Ayu Zehabesha-Official አዩዘሀበሻ


Channel's geo and language: Ethiopia, English


በዚህ ቻናል ሀገራዊና አለምአቀፋዊ መረጃዎችን በፍጥነት ያገኛሉ❗
የውስጥ መስመር👉http://t.me/ayulaw

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, English
Statistics
Posts filter


እነዚህ መኪኖች ወደ ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ የተለያዩ ጭነቶችን እና መድሃኒቶችን ለማድረስ የተንቀሳቀሱ ቢሆንም በአካባቢው በሚያጋጥም ተደጋጋሚ የፀጥታ ችግር ምክንያት መንገድ ላይ ከቆዩ ከአንድ ወር በላይ እንደሆናቸው አሽከርካሪዎቹ ገልፀውልኛል። በዚህ የተነሳ በደራ  አንድ ግልኮስ 2000ሺ ብር እየተሸጠ ነው ብለውኛል። በየቀኑ ሞት አለ ተኩስ አለ ህዝቡ ስጋት ላይ ነው። ከትናንት በስተያ በታጣቂዎች ሶስት ሰዎች ተገድለዋል ብለዋል።
ከደራ ወረዳ ወደ ሰላሌ ዩኒቨርስቲ ለ12ኛ ክፍል ፈተና የሄዱ ከ400 በላይ ተማሪዎች እጀባ የሚያደርግላቸው የፀጥታ ሀይል በማጣታቸው እስካሁን መመለስ አልቻሉም። ተማሪዎቹን ለመመለስ የተመደቡ ከ200 በላይ መኪኖችም እየተገላሉ ነው ብለውኛል(አዩዘሀበሻ)።
=======================
ትኩስ ያልተሰሙ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join አድርጉ+ለሌሎች ጋብዙ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ውስን ቤቶች ቀሩ‼️
በልዩነት የቀረበ #ትራኮን❗
  +251937979700
ትራኮን ሪል እስቴት(Tracon realestate )
👉 በ50,000 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ
      ኮምፓውንድ ,  በከፍተኛ ጥራት እና
      በልዩ ዲዛይን የተገነቡ ውብ    
      አፓርትመንቶች
👉  በለቡ መድሀኒያለም 
👉  90% የተጠናቀቀ
👉  በ25% ቅድመ ክፍያ
👉  50%የባንክ ብድር የተመቻቸለት
👉  በ 1 አመት  ውስጥ የሚረከቡት

ትራኮን በምን ይለያል???🤔🤔🤔🤔

🦋በኢትዮጵያ ብር ብቻ መሸጡ እና ዶላር
     አለመጠቀሙ
🦋 በወለል 4 ቤቶች
🦋በወለል 4 ሊፍቶች
🦋 ሶስት ቆንጆ እይታ ያላቸው በረንዳዎች
🦋 የከርሰ ምድር ውሃ
🦋 ቆሻሻ ማስወገጃ
🦋 ሲሲቲቪ ካሜራ
🦋 ሴንትራል ዲሽ
🦋 በቂ የመኪና መቆምያ
🦋 አውቶማቲክ ጄኔሬተር
🦋 መዋኛ ገንዳ(ለህፃናት እና ለአዋቂ)
🦋 የልጆች መጫወቻ
🦋 አረንጋዴ ስፍራ
🦋 የስፖርት ቦታዎች (2 የሜዳ ቴኒስ ,
                                1 የቅርጫት ኳስ )
🦋 ሳይክል መንጃ
🦋 የመሮጫ ሜዳ

ለበለጠ መረጃ : ለቢሮ ቀጠሮ ,ሳይት ለመጎብኘት ይደውሉ።
        +251937979700
የሽያጭ ሱፐርቫይዘር : ኪሩቤል
            0937979700

         በልዩነት የቀረበ!!!!!!!


ጎፋ‼️
ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ የደረሰባቸውን ሰዎች ለመጎብኘት ዛሬ ጠዋት ወደ ጎፋ ማቅናታቸውን የደረሰኝ መረጃ ያመላክታል።
#አዩዘሀበሻ
=======================
ትኩስ ያልተሰሙ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join አድርጉ+ለሌሎች ጋብዙ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


በ8% ብቻ ቅድመ ክፍያ የቤት ባለቤት ይሁኑ

ከ ቦሌ ኤርፖርት በቅርብ ርቀት በሚገኘው "ለቡ መብራት ሃይል" 65,395 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ዘመናዊ መንደር እየገነባን እንደሆነ ሰምተዋል?

