ሐያት ሜዲካል ኮሌጅ ለ13ተኛ ጊዜ ያስተማራቸውን 48 የሕክምና ተማሪዎች አስመረቀ
ሐያት ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ 48 የሕክምና ተማሪዎቹን በትናንትናው ዕለት አስመርቋል፡፡
በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ላይም የጤና ሚንስቴር ተወካዮች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኃላፊዎች፣ የኮሌጁ መምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች፣ የተመራቂ ቤተሰቦች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
የኮሌጁ ዲን አቶ ኩፋ በዳሶ በሥነ-ስርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ "ተመራቂዎች ለዓመታት የሚሰጠውን ከባዱን የሕክምና ትምህርት በመከታተል ለውጤት በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ" ብለዋል።
"በአሁኑ ጊዜ ዓለማችን ላይ አዳዲስና ነባር በሽታዎች የሰውን ልጆቹ እየፈተኑ ይገኛሉ" ያሉት የኮሌጁ ዲን፤ "ለዚህም የተመራቂዎች ሚና አይተኬ መሆኑን በመረዳት፤ በሥራ ዓለም ለሚያጋጥሙ ፈተናዎች በኮሌጅ ቆይታችሁ በበቂ ሁኔታ የንድፈ ሀሳብም ሆነ የተግባር ዕውቀት እንደገበያችሁ ይታመናል።" ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም፤ ሐያት ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የጤና ባለሙያዎችን በብቃት እያሰለጠነ ለመቀጠልና ጥራት ያለው ትምህርት ለማስጠት ከወትሮው ጠንክሮ እየሠራ እንደሚገኝ የገለጹ ሲሆን፤ ኮሌጁንም ለማስፋፋት እየሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።
ተመራቂ ተማሪዎች ኮሌጁን የተቀላቀሉት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በተሰጣቸው የአቻ ግመታ መስፈርት መሰረት መሆኑ በሥነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።
እጩ ተመራቂዎቹ ጠቅላላ የሕክምና ትምህርትን ለስድስት ዓመታት ተከታትለውና መስፈርቱን አሟልተው፤ በኮሌጁ አካዳሚክ ኮሚሽን ተገምግሞ ከጸድደቀ በኋላ ለምርቃት መብቃታቸውም ተነግሯል፡፡
በተጨማሪም በሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ የተመረቁት እጩ ምሩቃን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የምግብ መድሀኒትና የጤና እንክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣንን መስፈርት በማሟላታቸው፤ በጤና ሚኒስቴርና አዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የመንግሥት ሆስፒታሎች የተወሰነላቸው የአንድ ዓመት የኢንተርንሽፕ ፕሮግራማቸውን መጨረሳቸው ተገልጿል።
ሐያት ሜዲካል ኮሌጅ ቋሚ መምህራንና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ሳይንስ ፋኩሊቲዎች እና በተለያየ መንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በኮንትራት በተቀጠሩ መምህራን የመማር ማስተማሩን ሂደት በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል።
በኮሌጁ ከሚገኙ የሕክምና ተማሪዎች መካከል የጅቡቲ፣ የዩጋንዳ ፣የደቡብ ሱዳን፣ የሶማሌላንድ፣ የፊሊስጤምና የኬንያ ዜግነት ያላቸው ተማሪዎች እንደሚገኙበትም ተመላክቷል።
ኮሌጁ ከዘንድሮ ተመራቂዎች ጋር 944 በሜዲካል ዶክትሬት ዲግሪ ለ13ኛ ጊዜ ያስመረቀ ሲሆን፤ እስከ 2010 መጨረሻ ድረስ 188 ነርሶች በዲግሪ ማስመረቁ ተገልጿል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news