Never give up!
ህይወት ተገማች አይደለችምና ትናንት ሌላ ሰው ነበርክ፣ ዛሬም እንዲሁ ሌላ ሰው ሆነሃል፣ ለውጥህ ነገም እንዲሁ ይቀጥላል። የሚጓዝ ስው ይደናቀፋል፤ ግፋ ሲልም ይወድቃል፤ ይጋጋጣል፤ ይጎዳል፤ ይታመማል። ነገር ግን በእንቅፋቱ ምክንያት ከመንገዱ አይገታም፤ በውድቀቱ ምክንያት ወደኋላ አይመለስም፤ በጉዳቱ ምክንያት ሊሔድ ካሰበበት ቦታ አይቀርም። ምንም ያጋጥምህ በማቆም የሚመጣው ሽንፈት፣ በማቋረጥ የሚያገኝህ ተስፋ መቁረጥ እንዳይቆጣጠርህ እራስህን አበርታ። አንድ ሁለቴ ልትሸነፍ ትችላለህ፣ ወደኋላም ልትመለከት ትችላለህ ተስፋ ቆርጠህ ያቆምክበት ወቅት ግን የመጨረሻው አንገት አስደፊ የስቃይ ሽንፈትህ ይሆንብሃል። ለሽንፈት እጅ እንዳትሰጥ፤ በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ፤ ድሉ ያንተ እንጂ የሽንፈትህ፣ የተስፋ መቁረጥህ፣ የውድቀትህና የበታችነትህ አይደለም። ያቆምክ እለት ሽንፈትህ ይጀምራልና ምንም እንኳን ቢከብድህ መቼም ጥረትህን እንዳታቆም፤ እንዳታቋርጥ።
Via fb(meta) page