#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስድስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
የባልና ሚስቶቹ የምክር አገልግሎት እንደቀጠለ ነው…ዛሬ ወንጪ ከከተሙ አስራአራተኛው ቀን ላይ ሲሆኑ በዚህ የ14 ቀን ጉዞቸው ከፍተኛ ለውጥ ላይ ደርሰዋል…
አሁን በዚህ ሰአት ከሁለቱም ፊት ለፊት ተቀምጦ ተራ በተራ እያያቸው እያተናገረ ነው..
‹‹ሰው ምን ጊዜም ከስህተት ጋር ሚኖር ፍጡር ነው፡፡ከሰው ጋር ስንኖር ስህተት ፈላጊ ከሆን በማንኛውም ሰው ላይ ከመጠን ያለፈ ስህተቶችን በቀላሉ ማግኘት እንችላለን…..ያ ደግሞ ከሰው ጋር አያኖረንም…አንዳችን የሌላችንን ክፍተት ለመድፈን መፈጠራችንን እስካላሰብን
ድረስ ምንም ነገር ሰላም ሊሆን አይችልም፡፡ደግሞ አስቡት የጋብቻ ዋናው አስፈላጊነትም ይህ ነው ፡፡ወንድ ልጅ በራሱ ፍፅም ወንድ ብቻ አይደለም..75 ፐርሰንት የወንድነት ሆርሞን ሲኖረው 25 ፐርሰንት ግን የሴት ሆርሞን በውስጡ ይዞል..ሴቷም በተመሳሳይ 75 ፐርሰንት የሴት ሆርሞን ሲኖራት 25 ፐርሰንት የወንድ ሆርሞን ይዛለች…አያችሁ የተፈጥሮን ረቅቂነት ..ሁለቱ ሲጣመሩ ...አንድ ሙሉ ወንድና አንድ ሙሉ ሴት ይገኛል ማለት ነው፡፡ለመዋሀድ ደግሞ ፍቅር ዋናው አገኛኝ መሰላል ነው፡፡››
‹‹ግልፅ ነኝ አይደል?››
‹‹አዎ .. ቀጥል››ሲሉ የተናገሩት አቶ ኃይለ ልኡል ናቸው
ሰለሞን ንግሩን ቀጠለ‹‹በአንድ መንደር ውስጥ ትኖር የነበረች ሴት ሶስት ሽማግሌዎች ከቤቷ አካባቢ ከውጭ በፀጥታ ተቀምጠው ተመለከተች። ሴትዬዎም ከቤቷ ወጣችና ወደሽማግሌዎቹ ቀርባ" እናንተን ከዚህ በፊት አይቼያችሁ አላውቅም።ግን እዚህ በደጃፌ ለረጅም ጊዜ ተቀምጣችኋል። እርግጠኛ ነኝ እርቦችኋል። እባካችሁ ወደቤቴ ዘልቃችሁ ግብና ቤት ያፈራውን ቅመሱ››አለቻቸው።
ከመካከላቸው አንደኛው ሽማግሌ‹‹የቤቱ አባወራ በቤት አለ?››ሲሉ ጠየቋት። እሷም መለሰች‹‹አይ የለም››ስትል መለሰች።
ሽማግሌውም"ስለዚህ ወደቤት መግባት አንችልም።"ሲሉ መለሱላት።
ሴትዬዋም ወደውስጥ ተመልሳ ገባች ።መሸቶ ባሏ እንደመጣ ስለሰዎቹ ነገረችው። ባሏም
‹‹በይ አሁን ሂጂና ወደውስጥ እንዲገብ ጋብዢያቸው››አላት።
እሷም ወጣችና ወደውስጥ እንዲገብ በድጋሚ ጠየቀቻቸው‹‹ባለቤቴ ቤት ነው ያለው..ወደውስጥ እንድትገብም ጋብዛችኋል...እባካችሁ ወደ ውስጥ ዝለቁና የሆነ ነገር ቅመሱ››