*ለኢንቨስትመንት ቢሉ ለመኖሪያ

69 ካሬ  ባለ አንድ መኝታ
99 ካሬ ባለ ሁለት መኝታ
139 ካሬ ባለ ሶስት መኝታ

ለየት ባለ የቤት ዲዛይን

በሶስት አመት 50% ብቻ በመክፈል 50% ብድር አመቻችተናል

*ከ4,500 በላይ አባወራ በሚኖርበት በዚህ ዘመናዊ መንደር ልነግድ ካሉን ደሞ ከ39 ካሬ ጀምሮ እስከ 965 ካሬ ድረስ የንግድ ሱቆችን በመሸጥ ላይ ነን

ማስታወሻ ከ4% ጀምሮ በመክፈል መመዝገብ ይችላሉ

እያለቀ ነው አሁኑኑ ይደውሉልን
0937764111


አዲሱ ቅጣት ተግባራዊ እየሆነ ነው‼️
👉አሽከርካሪዎች ለትምህርት ተጠቀሙበት❗
ትናንት ሐምሌ 19/2016 በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በመሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ያደረሱ ግለሰቦች ህዝቡ በሰጠው ጥቆማ መሰረት በደንብ ጥሰት ተቀጥተዋል።

በዚህም መሰረት ፦                       
               
1.ቦሌ ክ/ከተማ

የኮቨርስቶን መንገድ የሠበረ  አንድ ተሽከርካሪ  5,000  ብር ተቀጥቷል። እንዲሁም በዚሁ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ተረፈ ምርት (ቆሻሻ) በዋና መንገድ ላይ ያወረደ ተሽከርካሪ  50,000 ብር ተቀጥቷል።

2. ቂርቆስ ክ/ከተማ
ሞተር ሳይክል በእግረኛ መንገድ ላይ ያቆመ ግለሰብ 3,000 ብር ተቀጥቷል።

አካባቢያቸዉን ያቆሸሹ ሁለት ሱቆች በአጠቃላይ 20,000 ብር ሲቀጡ፣ አከባቢውን ያቆሸሸ አንድ የፅዳት ማህበር 20,000 ብር ተቀጥቷል።

3. ልደታ ክ/ከተማ ደግሞ አንድ ተሽከርካሪ መንገድ የማበላሸት ተግባር በመፈፀሙ 50,000 ብር ተቀጥቷል።
=======================
ትኩስ ያልተሰሙ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join አድርጉ+ለሌሎች ጋብዙ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


መሃል ፒያሳ ላይ ሱቅዎን ይግዙ‼️

📌 ከዓድዋ ሙዚየም ፊትለፊት ፣ ከቴድሮስ አደባባይ ወደ ሙሀሙድ ሙዚቃ ቤት በሚወስደው ዋና መንገድ ላይ መገንባት ላይ የሚገኘዉን የገበያ መአከላችንን ለሽያጭ ማቅረባችንን ስናበስራቹ በታላቅ ደስታ ነዉ።

