#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አምስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ሰለሞንና የበፀሎት ቤተሰቦችን አብዛኛውን ጊዜያቸውን አካባቢውን ያለውን እያንዳንዱን መስህብ በመጎብኘት ነው የሚያሳልፉት….እያንዳንዱ ውይይትና ምክረ-ሀሳብም በመዝናናት ውስጥ ሆነው የሆነ ቦታ አረፍ ሲሉ ወይም ቡና ለመጠጣት የሆነ ካፌ ሲቀመጡ በውይይትና በጫወታ መልክ የሚሰጥ ስለሆነ እንደ ቢሾፍቱ አስጨናቂና ጭንቅላት የሚይዝ አይነት አልነበረም፡፡
በወንጪ ኢኮ ቱሪዝማ ማዕከል ውስጥ ከሚገኙት እና ለጉብኝት ዝግጁ ከሆኑት ዋና ዋና አይን ሳቢና ቀልብ አስደንጋጭ የቱሪስት መስህቦች ውስጥ ጥቂቶቹ
ጎሮ በሚባለው ስፍራ የተገነባው ጎሮ ካልቸራል ሴንተር የወንጪ ኢኮቱሪዘም ፓርክ አንዱ መገለጫና ውበት ነው፡፡ በህንፃው ላይ ባህላዊ ምግቦች የሚገኙበት ውብ የሆነ ሬስቶራንት..ባህላዊ የሆኑ የእጅ ስራ ውጤቶች የሚሸጥባቸው ሱቆች…የተለያዩ ዝግጅቶችን ለማዘጋጀት የሚያገለግል እስከ 3መቶ ሰዎች ማስተናገድ የሚችል ውብ የሆነ አምፊ ትያትር ከአካባቢው ከሚገኙ አገልግሎቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ እና አካባቢው ላይ ሆኖ ቁልቁል ወደታች ሀይቁንና ከማዶው ያለውን ተራራ ሲያዩት ልብን ስውር የሚያደርግ የተለየ አይነት አስደማሚ እይታ አለው፡፡
ከጎሮ 2.3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ነዲ ካልቸራል ሴንተር ደግሞ ሌላው ልብ ሰዋሪ ቦታ ነው፡፡ነዲ ከስሙም መረዳት እንደሚቻለው በአካባቢው የሚመረት የወንጪ ማር እና የማር ውጤቶች እንደብርዝና ጠጅን ጨምሮ መሸጫ እንዲሆን ታስቦ የተገነባ ህንጻ ነው…የህንፃው ጠቅላላ ዲዛይን አገልግሎቱን ታሳቢ ተደርጎ የተሰራ ስለሆነ ውብ ነው፡፡በማር እንጀራ ቅርፅ የተሰራ ሁለት ሶስት ጓደኛሞች ተቀምጠው ቁልቁል ሚታየውን ውብ እይታ ዘና እያሉ ወሬያቸውን የሚጠረቁበት ውብ ስፍራ አለ፡፡
ሙለታ ወንጪ ሬስቶራንት ሌላው በስፍራው የሚገኝ ውብ ቦታ ነው …በዚህ ስፍራ ሬስቶራንቶችና ሱቆች የፈረስ ማስዋቢያና ባህላዊ እቃዎች የሚሸጡበት ሱቆች ሲኖሩ ኩኪስ ብስኩት የመሳሰሉትም ቀላል ምግቦችን ማግኘት ይቻላል ፡፡
