ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና (Entrance Exam) ለሚወስዱ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት (Tutorial) ለመስጠት ዛሬ የካቲት 22/2017ዓ.ም የማስጀመሪያ መርሃግብር አካሄደ።
****
በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚታየውን የትምህርት ጥራት ለማሻሻል የሁሉም ባለድርሻ አካላት አስተዋፅኦ የሚፈልግ በመሆኑ ጂንካ ዩኒቨርሲቲም የራሱን ሀላፊነት ለመወጣት በጂንካ ከተማ ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ይሰጣል ሲሉ የማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ዲን መ/ር አብረሃም ዮሀንስ ገልፀዋል።
ዘንድሮ ለሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ከትምህርት ቤቶቹ ጋር በመተባበር የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠቱ ትልቅ ማነቃቂያ እንደሚፈጥር በመግለፅ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንትም የተቻለውን ሁሉ አስተዋጽኦ ለማበርከት ቁርጠኛ መሆኑን ተጠቁሟል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news