#Mpox #Ethiopia
ኢትዮጵያ ውስጥ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ተገኝቷል ?
“ የእኛም ሰዎች እዛ ሂደው ስላዩ አረጋግጠዋል ሞንኪፖክስ አይደለም፡፡ ቺክንፖክስ ነው ” - ጤና ሚኒስቴር
ኦክስፋም ኢትዮጵያ የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በሶማሌ ክልል በዝንጀሮ ፈንጣጣ (Mpox) የተጠረጠረ ኬዝ መገኘቱን የሚያሳይ አጭር ሪፖርት ትላንት ይፋ አድርጎ ነበር፡፡
ሌላ አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀ ድርጅትም እዛ ካሉ ሰዎቹ የበሽታው ኬዝ በሶማሌ ክልል መገኘቱን እንደሰማ ገልጿል።
አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የሶማሌ ክልል ባለስልጣን ግን " ምንም የተገኘ ነገር የለም ውሸት ነው ያወጡት ሪፖርት " ብለውናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ እውነት ተከስቷል ? የሚለውን ጉዳይ ለማጣራት ሞክሯል፡፡
ጤና ሚኒስቴርንም በሽታው ወደ ሀገራችን ገብቷል እንዴ ? ሲል ጠይቋል።
የጤና ሚኒስትር ዴዔታ ደረጀ ጉዱማ (ዶ/ር) በሰጡን ምላሽ፣ “ አላጋጠመም፡፡ ያው ለነገሩ ትላንትም አረጋግጠን ነበር፤ ሰዎቹ (ኦክስፋም ኢትዮጵያን ማለታቸው ነው) የለጠፉትን እንዲያነሱ እያደረኩ ነበር፡፡ ቺክንፖክስ ነው ” ሲሉ ገልጸውልናል፡፡
“ የእኛም ሰዎች እዛ ሂደው ስላዩ አረጋግጠዋል ሞንኪፖክስ አይደለም፡፡ ቺክንፖክስ ነው፡፡ በእርግጥ ይመሳሰላል ሲምፕተማቸው፡፡ እንደ ቤተሰብ ሀፕን ያደረገ ነው፡፡ ኦረዲ ሌሎቹም ሪከቨር ስላደረጉ ሳምፕልም ወስደን ቼክ አድርገናል ሞንኪይፖክስ አይደለም ” ነው ያሉት፡፡
“ ቺክንፖክስ የሚባል አለ ፤ ሌላ በሽታ አለ ቀለል ያለ፡፡ ይህ ብዙ ቦታዎች አለ፤ ሰሞኑን ይሄኛው ስለተነገረ፣ ሰው ሲጠራጠር ቁስል፣ ቀላል የቆዳ ኢንፌክሽን እየመጣ ስለሆነ ከጥርጣሬ የተነሳ ነው ” ሲሉም ተናግረዋል፡፡
“ በእርግጥ ጥሩ ነው እንደዛ መሆኑ ግን ውዢምብርም ሊፈጠር ስለሚችል ጥንቃቄ አድርጉ፣ ፖስት እንዳታደርጉ ሚኒስቴሩ ነው ፖስት ማድረግ ያለበት ቼክ አድርጎ ከተፈጠረም፡፡ ሰስፔክትም አይባልም፡፡ ሰስፔክት በራሱ የራሱ ደፊኔሽን አለው ” ብለዋል፡፡
ቺክንፖክስ ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ጋር ተመሳሳይ ነው እንዴ ? ስንል የጠየቅናቸው ሚኒስትር ዴዔታው፣ “ ተመሳሳይ ነው፡፡ ከ100 በላይ ተመሳሳይ ምልክቶች ያሏቸው የቆዳ ኢንፌክሽኖች፣ ሌሎችም ኢንፌክሽኖች አሉ ” ብለዋል፡፡
የዝንጀሮ ፈንጣጣ በኢትዮጵያ ደረጃ ተከስቷል ? አልተከሰተም ? ለህዝቡስ ምን የጥንቃቄ መልዕክት ታስተላልፋለችሁ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ አቅርቧል።
ሚኒስትር ዴዔታው፣ “ ምንም ነገር የለም በርካታ ሳምፕሎችን ወስደን ቴስት አድርገናል፡፡ የእኛ ልጆች በየክልልም እየወረዱ በሁሉ ቦታ ላይ ሩመር ሲነሳ ያያሉ፡፡ ኢንቨስቲጌት ያደርጋሉ፡፡ ሳምፕል ይወስዳሉ፡፡ ሳምፕሉ ወደ እኛ ወደ ላብራቶሪ ይላክል፡፡ በርካታ ቴስቶች አድረገናል፡፡ ግን ምንም የለም ኔጌቲቭ ነው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
“ ኤርፖርት ላይ ሥራችንን አጠናክረን ቀጥለናል፡፡ መግቢያና መውጫ በሮች ላይ የተያዩ ምልክቶችን እናያለን በተለይ ትኩሳት ያላቸውን ሰዎች እንለያለን፡፡ የትኛውም ቆዳቸው እብጠት ካለ እያረጋገጥን እንገኛለን ” ብለዋል፡፡
“ ማህበረሰቡ ግን ይህን አይነት ምልክት ካለ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል ግን በተለይ ለጤና ተቋማት ሪፖርት እንዲያደርግ ነው የሚጠበቀው፡፡ እንደዛ አይነት ሰው ካለ ደግሞ ንክኪ እንዳይኖር ጥንቃቄ ማድረግ፡፡ ንክኪም ካለ ቶሎ በአግባቡ እጅን መታጠብ፣ በፍጥነት ወደ ጤና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል ” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
NB. ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን መረጃ ከጤና ሚኒስቴር ጠይቆ ባዘጋጀበት ሰዓት ኦክስፋም ኢትዮጵያ " በሶማሌ ክልል በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተጠረጠረ ኬዝ ተገኝቷል " የሚለውን መረጃ ከገጹ ላይ አጥፍቷል።