የቃየል ሚስት ነገር
----◉----
ከበርናባስ በቀለ
ትራንስፖርት ውስጥ ነኝ፤ መኪናዋ 5Lነች። የምታውቋት ትንሽዬ መኪና በሚገራርሙ ጨዋታ አዋቂ ወጣቶች ወግ ደምቃለች። ሾፌሩ ወደ ፊት ሲነዳ ወጣቱ ረጅም ርቀት የኋሊት ኼዶ በአንድ ወሳኝ ጉዳይ እየመከረ ነው። ደግሞ ወጣቶቹ ሁለት ቡድን ሆነዋል፤ የፊት ወንበርና የኋላ! ከፊት ወንበር፦ "ቃየል ሚስት ያገኘው ከየት ነው?" አንደኛው ከኋላ ቀበል አደረገና፦ "ሔዋን የወለደችው መንትዮችን ነበርና ቃየል ያገባው የአቤል መንትያ ሆና የተወለደችውን ልጅ ነው። እንደውም ቃልየና አቤል መጀመሪያ የተጣሉት እኮ በችኮቹ ነበር፤"
ከኋላ ወንበር ያለው ጎረምሳ፦ "እንዴ! አንተ ቃየልና አቤል የተጣሉት በመስዋዕት አይደለም? ከፊት ወንበር ምላሽ ተሰነዘረ፦ "እርሱ (የመስዋዕቱ ነገር) እኮ immediate ኮዙ ነው፤ ግን ቁርሾው የቆየ ነው! የአቤል መንትያ ሆና የተወለደችው ሴት ልጅ በጣም ቆንጆ ነበረችና አዳም ቃየል እንዳይነካት አራርቆ ያስቀምጣቸዋል፤ ቃየል ግን እየኼደ ይረብሸ ነበር። በዚያ ከአቤል ጋር (በችኳ ምክንያት) ተጣሉ። ይገረምሃል ጸቡ ከባድ ነበር። እንግዲህ በዚያው ሰሞን ነው የመስዋዕቱ ነገር ተደርቦ ሲመጣ ቃየል ጓ ያለው!"
ከፊት ወንበሩ ቡድን አንደኛው ጎረምሳ በጣም ተገረመ። "የሚገርም ነገር ነው! መጽሐፍ ቅዱስን በዚህ መልኩ አይቼ አላውቅም። እውነትም የእግዚአብሔር ቃል ጥልቅ ነው!" አለ። ከዚህ በላይ ልሰማቸው ስላልቻልኩኝ የኋላ ወንበሩን ወጣት በድንቅ ትንታኔህ ተገረሜአለሁ! ግን ይህን ቃየልና አቤል የተጣሉበትን ምክንያት ከየት ነው ያነበብኸው? ከየትስ አየመጣኸው? አልሁት።
ልጁም፦ "ከትውፊት ነው ያነበብሁት Bro!" እኔም ትውፊቱን እንዴት አመንኸው? እርሱም ቀበል አደረገና፦ "ትውፊቱን የተረጎሙልንን አባቶች አምናቸዋለሁ።" እኔም፦ ከየት ነው የተረጎሙት? እርሱም፦ "ከቃሉ ነዋ።" እኔም ቀጥዬ፦ ጉዳዩን ከዘገበው የዘፍጥረት ጸሐፊ በላይ በሌሉበት ዘመን የተከሰተውን ታሪክ የተረጎሙ ሰዎችን ትርክት ስለምን አመንህ!? እርሱም፦ "ውይ! ይገርማል። እንደዚህ አስቤ አላውቅም። ያወራኸኝ ጥሩ ነገር ይመስላል"
ቅድም ላይ ተረቱን ለጓደኛው ሲያስረዳ "የእግዚአብሔር ቃል ጥልቅ ነው፤ እንደዚህ አስቤ አላውቅም" ያስባለው ይኸው ልጅ እኔ ደግሞ በተራዬ እርሱን ስጠይቀው እርሱም "ውይ! እንደዚህ አስቤ አላውቅም" ምን አይነት ትውልድ ነው? ቃሉን ትተው ከንቱ ተረታቸውን ለትውልዱ የሚግቱ ሰዎች ግን!😥
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