ሦስት መምህራን "ምርጥ መምህራን" ሆነው ተመረጡ
* መምህራኑ የተዘጋጀላቸውን የሜዳልያ፣ የዋንጫና የሰርተፍኬት ሽልማት ከኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕረዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ በንቲ እጅ ተቀብለዋል
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የተማሪዎች ሽልማት ድርጅት የተሰኘ ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ጥር 7/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ትምሀርት ሚንስቴርን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት በተገኙበት የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ፣ መምህራንና የትምህርት ተቋማት የመጀመሪያውን የሽልማትና የዕውቅና መርሀግብር በደማቅ ስነ-ስርአት አከናውኗል።
ድርጅቱ ሦስት መምህራንን አወዳድሮ ለሽልማት እንዲያቀርብ ለኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ሙሉ ኃላፊነት ወስዶ ነበር።
በዚህ መሠረት ...
* መምህርት መስከረም ታዬ ከአዲስ አበባ በ2015 ዓ.ም አፈፃፀም የ2016 ዓ.ም ምርጥ መምህርት ተብላ ማህበሩ በጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ ባዘጋጀው የአለም መምህራን ቀን ክብረ-በአል ላይ የተሸለመች፤
* መምህር አብዮት በዛብህ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በ2016 ዓ.ም አፈፃፀም ማህበሩ በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ባዘጋጀው የአለም መምህራን ቀን ክብረ-በአል ላይ የ2017 ዓ.ም ምርጥ መምህር ተብሎ የተሸለመ፤
* መምህር ሰለሞን ንጉሴ ከኦሮምያ በ2017 ዓ.ም ምርጥ መምህር ምርጫ ላይ 2ኛ የወጣ ናቸው።
የመምህራኑ ምርጫ የተካሄደው ለሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች መምህራን ማህበራት ከኢመማ መስፈርት ተዘጋጅቶ ከተላከ በኋላና ከመጡት መካከል የኢመማ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በሚያደርገው ምርጫ ነው።
የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር የትምህርት ማህበረሰቡን ዕውቅናና ሽልማት የሚሰጡ ተቋማትን የሚያበረታታ ሲሆን ይህንን መርሀግብር ላዘጋጀው ድርጅትና ለዋና ስራአስኪያጁ ለአቶ ቢንያም ጫኔ ምስጋናውን አቅርቧል። ይህ መርሀግብር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news