ሰዓት ጊዜን ያሳያል፣ ጊዜ ደግሞ የሰውን ማንነት!
መንደርተኝነትን ነፍሳችን አብዝታ ትፀየፋለች። የትግላችን አልፋና ኦሜጋም ከአማራነት ስንዝር ዝቅ ሊል እንደማይችል ብዕራችንን ስናነሳ ለእራሳችን የገባነው ቃልኪዳን ነበር።
የአማራ መገፋትና መሳደድ በጉራፈርዳ ጅማሮውን አድርጎ እያለ፣ በወለጋ "ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም" ያለችው ነፍስ ያላወቀች ህጻንን የትግል ቃልኪዳናችንን አድርገን ተነስተን፣ እኛ "ከመንደሬ ውጭ እንጃልህ" ወደሚል አቋም ልንከረበት ፈፅሞ አይቻለንም።
ይህንን እያልን ያለነው… ትናንት የአማራ ብሄርተኝነት እንዲያብብ ብዙ የሰሩ ወንድሞቻችንን ዛሬ በነበሩበት ቦታ ስላጣናቸው ብሎም የመንደርተኝነት ባንዲራ አንጋች ሆነው በማየታችን ነው። መንደርተኝነት ከብአዴናዊ አስተሳሰብም በእጅጉ ያነሰ የድንኮች መገለጫ ነው - ብአዴን በግልፅ "ከክልሉ ውጭ ያለ አማራ አይመለከተኝም" ይላል፤ መንደርተኝነት ደግሞ ከዚህም ያነሰና የከፋ ብአዴናዊነትና የአንካሶች መገለጫ ነው።
ይህን የሰንካሎች አስተሳሰብ ትናንት በአያሌው መንበርና ኃይለየሱስ አዳሙ ብቅ ብሎ እራሳቸውን ይዟቸው ከስሟል። ዛሬ ደግሞ የአያሌውን ቆብ ያጠለቁ፣ እሱን የበላ ቅጫም እኔንም ካልበላኝ ባዮች፣ የኃይለየሱስን ቡትቶ አስፍቼ ካለበስኩ የሚሉ መንደሬዎች ወደ አደባባይ ብቅ ብቅ ብለዋል።
በዚህ ሂደት ትናንት ያከበርናቸው አለፍ ሲልም ብዙ ነገሮችን አብረን የሰራን ወንድሞቻችን ሳይቀር እነሱም ቆቡን አጥልቀው፣ ቡትቶውን አገልድመው ስላየን በእጅጉ ህመም ሆኖብናል። ትናንት እነዛን ከጠላናቸውም በላይ የእነዚህ የጊዜ ጉዶች በእጅጉ ቀፈውናል። የጊዜ ጉዳይ ሆነና ዛሬ ነግቶባቸው ተጋልጠዋል፤ ነገ ደግሞ ይከስማሉ።
ሃሳብህ ተቀባይነት ያጣ ሲመስልህ "ከአያሌው ካልወለድኩ" በሚል መገልገል ከጀመርክ ድሮውንም ስህተቱ የማይገባህን ቦታ የሰጠንህ የእኛ ነበር። አይተናቸው አይተናቸው "እንዲህ ያደረጋቸው ጊዜያዊ እልህ ወይም ኢጎ ይሆናል" ከሚል አረዳድ ይልቅ ድብቅ ማንነታቸው ተጋለጠ ወደሚል ድምዳሜ ዛሬ ላይ ደርሰናል። በትግሉ ሜዳ ያሉ ወንድሞቻችን ወደ አንድነት እንዳይመጡ፣ መሃል ለመቆም እየሞከሩ ያሉ ደንቀራ ብዕረኞችና ምላሰኞችን ገሸሽ ማድረግ ከታጋዮችም ሆነ ከሰፊው ወገናችን ለነገ የማይባል የውስጥ ስራ ነው።
ለምንወደው ወገናችን ዛሬም የምንለው እንኳን እንደኛ እንቶ ፈንቶው ሲሞነጫጭር ለሚውል ብዕርተኛ ወይም ምላሰኛ ይቅርና ነፍጥ ያነሳ የትግል ሜዳን ጀግናንም ቢሆን… ግለሰቦች ላይ የተንጠለጠለ የትግል ግብ ሊኖረን አይገባም። ግለሰቦች እንደ አብኖች ሊንሸራተቱ ወይም ሊለዮን ይችላሉ ነገር ግን ትግሉን የትግሉ ቃልኪዳን ላይ ያመረኮዘ ኃይል እና ከትግሉ ዓላማ ላይ አይኑን የማይነቅል ትውልድ መሆን አለብን። የመንደሬን እንጉርጉሮ ስለሰማሁ ልበ-ተላላ የምሆን ከሆነ ገና አልገባኝም፤ ልክ አይደለሁም። ባህርዳር ዊክሊክስን የምታምኑት ለትግሉ ቃልኪዳን እስከታመነችና ትግሉን እስካገለገለች ድረስ ብቻ ነው፤ በአቋም ሸርተት ስንል አይናችሁን ለአፈር ማለት ከወገናችን የሚጠበቅ ነው። ለሌላውም ይህ እንደ አቋም ሊፈፀም የግድ ይላል።