‹‹ጥሩ ..እኔም ቢጃማ ነገር ብለብስ ደስ ይለኛል…››አሉና ሁለቱም ወደ የሻንጣቸው ሄዱ…ከ10 ደቂቃ በኃላ ሁለቱም በለሊት ልብሳቸው ለበሱና እጃቸውን ታጥበው የምግብ ጠረጴዛው ፊት ለፊት ተቀመጡ…ከአመታት በኃለ አንደኛው በሌለኛው እጅ በፍቅርና በሳቅ ታጅበው ራታቸውን በሉና ሻምፓኛቸውን ከፈቱ..ሁሉ ነገር ውብ ነበር…ልክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደተያዩ ነው የሆነው…የሁለቱም ልብ ምት እንደወጣት ልብ ነው ከቁጥጥር ውጭ የሆነው…ከአመታት በኃላ ነው የአንዳቸው ገላ ለሌለኛቸው ምላሽ በመስጠት እንደ እሳት ጎመራ መንቀልቀል የጀመረው….ከአስራ ምናምን አመት በኃላ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ የአንደኛቸው ከንፈር ሌላኛቸው ላይ ያረፈው….የአንዳቸው እጅ የሌለኛቸውን ፓንት ወደታች አንሸራቶ ያወለቀው፡፡
///
በፀሎት እና ለሊሴ ዛሬ የመጨረሻ ቀን የወንጪ ቆይታቸው ነው፡፡በዚህም የተነሳ ቀኑን ሙሉ ላለፉት 15 ቀን ሲያስተናግዶቸው የነበሩትን ዘመዶቻቸውን በጠቅላላ እየዞሩ ተሰናብተው ጨለምለም ሲል ቀጥታ ሻንጣቸውን አንጠልጥለው የመጨረሻ አዳራቸውን በፓርክ ውስጥ ለማድረግ እነአቶ ኃይለልኡል እንዳያዮቸው እየተጠነቀቁ ቀጥታ ሰለሞን ወደ ያዘላቸው ሎጅ ነው ያመሩት፡፡ክፍላቸው ከሰለሞን ክፍል ቀጥሎ የሚገኝ ሲሆን በለሁለት አልጋ ክፍልነው፡፡
ሰለሞን አቶ ኃይለልኡልና ባለቤታውን ራት ካበላና ወደ መኝታ ቤታቸው ካስገባቸው በኃላ ሌሊሴንና በፀሎትን እራት ለመጋበዝና ውቡን የመጨረሻውን ምሽት አብሮቸው ለማሳለፍ ይዞቸው ወጣ፡፡
ከሎጃቸው ፊትላፊት ባለው ጉብታ ላይ ቁጭ ብለው ሀይቁን ቁልቁል እያዩ እያወሩ ነው፡፡
‹‹በእውነት በሕይወቴ እንደዘንድሮ አስደማሚና አስደናቂ ነገር ገጥሞኝ አያውቅም›› በማለት የጫወታውን ርዕስ የመረጠው ሰለሞን ነበር፡፡
‹‹እንዴት ማለት?››አለችው ለሊሴ፡፡
‹‹እንዴ ..ይታይሽ አንድ ሴት ዝም ብላ በስልኬ በመደውል ስራ ልቀጥርህ እፈልጋለው
…አሁን መቶ ሺብር ልላክልህ ፣ ስራውን ስትጨርስ 5 ሚሊዬን ብር እንድታገኝ
አደርጋለው››ስትለኝ መጀመሪያ ቀልድ ነበር የመሰለኝ…ይገርምሻል የባንክ ቁጥሬን አንኳን ስልክላት ቆይ እስኪ ጉዷን አያለው ብዬ ነበር…እሷ ግን ብሩን ልካ አስደመመችኝ፡፡ወዲያው ከወላጆቾ ስር ጠፍታ በሀገር አቀፍ ደረጃ የምትፈለግ ልጅ ሆና አገኘኋት..በእውነት ያንን ሳውቅ በጣም ፈርቼ ነበር፣በዛ ተገርሜ ሳልጨርስ እንቺ ለማሪያም ድግስ በጠራሽኝ ጊዜ እናንተ ቤት ቁጭ ብላ አገኘኋት….ከዛ የሁሉ ነገር መነሻ አንቺ እንደሆንሽ ተረዳሁ…ምክንያቱም ስለእኔ ከአንቺ ባትሰማና ስልኬንም ካንቺ ዘንድ ባታገኝ ይሄን ሁሉ ታሪክ አምልጦኝ ነበር…ከዚህ ሁሉ የሚገርመው ደግሞ አሁን የምሰማው ነገር ነው…የአንቺ እህት ለእሷ ልቧን መለገሷ……ይገርምችኋላ ለቀናት እንዴት ያንን ቤት መረጠች …?ብዬ ስብሰለሰል ነበር..ለካ ከዛ ቤተሰብ ጋር ያላታ ትስስር ጥልቅና በደም የተገመደ ነበር›››
‹‹ታድዬ ደግሜ ደጋግሜ ነው ያስደመምኩህ ማለት ነው››አለችው በፀሎት
‹‹በጣም..እንጂ››
‹‹ምን እሱን ብቻ እኔንም ነው ስታስደምሚኝ የከረምሽው…በተለይ በቀደም ማንነትሽን ስትነግሪኝ….አብጄ እየቃዠው ነበር የመሰለኝ››አለች ለሊሴ፡፡
