ከኤጀንሲው ሰራተኞች ጋር በጋራ በሚሰሩ ህገወጥ ደላሎች ምክንያት አገልግሎት ፈላጊው ህዝብ አሁንም እየተንገላታ ነው ተባለ‼️
በርካታ የህዝብ ቅሬታ ከሚቀርብባቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች አንዱ በሆነው፤ በኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ኤጀንሲ በህገወጥ ደላላ ብር ተበላን የሚሉ ዜጎች አቤቱታን እያቀረቡ ይገኛል ፡፡
የአስቸኳይ ፓስፖርት ላልተወሠነ ጊዜ አገልግሎት መስጠት አቁሞ የነበረ መሆኑን ተከትሎ ህገወጥ ደላሎች ከውስጥ ሠው እንዳላቸው በማሳመን እና ተጨማሪ ክፍያን ጭምር በማስከፈል የአገልግሎት ፈላጊውን ህብረተሠብ ብር በመብላት ላይ እንደሚገኙ ዜጎች ተናግረዋል።
እነዚህ ደላሎች ህገወጥ ስራቸውን በመስሪያ ቤቱ አካባቢ ሆነው መስራታቸው ህዝብን የበለጠ እንዲታለል አድርጎታል ይላሉ ቅሬታ አቅራቢዎች፡፡
የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ማስተዋል ገዳ፤ ህብረተሠቡ በዋነኝነት እየታለለ ያለው ፖስፖርቱን ለማግኘት ካለው ፍላጎት አንፃር የሚባለውን በማመኑ ነው ይላሉ፡፡
ህገወጥ ስራ ከሚሰሩ ደላሎች ጋር በጋራ የሚሠሩ ሰራተኞች እንዳሉ ደርሰንበት ለህግ ተላልፈው እንዲሰጡ አድርገናልም ብለዋል።
እነዚህ ህገወጥ ደላሎች በአብዛኛው ኢንተርኔት ቤት ያላቸው ናቸው የሚሉት ዳይሬክተሯ፤ እነሱን የማገድ ስልጣኑ የለንም ብለዋል።
ከመስሪያ ቤታችን ጋር የሚሠሩትን እና ህገወጥ ሰራተኞችን በህብረተሰብ ጥቆማ እንዲሁም በምርመራ በህግ አግባብ እንዲቀጡ መስሪያ ቤቱ ሀላፊነቱን እየተወጣ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
#Ethiofm
=======================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s