የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕክምና ሳይንስ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በሕክምና ሳይንስ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 197 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡
ከተመራቂዎች መካከል 153 በሜዲካል ዶክትሬት፣ 21 በጥርስ ሕክምና እና 23 ተማሪዎች ደግሞ በአኔስቴዥያ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው፡፡
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ተገኝተዋል፡፡
ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ተመራቂዎች ሕሙማንን ማከም ብቻ ሳይሆን የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ በመረዳት በሕብረተሰቡ ጤና ላይ የበለጠ ምርምር ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
የተሻሉ ሐኪሞች ለአዳዲስ ሃሳቦች እንደሚተጉ አንስተው÷ተመራቂዎች ለታካሚዎች ሰብዓዊ ርህራሄ በመስጠት ሙያዊ ሥነ-ምግባር አክብረው እንዲሰሩም ጠይቀዋል።
ዶ/ር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው÷የጤና ባለሙያዎች ቀጣይነት ላለው የጤና ሥርዓት ወሳኝ እንደሆኑ መናገራቸውን የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመላክታል፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news