ጂንካ ዩኒቨርሲቲ አፈር አልባ የከብቶች መኖ አመረራት ዘዴን አስተዋወቀ
***
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በአስር ቀናት ውስጥ ምርት መስጠት የሚችል አፈር አልባ የእንስሳት መኖ አመራረት ዘዴን አስተዋወቀ።
የዩኒቨርስቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ዓለሙ አይላቴ እንደገለጹት ሀይድሮፖኒክ ፎደር ወይም አፈር አልባ የተሰኘው የመኖ አዘገጃጀት የወተት ምርታማነትን በእጥፍ የሚያሻሽል ነው።
አፈር አልባ የመኖ አመራረት ዘዴ በኢትዮጵያ ያልተለመደ እና በጥቂት የዓለም ሀገራት የሚተገበር መሆኑን ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት ለመኖ ልማት የሚሆኑ የእርሻ መሬቶች ለሰብል ልማት እየዋሉ እንደሆነ የገለፁት ፕሬዚዳንቱ፣ ከመሬት ጥገኝነት የተላቀቀው የአፈር አልባ የመኖ አመራረት ዘዴ ይህንን ችግር በመቅረፍ በአነስተኛ ቦታ ማምረት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል ።
የአፈር አልባ መኖ አዘገጃጀት በተለይ ለከተማና ከተማ ቀመስ አካባቢዎች አመቺ መሆኑንም አብራርተዋል።
የዩኒቨርሲቲው የእንስሳት እርባታ ተመራማሪ ነገሰ ጋሹ በበኩላቸው በአፈር አልባ ዘዴ የተመረተ መኖ የፕሮቲን እና የቫይታሚን ይዘቱ ከሌሎቹ የተሻለ ነው።
ይህ የአመራረት ዘዴ በተለይ ውሃ አጠር በሆኑ አካባቢዎች ለማምረት ምቹ ቴክኖሎጂ መሆኑን ገልፀው፤ በመስኖ አንድ ኪሎ መኖ ለማምረት በአማካይ እስከ 90 ሊትር ውሃ እንደሚወስድ በአፈር አልባ ዘዴ 1 ኪሎ መኖ ለማምረት ግን እስከ 2 ሊትር ውሃ ብቻ ጥቅም ላይ እንደሚውል ተናግረዋል።
የአፈር አልባ መኖ አዘገጃጀት ከ7 እስከ 10 ቀናት ውስጥ ምርቱ ለመኖነት እንደሚውል አንስተው በመስኖ እስከ 70 ቀናት እንደሚፈጅ ገልጸዋል።
አፈር አልባ መኖ አመራረት ቴክኖሎጂ ዓመቱን ሙሉ አረንጓዴ መኖ ማልማት የሚያስችል ሲሆን የአየር ንብረት ለውጥንም መቋቋም የሚያስችል ውጤታማ የሆነ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ መሆኑንም አክለዋል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news