#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሶስት
፡
፡
#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በማግስቱ የናፈቀው ቢሮ የገባው አራት ሰዓት አካባቢ ነበር….የማታው ስካር አንጎበሩ ሙሉ በሙሉ አለቀቀውም…አሁንም ጭንቅላቱን እየወቀረው ነው፡፡ለፀሀፊው መምጣቱን
ስላልነገራት አልገባችም…ከፍቶ ገባና ቁጭ አለ ..የሚሰራው ስራ ስላልነበረ የሚያደርገው ነገር ግራ ገባው..ስልክ አውጥቶ ደወለ፡፡
‹‹እንዴት ነሽ…ለሊሴ?››
‹‹ደህና ነኝ ሰለሞን…እንዴት ነው ስራ?››
‹‹አሪፍ ነው..አሁን ተመልሼለሁ…ቢሮ ነው ያለሁት››
‹‹ውይ ለምን ሳትነግረኝ..ቀድሜ ገብቼ አፀዳድቼ ጠብቅህ ነበረ እኮ››
‹‹አይ ችግር የለውም..ቢሮው አሁንም ንፅና የተስተካከለ ነው››
‹‹አዎ እሱማ በሶስት ቀን አንዴ ከፍቼ አናፍሰዋለው….እና ስራህን ጨረስክ ማለት ነው?››
‹‹አይ አልጨረስኩም…በመሀል የሶስት ቀን እረፍት ስላለኝ ነው የመጣሁት…ለመሆኑ ያንቺ ነገር እንዴት ሆነ?››
‹‹የቱ?››
‹‹የሁለቱ ፍቅረኞችሽ ነገር?››
ለሊሴ ሰለሞን ባቀረበላት ሀሳብ መሰረት ከሁለት ፍቅረኞቾ መካከል አንዱን ለባልነት ለመምረጥ ምታደርገውን ጥረት ወዲያው ነበር የጀመረችው ….መጀመሪያ ነጋዴውን ለአንድ ወር ላታገኘው እንደማትችል ነግራ ከመንግስት ሰራተኛው ጋር ነበር የቀጠለችው..ሲደውልላት ትሄዳለች..ዝም ሲላት ትደውልለታልች….ከስራ መልስ ሳታገኘው ወደቤት አትገባም…እሁድ ቢያንስ ግማሹን ሰዓት ከእሱ ጋር ነች፡፡ይበልጥ ትኩረቷን ሰብስባ ከእሱ ጋር ባሳለፈች መጠን በፊት ከምታውቀው በላይ እያወቀችው …በፊት ከምታዳምጠው በላይ እያዳመጠችው መጣች፡፡አሁን ያለበትን የኑሮ ደረጃ ብቻ ሳይሆን ..
የወደፊት እቅዶቹንና እነዛን እቅዶች ለማሳካት እያደረገ ያለውን ተጋድሎም እየተረዳችና እየተገነዘበች መጣች…..እሱ ላይ ያላት ቅሬታ ባገባው እኔን አኑሮ ቤተሰቦቼንም እንድረዳ የሚያበቃኝ ህይወት ሊሰጠኝ አይችልም የሚል ነበር…አሁን ስታስበው ግን ያንን ከእሱ ብቻ መጠበቅ እንደሌለባት ነው የገባት…እሱ ባለው ቁርጠኝነት ላይ እሷ ተጨምራበት ካገዘችውና ከጎኑ ሆና አብራው ከታገለች ጎዶሎው ሊሞላ የሚችል አይነት እንደሆነ ተረድታለች…ግን ውሳኔ ላይ ከመድረሷ በፊት ለእሱ የመደበችለት ወር ተገባደደ እና ለዛኛው የሰጠችውን ተመሳሳይ ምክንያት ሰጥታ ..ለአንድ ወር ያህል ልትደውልለትም ሆነ ልታገኘው እንደማትችል ነገራ ወደነጋዴው ሄደች፡፡