ነዲ ሰስፔንድድ የመስታወት ቴራስ ሌላው በአካባቢው ያለ ውብ ህንፃ ነው፡፡ይህ የመስታወት ወለል ግማሽ ክብ አይነት ቅርፅ ሲኖረው በሶስት ድርብርብ ተደርጎ የተሰራና እላዩ ላይ ወጥታው በመስታወቱ አሻግረው ወደታች ሲመለከቱ ከስር የሚታየው አስፈሪ ገደል መሳይ ግን በአረንጓዴ ሳርና ተክሎች የተሸፈና ውብ ስፍራ በማዶ የሚገኘው የጠራ ሀይቅ …በቃ አስፈሪ ግን ደግሞ አስደሳች እይታ ነው፡፡ይህ የመስታወት ቴራስ በአንድ ካሬ ሜትር ላይ 400 ኪ.ግራማ የመሸከም አቅም እንዳለው ቢታወቅም በርከት ያለ ሰው ከወጣበት ግን ከአሁን አሁን መስታወቱ ተፈርክሶ ሾልከን ወደገደሉ ብንንከባለልስ? የሚል የፍራቻ ስሜት ሰቅዞ የሚያሲዝ አይነት ነው፡፡ከዚህ አስደማሚ የመስታወት ቴራስ ጎን አምፊትያትር ያለ ሲሆን በተያያዥነትም…ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚሰጥ ካፍቴሪያ አለ፡፡ከዚህ ስፍራ ቀጥታ ወደሎጅ የሚወስድ የመኪና መንገድ ከላይ የመስታወት ቴራሱ ላይ ሆነው ከስር ማየት ይቻላል፡፡
ከዛ ደግሞ የተፈጥሮ ፍል ውሀ ያለበት በደን የተሸፈነ ሲሆን በአካባቢው ጉሬዛ ፤ጦጣ አእዋፍት ፤አምቦ ውሀ የተፈጥሮ ፏፏቴ ይገኛል …ጎን ለጎን ያሉ ሙቅና ቀዝቃዛ ኩሬ የኬብል ድልድይ ፤ወንዝ ..ብዙ ብዙ አስደማሚ ተፈጥሯዊ ነገር ይገኛል፡፡የነዲ መዝነኛ ስፍራን እና የተፈጥሮ ፍል ውሀን የሚያገናኝ በብረት የተሰራ እስካይ ብሪጅ አለ፡፡ብሪጁ 72 ሜትር ርዝመትና ኖሮት ሀምሳ ሜትር ከፍታ እንዲኖረው ተደርጎ የተሰራ አስፈሪ ግን ደግሞ የራሱ የሆነ ውበትና የተለየ ስሜት የሚያጭር ልዩ ድልድይ ነው፡፡
እነዚህን ሁሉ ባለፈው አንድ ሰምንት ውስጥ የጎበኞቸው ቦታዎች ናቸው፡፡ በስምንተኛው ቀን ከቀኑ 9ሰዓት አካባቢ ለበፀሎት ደወለላት
‹‹ሄሎ..እንዴት ነሽ?››
‹‹አለሁልህ…ገነት ገብቼለሁ››
‹‹ወደድሽው ማለት ነው››
‹‹እንዴ ትቀልዳለህ እንዴ …?አካባቢው እኮ እንኳን እንደእኔ አፍጥጠው የሚያዩ ሁለት አይኖች ላሉት ሰው ይቅርና አይነ-ስውር ቢመጣበት እንኳን ውበቱ በሽታ ሳይቀር ይታወቀዋል፡፡››
‹‹ዋው ድንቅ አገላለፅ ነው….በጣም ማርኮሻል ማለት ነው…እኔንም አንድ ቀን ወስደሽ እንደምታስጎበኚኝ ትስፋ አለኝ፡፡››
‹‹በደንብ እንጂ…ለዛውም በቅርብ ነዋ››
‹‹አሁን የት ነሽ…?ላለፉት አንድ ሰዓት ለሊሴ ጋር በሳይክል አካባቢውን ስናካልል ነበር.. አሁን ድክም ብለን ነዲ ካልቸራል ሴንተር የሚባለው ስፍራ ላይ ነን ፡፡
‹‹ምነው…ጠጅ እየጠጣችሁ ነው እንዴ?››ሲል ጠየቃት
‹‹አይ ትኩስ ወለላ ማር እየበላን››
‹‹በቃ ..ሰዓታችሁን አልውሰድባችሁ…..ዘና በሉ››
‹‹እሺ ቸው…ለሊሴ ሀይ እያለችህ ነው፡፡››
‹‹ሀይ በይልኝ‹‹ስልኩ ተዘጋ፡፡
