አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር በቅርቡ የተገበረውን ሪፎርም አስመልክቶ ከአጠቃላይ ሰራተኞቹ ጋር ዛሬ ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም በግራንድ ኤሊያና ሆቴል ውይይት አድርጓል።
ትግበራ ላይ የዋለው ሪፎርምን እና አንዳንድ በተቋሙ ውስጥ የተደረጉ የአሰራር ለውጦችን አስፈላጊነት ያስረዱት የኅብረት ስራ ማህበሩ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘሪሁን ሸለመ አዋጭ ከትንሽ ተነስቶ አሁን ላይ ከ380 በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞች የስራ እድል መፍጠር በመቻሉ ደስተኛ ነኝ ብለዋል።
አክለውም ሰራተኞች በተመደቡበት የስራ መስክ የአገልጋይነት መንፈሳቸውን ይበልጥ በማዳበር በቅንነት እና በታማኝነት አባላትን እንዲያገለግሉ ጠይቀዋል።
የአዋጭ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ መስፍን ገ/ስላሴ ኅብረት ስራ የድህነት ማስታመሚያ ሳይሆን የሃብት ማፍሪያ መሆኑን አዋጭ በአባላቶቹ አረጋግጧል ያሉ ሲሆን ሰራተኞቹንም ከዚህ በላይ ጠንክራችሁ በመስራት የላቀ ውጤት ማስመዝገብ ትችላላችሁ በማለት አበረታተዋል።
የአዋጭ ሰራተኞች በበኩላቸው በተደረገው ሪፎርም መደሰታቸውን ገልፀዋል።