‹‹እኛ በአንድ ላይ ወደውስጥ መግባት አንችልም››አሏት
‹‹ለምን ?››ግራ ገብቷት ጠየቀች።
ከሽማግሌዎቹ አንድ መመለስ ጀመረ "ይሄውልሽ ..."ወደአንደኛው ጓደኛው በጣቱ እየጠቆመ "..እሱ አቶ ሀብት ነው ወደቤትሽ ከገባ ቤትሽ በሀብት ለዘላለም እንደተሞላ ይዘልቃል።...ይሄኛው ደግሞ አቶ ስኬት ነው ከአንቺ ጋር ተከትሎ ወደውስጥ የሚገባው እሱ ከሆነ ቤትሽ በስኬት ይሞላል።እኔ ደግሞ አያ ፍቅር እባላለሁ። እኔ ከገባሁ ደግሞ በዘመንሽ ሁሉ በቤትሽ ፍቅር ሞልቶ ይፈሳል።ክፍቱ ግን አስቀድመን እንደነገርንሽ ሶስታችንም በአንድ ላይ ወደውስጥ መግባት አንችልም። ስለዚህ ወደቤትሽ ተመለሺና ከባልሽ ጋር በመማከር ከሶስታችን ማንኛችንን ወደውስጥ እንደምታስገብ ወስኑ "በማለት አብራሩላት።
እሷም እንደተባለችው ወደውስጥ ተመልሳ የሰማችውን ሁሉ ለባሏ አስረዳችው። ባሏ በሰማው ነገር ፈነጠዘ‹‹አቶ ሀብትን እንጋብዘው ፤ይግባና ቤታችን በሀብት ይሙላው፤ከእሱ የሚበልጥ ምን አለ?።››አላት።
ሚስትዬው ግን ውሳኔውን ተቃወመች"ለምን ስኬትን አንጋብዘውም፤ከሀብት ይልቅ ስኬት ነው የሚጠቅመን"አለች። እቤት ውስጥ የነበረች የልጃቸው ሚስት ወሬቸውን ስታዳምጥ ስለነበረ ወደእነሱ ቀረበችና‹‹ለምን ፍቅርን አንጋብዘውም..ከሁሉም በላይ በቤታችን ፍቅር ቢሞላ ይሻላል››የሚል ሀሳብ አቀረበች።
ጥቂት ካሠላሠሉ እና ከተከራከሩ በኃላ ባልና ሚስቶቹም በሀሳቧ ተስማሙ ፤ሚስትም ተመልሳ ወጣችና ወደእንግዶቹ ሄደች። ‹‹ከመካከላችው ፍቅርን ለመጋበዝ ወስነናል፤አያ ፍቅር እባክህ ተነስና ወደቤታችን ዘልቀህ ግባ...የተዘጋጀውን መአድም አብረኸን ተቋደስ..ሌሎቻችሁ ስላልመረጥናችሁ ይቅርታ "ስትል ተናገረች።
ፍቅር ተነሳና ወደቤት ለመግባት መንቀሳቀስ ሲጀምር ስኬትና ሀብትም ከተቀመጡበት ተነስተው ከኃላው ተከተሉት። ሴትዬዋ ግራ ገባት ‹‹አብረን መግባት አንችልም.. ከመሀላችን አንዳችንን ምረጪ አላላችሁኝም ነበር እንዴ?"ስትል ጠየቀች።
ከመሀከላቸው አንደኛው ማስረዳት ጀመረ‹‹ልጄ ስትመርጪ ስኬትን ወይም ሀብትን መርጠሽ ቢሆን ኖሮ አንዳችን ብቻ ነበር ወደቤትሽ የምንገባው።አሁን ግን የመረጥሽው ፍቅርን ነው። እኛ ደግሞ ፍቅር በገባበት ሁሉ ተከትለን መግባት ግዴታችን ነው።እኛም እራሳችን የፍቅር ምርኮኞች ነን።በዚህ ምክንያት ሶስታችንም የግድ ወደቤትሽ እንገባለን። ካዘጋጀሽውም መአድ እንቋደሳለን።ቤትሽንም ዘላለም በሚትረፈረፍ ሀብት ፤ስኬትና ፍቅር እንሞላዋለን።"አሏት። እሷም በደስታ እየፈነጠዘች ወደቤቷ ይዛቸው ገባች።