‹‹አንቺ ሀለቃዬን ምን ልታደርጊው ነው?››ለሊሴ በመገረም ውስጥ ሆና ጠየቀቻት፡፡
‹‹ምን አደረኩብሽ…?››
‹‹እንዴ እያየሁ…ከተዋወቃችሁ ገና ሳምንት ነው..ግን ይሄውና በየቀኑ ይደውልልሻል፣ ገባሽለት እንዴ?››
‹‹አረ አንቺ ደግሞ…››በፀሎት እንደማፈር ብላ ተሸኮረመመች፡፡
‹‹ምነው..ቢሆን ደስ ይለኛል..ምርጥ ሸበላና የተማረ ሰው ነው..በዛ ላይ ትህትና አለው…እና አንቺን እህቴን ብድርለት በጣም ደስ ይለኛል››
‹‹በይ አንቺ ካዳመጡሽ …ብዙ ታወሪያለሽ››
ለደቂቃዎች ሁለቱም ዝም ተባባሉና በየግላቸው ሀሳብ መብሰልሰል ጀመሩ፣…በፀሎት ድንገት‹‹አካባቢው ግን አያስደንቅም?››ብላ አዲስ የመወያያ ርዕስ ከፈተች፡፡
‹‹ በጣም እንጂ…እያንዳንዱ ስፍራ የራሱ የሆነ እይታ አለው…አሁን ጎሮ ጋር ሆነሽ ቁልቁል ስታይ የተለየ አይነት እይታ..ከሊበን ሆነሽ ስታይው ደግሞ የተለየ አይነት እንደምታይው እዚህ ሆነሽ ስትመለከቾ ደግሞ ሌለ አይነት…በእውነት ይሄ በጣም አስገራሚ ነው፡፡ቦታ በቀየርሽ ቁጥር የምታይውም ነገር ይቀየራል…››
‹‹አዎ እንግዲህ …አምላክ ሲጠበብ ወሰን የለውም….››
‹‹እውነት ነው አምላክ ሲጠበብ ወሰን የለውም››የሚል ጣልቃ ገብ ዓ.ነገር ሁለቱንም ከተቀመጡበት በርግገው እንዲነሱ አደረጋቸው፡፡ሌላ ሰው ነበር ከጀርባቸው የተናገረው፡፡
‹‹አንተ….እንዴት?››
‹‹ያው እንደዚህ››አለና ሁለቱንም በየተራ ሰላም አላቸው፡፡ተያይዘው ተቀመጡ፡፡
‹‹እዚህ ሆነህ ነበር እንዴ የምትደውልልኝ…?››በፀሎት በገረሜታና ባለማመን ጠየቀችው፡፡
‹‹አዎ…››
‹‹እኔ ደግሞ ምን አይነት ሞኝ ነኝ ..የት ነሽ ስትለኝ ያለሁበትን በየዋህነት መዘርዘሬ››
‹‹ምነው ስለመጣው ከፋሽ እንዴ?››
‹‹አረ በፍፅም››
የሰለሞንንና የበፀሎትን የማያቆርጥ ጥያቄና መልስ በዝምታ እየታዘበች በውስጦ እነዚህ ሰዎች ምንድነው እንዲህ ያቀራረባቸው..?ሰውዬውስ እሷን ፍለጋነው እንዴ እዚህ የመጣው
?እያለች በውስጦ ተብሰለሰለች ፡፡ልክ ልቧን እንዳነበበ ለጥያቄዎቾ መልስ ይሰጣት ጀመር…‹‹ያው ባለፀጋዎቹ ደንበኞቼ እዚህ ካልመጣን ሲሉ ተከትያቸው መጠሁ..ያው አስገድደው ሲያስደስቱኝ ምን ላድርግ..እየመጣሁ ሳለሁ ደግሞ እናንተ እዚህ እንዳላችሁ ትዝ ሲለኝ..የበለጠ ዘና አልኩ››
‹‹እና ታዲያ ሰዎችህ የታሉ?››በፀሎት ከወላጆቾ ጋር ድንገት ፊት ለፊት የመፋጠጥ ስጋት አስጨንቋት ጠየቀች
‹‹አሁን ክፍላቸው አረፍ ብለዋል….ለሚቀጥሉት ሁለት ሶስት ሰዓት እረፍት ነኝ….›› በፀሎት‹‹እና ታዲያ ወደፍል ውሀ ለምን አንሄድም?››የሚል ሀሳብ አቀረበች፡፡