"መፈንቅለ መንግስት አላደረኩበትም‼️
" ጌታቸው ላይ መፈንቅለ መንግስት ፈፅሜ ከሆነ በገለልተኛ አካል ይጣራ "
- ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ ጀነራል) " አውራ እምባ ታይምስ " ከተባለ ሚድያ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርገው ነበር።
በዚህም ወቅት በትግራይ ተካሂደዋል ተብሎ ተደጋግሞ ስለሚነገረው የመፈንቅለ መንግስት ጉዳይ ተጠይቀው መልሰዋል።
በቀድሞ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ሃይል ባለፈው ባወጣው መግለጫ " በትግራይ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በማካሄድ ስልጣን ከተያዘ 40 ቀናት ተቆጠረዋል " ብሎ ነበር።
ይኸው ኃይል " የአቶ ጌታቸው አስተዳደር ህገ-ወጥ ተግባሩ ተጋግሎ ወደ ተባባሰ ግጭት እንዳያመራ ስልጣን ጭምር ለሰላም ሲል አሳልፎ ሰጥቷል " የሚል አገላለፅም ተጠቅሞ ነበር።
ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ፥ " ጌታቸው ረዳ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አካል ሆኖ በተቋቋመው ጊዚያዊ አስተዳደር ወደ ኃላፊነት የመጡ ናቸው " ያሉ ሲሆን " ወደ ሃላፊነት መጋቢት 2015 ዓ.ም ነው የመጡት። የጊዚያዊ አስተዳደሩ ቆይታ ሁለት ዓመት መሆኑ ይታወቃል።
እንዲያ ሆኖም 6 ወር ሊራዘም ይችላል። ይሁን እንጂ የነበረው ጊዚያዊ አስተዳደር ለ6 ወራት ለማራዘም የሚያስገደድ በቂ ምክንያት አልተገኘም " ብለዋል።
" መጋቢት 2015 ዓ.ም ወደ ሃላፊነት የመጡት አቶ ጌታቸው መጋቢት 2017 ዓ.ም የሁለት ዓመት ቆይታቸውን ጨርሰዋል " ሲሉ አስረድተዋል።
" አሁን የተደረገው በፓርላማ በፀደቀ አዋጅ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ለአንድ ዓመት ማራዘም ነው።
በተራዘመው የጊዚያዊ አስተዳደሩ ዕድሜ የነበረው ፕሬዜዳንት ሊቀጥል ላይቀጥል ይችላል። አጋጣሚ ሆኖ አቶ ጌታቸው በሃላፊነት አልቀጠለም " ሲሉ ገልጸዋል።
"እኔ እንደ አዲስ በተራዘመው ጊዚያዊ አስተዳደር ወደ ሃላፊነት መጥቻለው። በትግራይ የሃላፊነት ጊዜው ጨርሶ ከሃላፊነት የወረደ እንጂ የተካሄደ መፈንቅለ መንግስት የለም። መፈንቅለ መንግስት አልተካሄደም ብቻ ሳይሆን ወደዛ የሚወሰድ ምክንያትም አልነበረም " ብለዋል።
" ያን ያህል ጉዳዩ አሳሳቢ ሆኖ መፈንቅለ መንግስት ተካሂደዋል ? ወይስ አልተካሂደም የሚል ክርክርና እሰጣ ገባ ካለ ለሦስተኛ ወገን እድል እንስጥ። የሚያጣራ አካል ይኑር።
ምናልባት እኔ ይህንን ጉዳይ የሚያጣራ አካል ላቋቁም ብል ተአማኒነትና ተቀባይነት ላይኖረው ስለሚችል ሦስተኛ አካል የሆነ ኮሚቴ ቢያጣራው እላለው " ሲሉ መልሰዋል።
"በጌታቸው ላይ መፈንቅለ መንግስት ፈፅሜ ከሆነ በገለልተኛ አካል ይጣራ " ሲሉም አክለዋል።
====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s