አያችሁ እናነት ሀብታም ናችሁ ስኬታማም ናችሁ…አሁን እየጣርን ያለነው ከመሀከሏችሁ ሾልኮ ተሰዶ ነበረውን ዋናውን ፍቅር ለመመለስ ነው..ፍቅር ከተመለሰ ሁሉ ነገር ሙሉ ይሆናል››
ዛሬ በዚህ በሰጠኋችሁ ምሳሌ በመሀከላችሁ፤በቤታችሁና በአካባቢያችሁ ፍቅር ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እያሰላሰላችሁ እንድታድሩ እፈልጋለው…ነገ እዚህ የምናሳልፍበት የመጨረሻ ቀናችን ነው…ተነገ ወዲያ ወደአዲስ አበባ እንመለሳለን….አሁን ዋናውን ነገር አጠናቀናል…በቀጣይ ቤታችሁ ሆናችሁ ልጃችሁም ተመልሳ ስራችሁን እየሰራች የምናደርገው ይሆናል…››በማለት የእለቱን ፕሮግራም አገባደደ
ባልና ሚስቶቹ ክፍላቸው ተያይዘው ሲገቡ የጠበቃቸው የተለየ ነገር ነበር፡፡የመኝታ ክፍላቸውን ግራና ቀኝ ግድግዳ ታኮ የነበረው ሁለት አልጋ ሁለቱም ወደመሀል ተስቦና አንድ ላይ እንዲገጥም ተደርጎ አንድ አልጋ ሆኗል….ግዙፉ የተዋሀደው አልጋ በነጭ ውብ አልጋ ልብስ ተሸፍኗል.. አልጋ ልብሱ መሀል ላይ በልዩ ዲዛይን የተሰራ ባለቀይ ቀለም የልብ ቅርፅ ይታያል..ሙሉ ወለሉ በቀይ ፅጌረዳ አበባ ከመሞላቱም በተጫማሪ ባለቆርቆሮ ልዩ ሻማ በመሀከል መሀከል ጣልቃ በማስገባት የተለያ ቀለም ያው ብርሀን እየረጩ ነው፡፡አደኛውን ግድግዳ ተጠግቶ በሚታይ ጠረጴዛ ላይ ሻማፓኝ መጠጥ ከውብ ብርጭቆዎች ጋር ይታያል…በሚገፋ ተሸከርካሪ ጠረጴዛ ላይ አስጎምዢ ምግቦች ተደርድረዋል…
ሁለቱም ባልና ሚስት በመጀመሪያ የተሳሳተ ክፍል የገቡ ነበር የመሰላቸው….የገዛ ሻንጣቸውንና ሌሎች የግል እቃዎችን ሲያዩ ተረጋጉና ወደውስጥ ዘልቀው በራፉን ዘጉት፡፡
‹‹ስንድ ይሄ ጉደኛ ልጅ የ20 አመት ጎረምሳ አደረገን እኮ..››
ወ.ሮ ስንዱ እንባቸው እየረገፈ ተናገሩ‹‹ያበቃልኝ መስሎኝ ነበር….እድሜ ለልጄ ይሄው ዳግመኛ ልጃገረድ ሆንኩ››
‹‹እንዴ ስንድ ዛሬ ሳቅና ፈንጠዝያ ነው እንጂ የምን ለቅሶ?››አሉን እጃቸውን ወደባለቤታቸው ጉንጮች በመላክ እንባቸውን ጠረጉላቸውና አቅፈው ሳሞቸው….‹‹በይ ዛሬ ምሽቱ የእኛ መሰለኝ..እንቀመጥ››
‹‹መጀመሪያ ልብሴን ልቀይርና ቀለል ያለ ልብስ ልልበስ…እስከዛ እንተ ቁጭ በል››