በእውነት ነገዴው ጋር ልክ እንደወትሮ ሁሉ ነገር ተሰርቶ ያለቀ ሆኖ ነው የጠበቃት…ቤቱ የተዘጋጀ..እቃዎቹ የተደራጁ ናቸው…አዎ እያንዳንዱን ሀብቱንና አኗኗሩን ተራ በተራ አሳያት፣ቀጥታ እንዳገባችው ሕይወቷን ወደመስራት ሳይሆን የተሰራ ህይወት ውስጥ ገብቶ ለመኖር መሞከር ብቻ እንደሚጠበቅባት ተረዳች ፣ግን ለምን ልቧ ወደኃላ እንደሚጎትታት ግልፅ ሊሆንላት አልቻለም‹‹…ታግዬ ያላሸነፉኩት በሌላ እጅ የተሰራ ህይወት ምን ትርጉም ይኖረዋል?››እራሷን ጠየቀች… መልሱ ቀላል አልነበረም….፡፡
ሁሉንም ሂደት አንድ በአንድ ዘርዝራ አስረዳችው፡፡ ሰለሞንም‹‹እና ምን ተሰማሽ?››ሲል ጠየቃት
‹‹አሁንም እንደተወዛገብኩ ነው…ግን በአእምሮዬ ውስጥ የሚመላለሱ ጥያቄዎች በፊት ከሚመላለሱት የተለዩ ናቸው…እንግዲህ እኔ በህይወቴ ጠንከር ያሉ ውሳኔዎችን የማስተላለፍ ከፍተኛ ድክመት እንደለብኝ ነው የተረዳሁት፡፡››
‹‹አይ እንደዛ አይመስለኝም …አንቺ ቀሪ ህይወትሽን አብሮሽ በደስታ የሚዘልቅና ከቤተሰቦችሽም ጋ ተሰስማምቶ የሚያኮራሽ ለፍፅምነት የተጠጋ ባል እየፈለግሽ ነው….በዚህ ምድር ላይ ደግሞ ለፍጽምና የተጠጋ ነገር መምረጥ ቀላል ነገር አይደለም፡፡አንድ ታሪክ ልንገርሽ..
‹‹ደስ ይለኛል››
ደቀ መዝሙሩ መምህሩን ‹‹ፍፁምና በህይወታችን እንዴት አድርገን ነው ፍፅማዊ የሆነ ነገር መጎናፀፍ የምንችለው? ሲል ጠየቀው ፡፡ መምህሩም አሰብ አደረገና ‹‹የዚህን መልስ
እንድነግርህ ከፈለክ በፊት ለፊት በር ወደ ግቢው የአትክልት ስፍራ ቀጥ ብለህ ግባ ።በመንገድህ ከምታገኛቸው አበቦች መካከል በጣም የሚያምረውንና ደስ ያሰኘህን ቀንጥስና በጎሮ በር ውጣ …አንዴ ያለፍከውን አበባ ከእንደገና ወደኃላ ተመልሰህ መቅጠፍ አትችልም አሉት።›› አለው ።እሱም ትዕዛዙን አክብሮ እንዳተባለው ወደ አትክልቱ ስፍራ ገባና እስከመጨረሻው ጥግ ከተጓዘ በኃላ ባዶ እጅን በጓሮ በር ወጣ።
መምህሩ ‹‹ለምንድነው አንድ ቀንበጥ አበባ እንኳን ይዘህ መውጣት ያልቻልከው?››ሲሉ ጠየቁት፡፡
‹‹ምርጥ የተባለውን አበባ ወዲያው እንደገባሁ ነበረ ያገኘሁት... ግን የተሻለ አገኛለሁ ብዬ በማሰብ ሳልቀነጥስ ወደፊት ቀጠልኩ .. መጨረሻው ላይም ደረስኩ.. ወደኃላ የመመለስ እድል ስለሌለኝ ባዶዬን ለመውጣት ተገደድኩ›› ሲል መለሰ።
