ህወሓት በሁለት ቡድን ተከፍሎ እየታመሰ ነው ሲሉ የቁጥጥር ኮሚሽን ሊቀመንበሩ ገለፁ‼️
ህወሓት በሁለት ኔትወርክ ተከፍሎ እየታመሰ ነው ሲሉ የቁጥጥር ኮሚሽን ሊቀመንበሩ ተክለብርሃን አርአያ መግለጻቸዉ ተሰምቷል፡፡
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ለ11 ቀናት ያካሄደው ዝግ ሰብሰባ የአቋም መግለጫ በማውጣትና በያዝነው ወርሃ ሀምሌ ጉባኤ ለማካሄድ ወስኖ ማጠናቀቁ መዘገባችን ይታወሳል።
ህወሓት ዝግ ስብሰባውን በማስመልከት የድርጅቱ የቁጥጥር ኮሚሽን ሊቀመንበር ተክለብርሃን አርአያ ከድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ጋር ቃለ-መጠይቅ አካሄደዋል።
ስብሰባውና ግምገማው ከመጀመሪያው በውጭ የተጠናቀቀ መጠላለፍ እና ተንኮል ያየለበት እንደነበር የገለፁት ሊቀመንበሩ የአመራር አንድነት አልነበረም ሲሉ ገልጸዋል።
ስብሰባውና ግምገማው በሁለት ኔትወርክ የተከፈለ እንደነበረ የገለጹት ሊቀመንበሩ በሰብሰባው የመናገር እድል ያገኘው ደጋፊ እንጂ ተቃዋሚ አይደለም ተነፍጎታል " በማለት አብራርተዋል።
የመናገር እድል ያገኙ ደጋፊዎች ለአንድ ወይም ለግማሽ ሰአት ብቻቸውን በመናገር የስብሰባ ጊዜ ሲያባክኑ ታይተዋል " ያሉት ተክለብርሃን " ስብሰባውና ገምገማው ነፃና ዴሞክራሲያዊ አልነበረም" ሲሉ ተናግረዋል።
" የተፈጠረውን ችግር ለማጣራት የተቋቋመው ኮሚቴ በህወሓት ውስጥ ሁለት ኔትወርክ መኖሩን አረጋግጧል " የሚሉት ሊቀመንበሩ " ኔትወርኩ ሳይበጣጠስ የአመራር አንድነት አይረጋገጥም " ብለዋል።
" ስብሰባውና ገምገማው አሰልቺ ከመሆኑ የተነሳ ' ተሰበሰብኩ አልተሰበሰብኩ ለውጥ የለውም ' በማለት መድረኩን ረግጠው የወጡ አመራር አሉ " ያሉ ሲሆን ፣ ግምገማው የሚፈለገውን ፍሬ አላፈራም "በማለት አክለዋል።
#አዩዘሀበሻ
👉ትኩስ ዜናዎችን ለማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s