ከአማራ ፋኖ በጎጃም ከተላለፈ መልዕክትና መመሪያ
የአማራ ፋኖ በጎጃም ም/ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው የአደረጃጀቱን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ካስተላለፉት መልዕክት ውስጥ የሚከተለውን አንኳር ነጥብ ለአፅንዖት አጋርተናል።
፭
መውጫ መልክት:-
የአማራ ፋኖ በጎጃም ከታህሳስ 2017 ዓ/ም ጀምሮ ባወጣው አዲሱ የፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር መመሪያ መሰረት ሙሉ የሰው ሀይሉን አሟልቶ ወደ ስራ እንደጀመረ ይታወቃል። የአማራ ፋኖ በጎጃም የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር መመሪያ የድርጅት ሀብትና ንብረት ተቋማዊ አሰራሩንና መርሁን በጠበቀ መልኩ ግልፀነት እና ተጠያቂነት በማስፈን እና ድርጅቱ ስም የሚሰበሰብ ማንኛውም ሀብት እና ንብረት በድርጅቱ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር መምሪያ እንዲሁም በስሩ በተቋቋመው የገቢ አስባሰብ ኮሚቴና በህጋዊ መንገድ ወክልና በሰጣቸው አስተባባሪዎች በኩል ብቻ እንዲተዳደር የአፋጎ ፍይናንስና አስተዳደር መመሪያ ይደነግጋል።
በመሆኑም የፋይናንሱን ስርዓት ግልጽነትና ተጠያቂነት በሰፈነበት መንገድ መምራት የብዙ ችግሮች ምንጭ ማድረቅም በመሆኑ ለሁሉም ክ/ጦሮች በመሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴና በመምሪያው በተሰጣችሁ ትዕዛዝ መሰረት ክ/ጦሩ ኬላን ተቆጣጥሮ በጥብቅ ዲስፕሊን በድርጅታችን የቀረጽ መመሪያ መሰረት እንዲተዳደር እያሳሰብኩ ይህን መመሪያ ተግባራዊ በማያደርግ ማንኛውም አካል ላይ አስተዳደራዊና ተገቢ እርምጃ የምንወስድ መሆናችንን እገልጻለሁ።
በተጨመሪም አፋጎ በአወጣው አዲሱ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር መምሪያ መሰረት ማንኛውም ከአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ ላሉ የትግሉ ደጋፊወች ከዚህ ቀደም ለትግሉ ስታደርጉት የነበረውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አፋጎ ትልክ አክብሮትና እውቅና እየሰጠ በቀጣይም ትግሉ ከመቸውም ጊዜ በላይ የእናንተን ድጋፍ የሚጠይቅበት ደረጃ ላይ በመድረሱና ፋይናንስ የትግሉ የጀርባ አጥንት መሆኑን በመረዳት የምታደርጉትን ማንኛውንም ድጋፍ በድርጅቱ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር በኩል ብቻ ድጋፋ እንድታደርጉ እየገለፅን ከአፋጎ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደርና በስሩ ከተቋቋመው የገቢ አስባሰብ ኮሚቴ ውጭ በየትኛውም መንገድ የሚደረግ ድጋፍ ካለ ድጋፍ ለድርጅቱ እንዳልተሰጠ የሚቆጠርና የተላከው ድጋፍ ለትግሉ እንቅፍት የሚፈጥርና ማእከላዊነትን በማላላት ለችግሮች መፈጠር ምክንያት ይሆናል።
ከዚህ በኋላ ማነኛውም የአፋጎ ደጋፊ፣ አባልና አመራር ከድርጅቱ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር እውቅና ውጭ በየትኛውም መንገድ ገንዘብ መሰብሰብ በጥብቅ የተከለከለ በመሆኑ በየትኛውም አለም የምትገኙ የአማራ ህዝብ ትግል ደጋፊዎች የምታደርጉት ድጋፍ በአፋጎ ፋይናንስና ንበረት አስተዳደር መመሪያና በገቢ አስባሰብ ኮሚቴው በኩል ብቻ መሆኑን እየገለፅን ለምታደርጉት አማራዊ የህልውና ትግል ድጋፋ እንደ አፋጎም በትግል ታሪካችን ትልቅ ክብር የምንሰጠው ይሆናል።
በተጨማሪም አፋጎ ከወታደራዊ አቅም፣ ከታክቲክና፣ ከአደረጃጀት አኳያ የአደረጃጀት ሪፎርሞችና የወታደራዊ መመሪያን እየከለሰ ሲሆን ለሚደረጉ ማንኛውም ለውጦች ሰራዊታችን ዝግጁ ሁኖ እንዲጠብቅ አሳስባለሁ።
መላው የአማራ ፋኖ በጎጃም ሰራዊታችን፤ የትግሉ ደጋፊዎችና የአማራ ህዝብ እንኳን ለአንደኛ ዓመት የድማማ በዓላችን አደረሳችሁ!!
▪︎ አዲስ ትውልድ፤ አዲስ አስተሳሰብ፤ አዲስ ተስፋ፤
▪︎ ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