በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤ ደንጎሮ ወረዳ በአማራዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መሰንዘሩ ተሰምቷል፡፡
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤ ደንጎሮ ወረዳ በተደጋጋሚ ካለፈዉ አመት ግንቦት ወር ጀምሮ በተለዬ መልኩ መንግስታዊ ጪፍጨፋ ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል። አሁንም ያንኑ ለማስቀጠል በማለም ሸኔወቹ ጪምር በማሰልጠንና ህጋዊ ካባ በማልበስ አማራን እንድጨፈጭፉ ሲያደርጉ ቆይተዋል።በዚህም በርካቶች መሞታቸዉ ይታወቃል። በአዲሱ አካሄዳቸዉ መሰረት ደግሞ በርካታ ወጥመዶችን በማጥመድ ያንኑ ጪፍጨፋና ዘረፋቸዉን ለማካሄድ እቅዳቸዉን ጨርሰዋል ነው የተባለው።
በበረሃዉ አካባቢ ከኦሮሞ አበል የወሰዱ አማሮችን ላለፉት 3 አመታት አበል እየተቀበሉ ሲያሳርሱ ቢቆዩም አሁን ግን የተባባልነዉን አልተቀበልንም በማለት የሃሰትና ክህደት ክስ አዘጋጅተዉ አማራዉን ለማሳደድ ዝግጅት ላይ መሆናቸዉ የተሰማ ሲሆን፣ ፊጣሊ (ጽንፈኛ) አማራ ተደራጀ በሚል ታፔላ በርካታ ንፁሃንን ለመጨፍጨፍ በመሯሯጥ ላይ ናቸዉም ተብሏል። በጎርቴ ቀበሌ ወረቦ በሚባል አካባቢ በመሄድ የተኩስ እሩምታ በመክፈት ንፁሃንን ለመጨፍጨፍ ያደረጉት ሙከራ በህብረተሰቡ መራር ትግልና የሁለት ሰላማዊ ሰወች የመቁሰል አደጋ ሲደርስ በመራር መከላከል አምልጠዋል ። ይህ ሲከሽፍባቸዉ ምንም ነገር የሌለባቸዉን ንፁሃንን ወደ ወረዳዉ ማጎሪያ ሁለት ግለሰቦችን ወስደዉ አግተዋል ተብሏል። ይህ መንግስታዊ ሽብር ስርአቱ ካልወደቀ በስተቀር ንፁሃን መከራና ስቃያቸዉ ቀጣይ መሆኑን ጥሩ ማሳያ ይሆናልም ነው የተባለው።
በኪረሙ እና አሙሩ አካባቢም መሳሪያ በመቀማት ንፁሃንን ለመጨፍጨፍ በአራርሳ መርዳሳ በአማርኛ ማዘናጊያ በኦሮምኛ እንጨፈጭፋችኋለን ፉከራ ተካሂዶባቸዉ በጭንቀት ላይ ናቸዉ ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል።