የኤሌክትሪክ አደጋን መቀነስ የሚችሉ የማከፋፈያ ምርቶችን ወደ ገበያ ለማቅረብ ዝግጅት እየተደረገ ነዉ ተባለ።
ይህን ያለዉ የቻይናዉ ኤፍ ኤንድ ቲ የኤሌክትሪክ እቃዎች አምራች ድርጅት ነዉ
ከአራት ወራት በፊት በኢትዩጵያ ስራ የጀመረዉ ኤፍ ኤንድ ቲ የተሰኘዉ የቻይና ካንፓኒ ከኤሌክትሪክ የጥራት ጉድለት ጋር በተያያዙ የሚፈጠሩ አደጋዎችን ችግር ለመፍታት በማለም ስራ ጀምሯል።
ድርጅቱ አዲስ ባስተዋወቀዉ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ምርት ላይ በሰጠዉ መግለጫ በሁለት አይነት የምርት አቀራረብ ለገበያ እንደሚቀርብ ገልፆል።
በተለያየ ይዘት ዩኤስቢ እንዲሁም ታይኘ ሲ ገመድ ቻርጀሮችን መቀበል የሚያስችል እንደሆነ የድርጅቱ ተወካይ ተናግረዋል።
ከአንድ ወራት በኋላ ገበያዉን ይቀላቀላል የተባለዉ ምርቱ ገበያዉ ላይ እየታየ ያለዉ እጥረት እና የጥራት ጉድለት ይሸፍናል ተብሎ የታመነበት ነዉ ተብሏል።
አዲሱ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ምርት ሁለት ሺህ አምስት መቶ ዋት የሀይል መጠን ያለዉ ነዉ።
ኤፍ ኤንድ ቲ የኤሌክትሪክ ገመዶች እና ኬብሎች አምራች ድርጅት አዲሱ ምርቱን በወር ሀምሳ ሺህ ያህል የማምረት እቅድ እንዳለዉ ገልፆል።
የሚያመርተውን ምርት በተመለከተ ከተሰጠዉ ተጨማሪ ማብራሪያ ደረጃቸውን የጠበቁ፣ ተፈላጊውን ጥራት የሚኖራቸዉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ ኬብል ምርቶችንና የኬብል ምርት ውጤቶችን ማምረት የጀመረ መሆኑ ተነስቷል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news