🍂ተጨማሪ ጾም ነክ ህግጋቶች
🍃 በረመዷን ወቅት የሰለመ(እስልምናን የተቀበለ) ሠው ያመለጡትን የጾም ቀናት ቀዷ አያወጣም።ከፊቱ ያሉትን የረመዷን ቀናቶች ግን በጾም ያሳልፋል።
🍃በረመዷን ወቅት ከእስልምና የወጣ(ካፊር የሆነ-አሏህ ይጠብቀን) ተመልሶ ወደ እስልምና ከገባ በክህደት ዘመን ያመለጠውን ፆም ቀዷ ማውጣት ይኖርበታል(የመዛሂቦች ኺላፍ ሊኖር ይችላል)
🍃አንድ ሰው ከእስልምና ከወጣ(ከከፈረ) በኋላ ተመልሶ ሙስሊም ከሆነ ያመለጡትን ጾሞች ሁላ (ሶላትን ጨምሮ ) ቀዷ ያወጣል ወይስ አያወጣም በሚለው ላይ ሊቃውንቶች የሃሳብ ልዩነቶች ይታይባቸዋል። አብዛኛዎቹ የሃነፊያ፡ሻፊኢያ እና ሃናቢላ ኡለማኦች የጾሙን ቀዷ ያወጣል የሚል ብያኔ ሰጥተዋል።
🍃እድሜያቸው የገፋ አዛውንቶች በረመዷን ወቅት መብላት ይችላሉ።(ከቻልይ ሚስኪኖችን የሚያበሉ ወይም ዘመድ አዝማዶቻቸው የሚጾኑላቸው ይሆናል)
🍃አንድ ጾመኛ በረመዷን የመጀመሪያ ሌሊት ላይ ያሰባት ኒያ ለተቀሩት የጾም ቀናት ታብቃቃዋለች።ማለትም በአንድ ኒያ ሙሉውን ረመዷን መጾም ይችላል። በየጾሙ ኒያን ማደስ ተወዳጅ መሆኑ አይዘነጋም።
🍃ከረመዷን ውጪ ላሉ የሱና ጾሞች ከፈጅር በፊት መነየት መስፈርት አይደለም ። ጸሃይ ከወጣች በኋላ ሃሳቡን ቀይሮ ^ጾመኛ ነኝ ^ማለት ይችላል። ረሱላችን (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) በቤታቸው ምግብ በማይኖርበት ግዜ በቀኑ ክ/ግዜ ጾምን ይነይቱ ነበር።
🍃ምንም ማፍጠሪያ ያላገኘ ጾመኛ በልቡ መብላትን ይነይታል(ያስባል) እንጂ አንዳንድ ሰዎች እንደሚያደርጉት ጣቱን አይጥባ፡ምራቁንም አጠራቅሞ አይዋጥ (ኢብኑ ኡሰይሚን-ረሂመሁሏህ)
🍃ረሱላችን (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) በሚያፈጥሩበት ወቅት ተከታዩን ዚክር ይሉ ነበር፡
ذهب الظمأ وابتلت العروق وثبت الأجر إن شاء الله
ጥማት ተወገደ ፡ ጅማቶችም ረጠቡ። ምንዳም በአሏህ ፍቃድ ተረጋገጠች።
🍃ሌሊት ላይ ሱሁርን መብላት ግዴታ ያልሆነ ተወዳጅ ሱና ነው።ሱሁርን መብላት ለጾመኛው በረካ እንደሆነ ረሱላችን( ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) በሃዲሳቸው አስተምረውናል) ።
🍃ሱሁርን ወደ ሌሊት ማገባደጃ(ፈጅር) አረፋፍዶ መብላት ሱና ሲሆን አህለል ኪታቦችን የሚጻረር ተግባር ስለሆነ እጅግ ተወዳጅ ሱና ነው።
🍃አንዳንድ ኡለማኦች እንደሚሉት - እጃችን ላይ የሚጠጣ ውሃ ይዘን ሳለ አዛን ካለብን የያዝናትን መጠጣት እንችላለን😊።(ፈትህ ዚል ጀላሊ ወል ኢክራም)