📌  አከራይተዉ የሚያገኙበት ፣ ነግደው የሚያተርፉበት ነውና ዛሬዉኑ የግሉዎ ያድርጉ።

✅ በ 750,000 ቅድመ ክፍያ
✅ ከ 30 ካሬ ጀምሮ

✅1400 ካሬ ላይ ያረፈ
✅ አመቺ በሆነ የአከፋፈል መርሀ ግብር በ1 ዓመት ውስጥ ተረክበው የሱቅ ባለቤት ይሁኑ
       
ለበለጠ መረጃ
📲 0983638578

WhatsApp: https://wa.me/c/251983638578
Telegram: https://wa.me/mahii15


Update‼️
የህወሓት ሊቀ-መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ዛሬ ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ “ድርጅታችን ህወሓት በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ስለወሰነ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በአዲሱ አዋጅ መሰረት እውቅና እንዲሰጠን እንጠይቃልን” የሚል ደብዳቤ አስገብተዋል ተብሏል።
የህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል ሰሞኑን ከፌዴራል መንግስትና ምርጫ ቦርድ ጋር በአዲስ አበባ በነበራቸው ውይይት “ህገወጥ ጉባኤ ካድረጋችሁ በህግ እንደምትጠየቁ እወቁ” የሚል መልስ እንደተሰጣቸው የተገለፀ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩም በተቃዋሚዎች ስብሰባ ላይ ህወሓት
አሁን ማድረግ ያለበት ምርጫ ቦርድ ጋር ሄዶ፣ በ 2-3 ሳምንት ዉስጥ የሚጠበቅበትን ዶክመንት አሟልቶ፣ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ ጉባኤውን ማካሄድ እንዳለበት ማስገንዘባቸው ይታወሳል።
ህወሀት የመንግስትን አቅጣጫ በመቀበል ህጋዊ ፓርቲ ለመሆን የተቃረበ ይመስላል።
#አዩዘሀበሻ
=======================
ትኩስ ያልተሰሙ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join አድርጉ+ለሌሎች ጋብዙ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


ታወጀ‼️
ለ3 ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ታወጀ‼️
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ወረዳ የደረሰውን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ ሕይወታቸው ላለፉ ዜጎች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከነገ ጀምሮ ለ3 ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሐዘን አውጇል።
#አዩዘሀበሻ
=======================
ትኩስ ያልተሰሙ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join አድርጉ+ለሌሎች ጋብዙ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


የሶማሊያ መንግስት በተደጋጋሚ የሚያወጣቸውን የትንኮሳ መግለጫዎች ኢትዮጵያ በቅርበት እየተከታተለችው ነው"- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር‼️
ኢትዮጵያ “የሶማሊያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፤ ኢትዮጵያ ለሶማሊያ መልሶ ግንባታ እያደረገች ያለውን ወሳኝ ሚና ላለመቀበል በሚያደርጉት ሙከራ በተለያዩ አጋጣሚዎች በሚሰጡት አላስፈላጊና ኃላፊነት የጎደለው መግለጫዎችን በቅርበት እየተከታተለችው መሆኑን" ገለጸች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ ኢትዮጵያ “የሶማሊያ መንግስት በተደጋጋሚ የሚያወጣቸውን የትንኮሳ መግለጫዎች ኢትዮጵያ እየተከታተለች መሆኑን” ገልጿል፡፡

የሶማሊያ መንግስት ከሚያቀርባቸው "መሰረተ ቢስ ክሶች" በተቃራኒ ኢትዮጵያ ወንድም ለሆነው የሶማሊያ ህዝብ ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን ከሦስት አሥርት ዓመታት ለበለጠ ጊዜ መስዋዕትነት እየከፈለች ተገኛለች ብሏል መግለጫው፡፡

ለቀጣናዊ ነፃነት፣ ባህላዊ ትስስር፣ በደምና በላብ የተገነባውን ታሪካዊ ግንኙነት ከግምት በማስገባትም ኢትዮጵያ ለተሰነዘሩባት መሠረተቢስ ክሶች ምላሽ መስጠትን እንዳልመረጠች የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ ከዚህ ይልቅ ኢትዮጵያ ለሀገራቱ ህዝቦች የጋራ ተጠቃሚነት ትዕግስትንና አዎንታዊ ተሳትፎን አማራጭ ማድረጓን አመላክቷል።

ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ከአቡደዋቅ ከተማ በሰሜን ምዕራብ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሺይላማው መንደር በሶማሊላንድ ሚሊሻዎች፤ የተለያዩ የጦር መሳሪያ የጫኑ ሁለት የጭነት መኪናዎችን መያዛቸውን ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ የሶማሊያ ባለስልጣናት የጦር መሳሪያዎቹ ከኢትዮጵያ የመጡ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው መግለጫ፤ “በአፍሪካ ቀንድ የሚደረጉ ህገወጥ የቀላል ጦር መሳሪያዎች ዝውውር ጉዳይ በጥልቀት እንደሚያሳስባት” አስገንዝቧል፡፡

ቀጣናው በግጭቶች፣ በማይፈተሹ የጠረፍ መስመሮች እንዲሁም በድንበር የደህንነት ችግሮች እየታመሰ በመሆኑ የቀጣናው ሀገራት እንዲህ ዓይነት ወንጀሎችን ለመዋጋት ኃይላቸውን ለማሰባሰብ እንደሚያገደዱ አመላክቷል፡፡
=======================
ትኩስ ያልተሰሙ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join አድርጉ+ለሌሎች ጋብዙ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s