ለተወሰነ ጊዜ ዝም ተባባሉና በለሊሴ ጥያቄ ሌላ ርዕስ ተከፈተ
‹‹ሶል አሁን ቤተሰቦቾን የምታገኘው ከዚህ እንደተመለስን ነው እንዴ?››ስትል ያሳሰባትን ጥያቄ የጠየቀችው፡፡
‹‹ምነው ጠየቅሽኝ?››
‹‹እኔ እንጃ የእኛ ቤተሰብ በፀሎትን እንዲህ በቀላሉ ለማጣት ዝግጁ የሚሆኑ አይመስለኝም…በተለይ ስለማንናቷ እነ አባዬ ሲያውቁ በጣም ነው የሚከብዳቸው..››
‹‹በፀሎት ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደለሊሴ ተጠጋችና አቅፋ እየወዘወዘቻት‹‹‹እህቴ ስለምን ማጣት ነው የምታወሪው…?ከአሁን ወዲህ እኔ ሁለት ቤተሰብ ነው ያለኝ…አንድ ቀን እዚህ ቤት ካደርኩ በሚቀጥለው ቀን እዛ አድርለሁ….ከተቻለ እና ሁሉም ከተሳማማ ደግሞ ሁላችንም ተሰብስበን አንድ ቤት ውስጥ እንድንኖር ነው የምፈልገው…እርግጥ ይሄ በአንዴ አይሆንም አውቃለው…ግን ሁለቱም ቤተሰቦቼ ቀስ በቀስ በደንብ እንዲተዋወቁና እንዲግባቡ ካደረግኩ በኃላ አንድ ላይ ሰበስባቸዋለው…የቦሌው ቤታችን እኮ አርባ ምናምን
ክፍል ነው ያለው…ከዛ ውስጥ አስሩን አንኳን አንጠቀምበትም…..እና እህቴ ስለመለያየትና ስለማጣት ምንም አታስቢ››
ለሊሴም‹‹እህቴ በጣም ነው የምወድሽ….ከእህቴ ሀዘን እንድፅናና ስላደረግሺኝ አመሰግናለው፡፡››ብላ እሷም በተራዋ አቅፋ ጉንጮን ሳመቻት፡፡
‹‹በቃ በቃ…መላቀሱ ይብቃችሁ…ለማንኛውም በፀሎት ቤተሰቦችሽን የምታገኝው እንዴት እና መቼ እንደሆነ ነገ ጥዋት ቁርስ እየበላን እናወራለን፡፡››
‹‹ለምን አሁን አናወራም… ?››መለሰችለት
‹‹አይ አሁን መሽቷል…ተነሱ እናንተም ወደክፍላችሁ ግቡ››ብሎ ቀድሞ ተነሳ..ለሊሴና በፀሎትም ተከትለውት ተነሱ
ሰለሞን እነሱን ወደክፍላቸው አስገብቶ ወደገዛ ክፍሉ ገባና ቢጃማውን ቀይሮ ቀድሞ ያዘጋጀውን ቢራ ከፈፍቶ መጠጣት ጀመረ…ሁለት ጠርሙስ ካገባደደ በኃላ አስቴር ትዝ አለችው፡፡ ሞባይሉን አነሳና ሰዓቱን ተመለከተ፡፡ ከምሽቱ አራት ሰዓት አልፏል…ደወለ….ከበርካታ ጥሪዎች በኃላ ተነሳ፡፡
‹‹ሄሎ ኪያ ተኝታሻል እንዴ ?ቀሰቀስኩሽ?››
አስቴር መለሰችለት‹‹አይ ወንድሜ ገና ለመተኛት እየተዘገጃጀው ነበር፡፡››
‹‹ደህና ነሽ?››
‹‹ደህና ነኝ…ምነው ቆየህ እኮ !አልጨረስክም አትመጣም እንዴ?››
‹‹ነገ ከሰዓት የምመጣ ይመስለኛል፡፡››
‹‹ጥሩ ነው…ልደውልልህ ነበር…››
‹‹ምነው በሰለም…፡፡››
‹‹አይ የፊታችን እሁድ የመስፍኔ ልደት ስለሆነ ሰርፕራይዝ ላደርገው አስቤላው…አንተም እንድትገኝ እፈልጋለሁ››
‹‹እንዴ እስከአሁን ወደመጣበት አልሄደም እንዴ?››
‹‹አይ ቀረ እኮ ….በፊትም ጥዬሽ የሄድኩት እየቆጨኝ ነው….ትዳሬን አክብሬ እዚሁ እየሰራሁ ከአንቺ ጋር ልጄን አሳድጋለው አለኝ››
‹‹እና መፋታቱን ሙሉ በሙሉ ተዋችሁት ማለት ነው?››
‹‹አንተ ደግሞ ስለምን መፋታት ነው የምታወራው….?በቃ ደህና እደር በሰላም ተመለስልኝ…መስፍኔ ከመኝታ ቤት እየጠራኝ ነው…››ብላ ስልኩን ዘጋችው፡፡
ጨጓራው ሲለበልበው ይታወቀዋል…በቃ ውስጡ እየነደደ ነው…አሁን ምንም የማያውቀውን አዲስ ነገር አልነገረችውም…ምን እንዳበሳጨው ለራሱም አልገባውም….ሌላ ቢራ ከፈተና አንደቀደቀው…ስልኩን ደግመኛ አነሳና ደወለ…
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose