የኢትዮጵያ ኮምፕርሄንሲቭ ዩኒቨርሲቲዎች ማህበር ተመሰረተ
21 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተካተቱበት የኢትዮጵያ ኮምፕርሄንሲቭ ዩኒቨርሲቲዎች ማህበር በይፋ ተመሰረተ።
የማህበሩ የምሥረታ ጉባኤ በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት በባሌ ሮቤ ተካሂዷል።
ትምህርት ሚኒስቴር ዩኒቨርሲቲዎች በሚያካሄዱት ተግባር ውጤታማ እንዲሆኑ በምርምር "አብላይድና ኮምፕሬሄንሲቭ" ብሎ ማደረጀቱ ይታወሳል።
የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ በበይነ መረብ ባስተላለፉት መልዕክት÷ ዩኒቨርሲቲዎች ተቀናጅተው መስራታቸው ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።
በዚህም ዩኒቨርሲቲዎቹ በአደረጃጀቱ የተሰጣቸውን ተልዕኮ የሚያረጋግጡ ተግባራት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመው÷ ለማህበሩ ውጤታማነት ሚኒስቴሩ እገዛ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
የማህበሩ ሰብሳቢ ሆነው የተመረጡት የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አነጋግረኝ ጋሻው (ዶ/ር) አዲሱ አደረጃጀት ዩኒቨርሲቲዎች በተሰጣቸው ተልዕኮ ውጤታማና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያግዛል ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲዎቹ ማህበር መመስረታቸው ከተናጥል ይልቅ ተግባራትን በማቀናጀት ተወዳዳሪና ውጤታማ ሥራ ለመስራት ያስችላልም ነው ያሉት።
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አህመድ ከሊል (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ማህበሩ የተቋቋመለት ተልዕኮ እንዲያሳካ ከሁሉም አመራርና ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።
በመስራች ጉባኤ ተሳታፊ የማህበሩ አባል ዩኒቨርሲቲ ተወካዮች በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news