አፄ ምኒልክ ክፍለ ጦር በአገዛዙ ኃይሎች ላይ ከፍተኛ ወታደራዊ ኪሳራ ማድረሱ ተገለጸ!!
መስከረም 23/2019 ዓ.ም
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ አፄ አምደጽዮን ኮር አፄ ምኒልክ ክፍለ ጦር፣ በመንዝ ላሎ ወረዳ በአገዛዙ ኃይሎች ላይ ከፍተኛ ወታደራዊ ኪሳራ ማድረሱን የኮሩ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል አስታወቀ።
በቀጠናው ለተከታታይ አራት ቀናት በተደረገው አውደ ውጊያ ከባድ ሽንፈት ያስተናገደው የአገዛዙ ኃይል፤ ተጨማሪ የሜካናይዝድ ኃይል ድጋፍ ከደብረ ብርሃን ከተማ በማስመጣት ጭምር ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራን እዳስተናገደ ኮሩ አረጋግጧል።
የአፄ ምኒልክ ክፍለ ጦር በመንዝ ላሎ ወረዳ ዙሪያ ከቀን 19/01/2019 ዓ.ም ጀምሮ ባደረጉት ታላቅ ተጋድሎ፡ በመካናይዝድ ታግዞ የነበረው የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ኃይል ጋር ጠንካራ የተሳካለት ኦፕሬሽን በመፈፀም በርካታ የአገዛዙ መስመራዊ ወታደሮች እስከወዲያኛው መሰናበታቸው ተገልጿል።
ከፍተኛ የሰው እና ቁሳዊ ኪሳራ ያስተናገደው የአገዛዙ ሠራዊት፡ በአውደ ውጊያው አንድ የኦራል ተሽከርካሪ በወገን ዲሽቃ ተመቶ ከጥቅም ውጭ እንደሆነ ሲታወቅ፣ ዘጠኝ(9) አባላቱ ሞተው አስራ ስድስቱ(16) ከባድ ቁስለኛ መሆናቸው ተረጋግጧል።
በመጨረሻም አገዛዙ በዚህ አውደ ውጊያ የወደቁትን አባላት አስክሬንና ቁስለኞቹን ይዞ ወደ ኋላ በማፈግፈግ፣ ከባድ ቁስለኞቹን ወደ ሞላሌ ሆስፒታል ወስዶ እያሳከመ መሆኑን ኮሩ በመረጃው ማረጋገጡን አመልክቷል።
" ክብር ለትግሉ ሠማዕታት!
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