የህወሓት ቁጥጥር ኮምሸን ዛሬ ሀምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም የጋራ መገረለጫ ሰጥቷል‼️
እሁን እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ወንበር ለማዳ እንጂ ህዝብ እና ድርጀት ለማዳን አይደለም ሲሉ የህወሓት ቁጥጥር ኮምሽን አባላት ገለፁ።

ትላንት በህዝባችን ላይ ያደረስነው ጉዳት ተረድተን ህዝባችን እናድን ህዝባችን በጃ ምክንያት ሌላ መከራ እና ጉዳት እንዳይደርሰው ራሳችን አግልለናል።

የህወሓት ቁጥጥር ኮምሽን አባላይ የሰጡት የጋራ መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች:-

👉#በድርጅቱ ውስጥ መርህ ጠፍቷል።

👉ኔትዎረክና መቧደን እየሰፋ መጥቷል።

👉#የቁጥጥር ኮምሸን አሰራሮች እየተጣሱ ቀጥለዋል።

👉#ስልጣን ያለ አግባብ መጠቀም እየበዛ መጥቷል።

👉 #ፀረ ዲሞክራሲየ‍አዊነት ተበራክቷል።

👉 #ግልፅነት፣ ዴሞክራሲያዊነትና የድርጅቱ የተሳትፎ መርህ እየተጣሰ እየሄደ ነው።

👉 #ዘጠኝ አባላት ያሉት አዘጋጅ ኮሚቴ ቢቋቋም ስራው ግን በሌሎች ተጠልፎ ለጥቅም እና ስልጣን ጉጉት ያላቸው አመራሮች  እየዋለ ነው።

👉#ቁጥጥር ኮምሽኑ የሚወስናቸው ውሳኔዎች ያለ አግባብ እየተለወጡ ለሌሎች ጥቅም እየዋለ ነው።

👉#ስለጣን ልቀቅ አልለቅም በሚል የሁለት ቡድኖች  ፍላጎት የህዝባችንን ስቃይ እንዲራዘም አንፈልግም።

👉#አካሄዳችን ህዝባችን በሚጠቅም።

👉#በአከባቢ  ስም የሚደረግ ንግድም ይቁም።

👉#እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን የሚል ሃሳብ ቁሞ ሁሉም የተግባባበትና የተማመነበት ጉባኤ መካሄድ አለበት።

👉#ከኔትዎርክ ሳንፀዳ የሚካሄድ ጉባኤ ህዝባችን ወደ አደጋ የሚከት ነው"ብሏል።
#አዩዘሀበሻ
=======================
ትኩስ ያልተሰሙ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join አድርጉ+ለሌሎች ጋብዙ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


መሃል ፒያሳ ላይ ሱቅዎን ይግዙ‼️

📌 ከዓድዋ ሙዚየም ፊትለፊት ፣ ከቴድሮስ አደባባይ ወደ ሙሀሙድ ሙዚቃ ቤት በሚወስደው ዋና መንገድ ላይ መገንባት ላይ የሚገኘዉን የገበያ መአከላችንን ለሽያጭ ማቅረባችንን ስናበስራቹ በታላቅ ደስታ ነዉ።

