የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ለ3 ሺህ 611 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረጉ
የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ቢሮ በጉዳዩ ላይ በሰጠው መግለጫ በክልሉ ህጉን መሰረት በማድረግ ይቅርታ መደረጉን ገልጸዋል።
የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ጉዮ ዋሪዮ በመግለጫቸው የክልሉ የይቅርታ ቦርድ በየደረጃው ማጣራት አድርጎ ለፕሬዚዳንቱ በማቅረብ ለህግ ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጓል።
ይቅርታ ከተደረገላቸው የህግ ታራሚዎች መካከል 3 ሺህ 334 ወንዶች ሲሆኑ ፤ 247 ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን አመልክተዋል።
ይቅርታ የተደረገላቸው የህግ ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም ባህሪ ማሰየታቸውና ከቅጣቱ መማራቸው በሚመለከተው አካል የተረጋገጠ መሆኑን አንስተዋል።
ታዳጊ ታራሚዎች ሆነው አንድ አራተኛ የእስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ እና ልጅ ይዘው በማረሚያ ቤት የሚገኙና እረጉዝ ሴቶች ይቅርታ ከተደረገላቸው መካከል መሆኑን ዐቃቤ ህጉ ገልጸዋል።
በተጨማሪም እድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ አዛውንቶችና የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው ከ10 ዓመት በላይ በማረሚያ ቤት ያሳለፉ ይቅርታ እንደተደረገላቸው ተናግረዋል።
በይቅርታው ካልተካተቱት መካከል የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው፣ በተደጋጋሚ ወንጀል የተሳተፉ፣ ዘረፋ፣ በሙስና እና በአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች የተሳተፉትን እንደማይመለከት አስረድተዋል።