መምህሩ መልሱን ሲሰሙ ፈገግ አሉና ‹‹አዎ! ትክክል ነህ ፤ህይወት እንደዛ ነው ።ፍፁምናን ለማግኘት ይበልጥ በዳከርን ቁጥር ብኩን እየሆንክ ትሄዳለህ።እውነተኛ ፍፁምናን መቼም የትም አታገኝም።››ሲሉ መለሱለት። ‹‹ገባሽ አይደል?››
‹‹አዎ ገብቶኛል››
‹‹እንግዲያው ፍፅም በምናብ አለም ካስቀመጥሽው ወንድ ጋር የሚስማማ ባል እንደማታገኚ አውቀሽ ለሚማጡት 10 ቀናት ሁለቱንም ሳታገኚ አስቢበት..ከዛ ማንኛቸው ናቸው የበለጠ የሚናፍቁሽ..የትኛው ቢያቅፍሽ ትፈልጊያለሽ ….?ማንኛቸው የልጆችሽ አባት ቢሆኑ ይሻላል..?በህልምሽ እየደጋገመ የሚመጣው የትኛው ነው?፡፡ለ10 ቀን አስቢበት፡፡››
‹‹እሺ እንደዛ አደርገላው..ግን አሁን አሁን እየገባኝ ያለው እኔ ከባሌ ምን እጠብቃለው ብቻ ሳይሆን ለባሌስ ምን ይዤለት ሄዳለው…?የሚለውን በጥልቀት ማሰብና መዘጋጀት እንዳለብኝ ነው፡፡ ››
‹‹ጎበዝ ነሽ…ይሄ ትልቅ መረዳት ነው..በይ ደህና እደሪ››
‹‹ውይ …ከመዝጋትህ በፊት…ድፍረት አይሁንብኝና ዛሬ ቤት ለምን አትመጣም››
‹‹ለምን?››
‹‹እማዬ የማሪያም ድግስ አለባት….ማህበርተኞቹ እስከ10 ሰዓት ነው የሚቆዩት 11 ሰዓት ብትመጣ በጣም ደስ ይለኝ ነበር…››
‹‹አረ ተይ››
‹‹ምን አለበት…ቤተሰቦቼ በጣም ነው ደስ የሚላቸው››
‹‹11 ሰዓት ነው ያልሽኝ?፡፡››
‹‹አዎ 11 ሰዓት››
ብቻውን ሆኖ ስለአስቴር እያሰበ ከሚሰቃይ ከሰው ጋር ተቀላቅሎ የባጥ የቆጡን እያወራ ሊረሳት ቢሞክር እንደሚሻለው አሰበእና ‹‹በቃ እሺ መጣለሁ››አላት፡፡
‹‹በቃ አቃቂ ፖሊስ ጣቢያው ጋር ስትደርስ ደውልልኝ..ወጥቼ እቀበልሀለው››
‹‹እሺ ደውላለው››
ስልኩን ዘጋው፡፡ እሺ ማለቱን ፍጽም አላመነም….ጠበል ለመቅመስ ከሜክሲኮ
አቃቂ….ለመሆኑ በህይወቱ ጠበል የተጠራውና ጥሪውን አክብሮ የሄደው መቼ ነው..?ፍጽም አያስታውስም….
እንዳለችው …..እንደደወለላት ደቂቃ ሳታባክን ነው ወጥታ የተቀበለችው….መኪናውን
እዛው አስፓልት ዳር ፓርክ አደረገና ተከትሏት ይዛው ሄደችው.. ግን ወደሚያስደነግጥ ቦታ ነው ይዛው የሄደችው…ይሄንን ግቢ ትናንትና በዚህን ሰዓት መኪና ውስጥ ሆኖ ከአሰሪዎቹ ጋር በመሆን ሲሰልለው ነበር …‹‹ምን አይነት መገጣጠም ነው?››ለለሊሴ ምንም አይነት የመደነቅና የመገረም ስሜት ሳያሳያት ተከተላት፡፡አሁን ነገሮችን ገጣጥሞ ሲያስብ በፀሎት እሱን እንዴት እንዳገኘችውና ስልኩን ከማን እንደወሰደች ተገለፀለት፡፡