📌  አከራይተዉ የሚያገኙበት ፣ ነግደው የሚያተርፉበት ነውና ዛሬዉኑ የግሉዎ ያድርጉ።

✅ በ 750,000 ቅድመ ክፍያ
✅ ከ 30 ካሬ ጀምሮ

✅1400 ካሬ ላይ ያረፈ
✅ አመቺ በሆነ የአከፋፈል መርሀ ግብር በ1 ዓመት ውስጥ ተረክበው የሱቅ ባለቤት ይሁኑ
       
ለበለጠ መረጃ
📲 0983638578

WhatsApp: https://wa.me/c/251983638578
Telegram: https://wa.me/mahii15


ሌላ አደጋ‼️
በቤንቺ ሸኮ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ በተከሰተ ሌላ የመሬት ናዳ የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ‼️
በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ በተከሰተው መሬት ናዳ ወደ ሁለት ቀበሌዎች  የሚወስድ የትራንስፖርት እንስቃሴ መቋረጡም ተሰምቷል።
ሌላው በጅማ ዞን ጎማ ወረዳ
በጅማ ዞን ጎማ ወረዳ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ምክንት የመሬት መሰንጠቅ እና መንሸራተት እያገጠመ ይገኛል። በሌሎች አከባቢዎች ያጋጠመው ከባድ አደጋ ከመድረሱ በፊት በተለይ የመሬት መንሸራተት ያገጠመባቸው ቀበሌዎች ቀዳ ማዬ፣ ፉንጡሌ፣ በሻሻ እና ባርሶማ ነዋሪው ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት ተላልፏል።
#አዩዘሀበሻ
=======================
ትኩስ ያልተሰሙ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join አድርጉ+ለሌሎች ጋብዙ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


በ #ትግራይ ያለውን የረሃብ ቀውስ የሳተላይት ምሥሎች እና የዶክተር ምስክርነት አመለከተ‼️
በትግራይ ክልል አስከፊ የሆነ የሰብዓዊ ቀውስ እና የረሀብ አደጋ እየተባባሰ መምጣቱን የሳተላይት ምስሎች ማረጋገጡ ተዘገበ።

በክልሉ ከተከሰተው ደም አፋሳሽ ጦርነት በኋላ በድርቅ እና ሰብል ባለመሰብሰቡ ምክንያት የከፋ የሰብአዊ ቀውስ እየተከሰተ መሆኑ ቢቢሲ ዘግቧል።

ከክልሉ ዋና ከተማ መቀለ 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ቆሪር በተሰኘው ስፍራ አነስተኛ ሃይቅ የሚገኝ ሲሆን ሰው ሰራሽ ግድብም ተሰርቶለት ከግድቡ ጀርባ በታቆረው ውሃ በርካታ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ሲያደርግ ቆይቷል።

ይሁንና ቢቢሲ ከሳተላይት ምስሎች አረጋገጥኩ ብሎ እንደገለጸው በሰኔ 2016 ዓ.ም. ውሃ ማቆሪያው ደርቆ፤ የእርሻ ቦታውም ተራቁቶ ይታያል።
=======================
ትኩስ ያልተሰሙ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join አድርጉ+ለሌሎች ጋብዙ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


በ8% ብቻ ቅድመ ክፍያ የቤት ባለቤት ይሁኑ

ከ ቦሌ ኤርፖርት በቅርብ ርቀት በሚገኘው "ለቡ መብራት ሃይል" 65,395 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ዘመናዊ መንደር እየገነባን እንደሆነ ሰምተዋል?

*ለኢንቨስትመንት ቢሉ ለመኖሪያ

69 ካሬ  ባለ አንድ መኝታ
99 ካሬ ባለ ሁለት መኝታ
139 ካሬ ባለ ሶስት መኝታ

ለየት ባለ የቤት ዲዛይን

በሶስት አመት 50% ብቻ በመክፈል 50% ብድር አመቻችተናል

*ከ4,500 በላይ አባወራ በሚኖርበት በዚህ ዘመናዊ መንደር ልነግድ ካሉን ደሞ ከ39 ካሬ ጀምሮ እስከ 965 ካሬ ድረስ የንግድ ሱቆችን በመሸጥ ላይ ነን

