዳሮቶች፣ አሁናዊ ነባራዊ ሁኔታና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ወሳኝ መረጃዎችን አስመልክቶ ኅዳር 27/2017 ዓ/ም አዲስ ከተመደቡ አመራሮች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር እና የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ነባር የዩኒቨርሲቲውን አመራሮች ከዚህ ቀደም ለነበራቸው አገልግሎት ምስጋና በማቅረብ ከኃላፊነት ያነሱ ሲሆን አዳዲስ የዩኒቨርሲቲው አመራሮችን በተጠባባቂነትና በውክልና መድበዋል፡፡
ሚኒስቴር መ/ቤቱና ቦርዱ በጻፉት ደብዳቤ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዳምጠው ዳርዛ (ዶ/ር)፣ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዓለማየሁ ጩፋሞ (ዶ/ር)፣ የምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝደንት በኃይሉ መርደኪዮስ (ተ/ፕ) እና የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝደንት ወ/ሮ ታሪኳ ወ/መድኅን ከአመራርነት መነሳታቸውን ያሳወቀ ሲሆን በምትካቸውም ኢ/ር አብደላ ከማል (ዶ/ር) በተጠባባቂ ፕሬዝደንትነት እንዲሁም ኢ/ር ቦጋለ ገ/ማርያም (ዶ/ር) የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት፣ ተክሉ ወጋየሁ (ዶ/ር) የምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝደንት እንዲሁም ፕ/ር ጳውሎስ ታደሰ የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝደንት ሆነው ከታኅሣሥ 01/2017 ጀምሮ በውክልና እንዲሠሩ ተመድበዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት