የመቀለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጥያቄ ፍትሀዊና መመለስ የሚገባው ተባለ
👉 መቐለ ዩኒቨርስቲ ጉዳዩን በማስመልከት መግለጫ አውጥቷል
በትናንትናው ዕለት በመቐለ ዩኒቨርስቲ ዋና ግቢ ማለትም አሪድ ካምፓስ የምግብ መጠን ተቀነሰብን በሚል ምክንያት ተቃውሞ ተነስቶ እንደነበር ዳጉ ጆርናል ከምንጮች ሰምቷል።
ይህንን ተከተሎ የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር የምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ሓለፊ የሆኑት አቶ ጠዓመ አርዓዶም በፌስቡክ ገፃቸው በኩል ባስተላለፉት መልእክት የተማሪዎች ጥያቄ ፍትሃዊና መልስ የሚሻ ነው ሲሉ የተደመጡ ሲሆን አክለውም ጉዳዩ ወደ አመፅ ከመሸጋገሩ በፊት መፍትሄ ሊበጅለት ይገባ እንደነበርም ገልፀዋል።
መቀለ ዩኒቨርስቲ በበኩሉ ለተማሪዎቹ ባስተላለፈው መልእክት በሃገር ደረጃ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሃገራዊ የምግብ ሜኑ በትምህርት ሚኒስቴር ፀድቆ ለትግበራ መላኩ የገለፀ ሲሆን ዩኒቨርሲቲያው ከተማሪዎች ህብረት ጋር በመነጋገር የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የምግብ ሜኑን አዘጋጅቶ ወደ ትግበራ ማስገባቱ አስታውቋል።
ዩኒቨርስቲው አክሎም በሜኑው ላይ የሚስተካከሉ ነገሮች ካሉ ከብሄራዊ ሜኑው በይዘት እና በጀት ደረጃ እስካልተለየ ድረስ ጥያቄዎች በተማሪዎች ህብረት በኩል ቀርበው ማስተካከል እንደሚቻል የገለፀ ሲሆን ከዚህ ውጭ ግን በሃገር ደረጃ ተግባራዊ የሆነውን የምግብ ሜኑ በመቃወም የዩኒቨርሲቲውን መሰረተልማት ማጥፋት፣ የካፊተርያ እና የጥበቃ ሰራተኞች ላይ ጉዳት ማድረስ ተማሪዎች እንዲሁም ማህበረሰቡን እና ሃገሪቱን የሚጎዳና ተግባር ስለሆነ ቅሬታችሁን በሰላማዊ መንገድ መግለጽ እንዳለባችሁ እናሳውቃለን ሲል ተደምጧል።
በትናንትናው እለት በመቀለ ዩኒቨርስቲ ካምፓሶች የተነሳው ተቃውሞ በኃላ ላይ የአመፅ መልክ መያዙን የነገሩን ምንጮቻችን አመፁን ለማርገብ የፀጥታ ሀይል መሰማራቱን ብሎም ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ መውሰዱን ዳጉ ጆርናል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#ዳጉ_ጆርናል
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news