ማስታወሻ ከ4% ጀምሮ በመክፈል መመዝገብ ይችላሉ

እያለቀ ነው አሁኑኑ ይደውሉልን
0937764111


በትግራይ ክልል የወንጀል ድርጊት በ68 በመቶ መጨመሩ ተገለፀ‼️
በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ እየተፈጸሙ ያሉ ህገወጥ ድርጊቶችና የወንጀል ተግባራት ከባለፈው ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነጻጸሩ በ68 በመቶ መጨመራቸው ተገልጿል፡፡
የመቀሌ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ በሪፖርቱ እንዳስታወቀው በዚህ ዓመት የተፈጸሙ ወንጀሎች ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸሩ በአንድ ሺህ ስምንት መቶ አርባ አንድ አሃዝ ብልጫ አሳይተዋል፡፡
የቢሮ ምክትል ሃላፊ  ኢንስፔክተር ገብረጨርቆስ ገ/መስቀል  ባለፈው ዓመት በከተማዋ የተፈጸሙ የወንጀል ድርጊቶች አሃዝ 2 ሺህ 8 መቶ 95 የነበረ ሲሆን በተያዘው ዓመት ግን ወደ 4 ሺህ 7 መቶ 35 ማሻቀቡን ነው በማብራሪያቸው የጠቆሙት፡፡
የከተማዋ ከንቲባ ይትባረክ አምሃ በበኩላቸው አሁን ላይ በከተማዋ ከሚታየው የሰላምና ጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ  ከፍተኛ በጀት በመመደብ የህግ ማስከበር ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን በመግለጽ ይህ ግን ሊሳካ የሚችለው የህዝቡ ድጋፍ ሲታከልበት ነው ብለዋል፡፡
ከድህረ ጦርነት ማግስት ግድያ፣ እገታና መሰል ወንጀሎች የተበራከቱበት የትግራይ ክልል ከፍተኛ በተባለ የሰላም እጦት ውስጥ እንዳለ የሚታወቅ ነው፡፡
ከሰሞኑም የክልሉ መንግስት ባወጣው መግለጫ እየተተገበሩ ያሉ የህግ ማስከበር ተግባራትን ፖለቲካዊ አውድ ለመስጠት የሚሞክሩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሲል ማስጠንቀቁ የሚታወስ ነው፡፡
#አዲስማለዳ
=======================
ትኩስ ያልተሰሙ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join አድርጉ+ለሌሎች ጋብዙ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


Ads❗❗
ወዴት ሄደው መስራት ይፈልጋሉ ?
ወደ ተለያዩ ውጭ ሀገራት በክሬዲት ሄደው መስራት እንደሚችሉ ያውቃሉ❓❓
ፍላጎትዎን ለማሳካት እና ዕቅድዎን ለመተግበር ቁርጠኛ ከሆኑ እኛ ጋ ይምጡ! ስኬትዎን እናስቀድማለን!

ለበለጠ መረጃ
☎️ 0908396710
☎️ 0991945085


በህይወት መኖሩን ለማረጋገጥ ተማሪዎችን ከነ መምህራቸው ያገተው ሰው‼️
ባቡራም ብሂል የተባለው ህንዳዊ የ40 ዓመት ጎልማሳ ራጃስታን በተሰኘችው ግዛት የሚኖር ሰው ነው፡፡

የግዛቲቱ አስተዳዳሪዎች ይህንን ሰው መሞቱን የሚያትት ማስረጃ ለቤተሰቦቹ ይልካሉ፡፡ በህይወት እያለ መሞቱን የሚያስረዳ ማስረጃ የደረሰው ይህ ሰው አለመሞቱን ለማሳየት ወደ ተቋሞ ቢሄድም የሚሰማው ያጣል፡፡

መንግስት ለግለሰቡ የሞት ማስረጃ ከሰጠ በኋላ ንብረቶቹ ወደ ሌላ ሰው ሊያስተላልፍ እንደሚችል የሰጋው ባቡራም በህይወት መኖሩን ለማሳየት መላ ይዘይዳል፡፡

ይህ ግለሰብም ባሳለፍነው ሳምንት ቢላዋ እና ቤንዚን ነዳጅ በመያዝ ባቅራቢያው ወዳለ አንደኛ ትምህርት ቤት ያመራል፡፡
ትምህርት ቤቱ ውስጥ ከገባ በኋላም በትምህርት ለይ ወደ ነበሩ አንድ ክፍል ድንገት በመግባት ተማሪዎቹን ከነ መምህራኑ ያግታል፡፡

ተማሪዎች ከነ መምህራቸው ባልታወቀ ሰው መታገታቸውን ጥቆማ የደረሳቸው ፖሊሶችም ወደ ስፍራው ያመራሉ፡፡
በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ይህ በህይወት የለም የተባለው በመጨረሻም ድርጊቱን የፈጸመው አለመሞቱን ለማሳየት በሚል እንደሆነ ይናገራል፡፡

በመጨረሻም ሞቷል በሚል በስህተት ተመዝግቦ የነበረው ሰው በህይወት መኖሩን አረጋግጧል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡፡፡
ይሁንና ግለሰቡ ለፈጸመው ወንጀል መቀጣቱ እንደማይቀር በፖሊስ ተነግሮታል ተብሏል፡፡
#alain #Ayuzehabesha
=======================
ትኩስ ያልተሰሙ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join አድርጉ+ለሌሎች ጋብዙ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s

18 last posts shown.