#ቢያበሉኝ_ቢያጠጡኝ
ቢያበሉኝ ቢያጠጡኝ ፈትፍተዉ ቢያጎርሱኝ
ያሻኸዉን ዉሰድ ሁሉ የአንተ ነዉ ቢሉኝ
እኔስ እንደ ሥሟ የጣፈጠ አጣሁኝ
እኔስ እንደ ሥሟ የጣፈጠ አጣሁኝ /2/
አዝ...........
የእዚህ ዓለም ነገር ባዶ ሆኖብኛል
ዛሬ የበላሁት ነገ ይርበኛል
መራራው ሕይወቴ ጣፋጭ የሚሆነው
እመቤቴ ስሚኝ በአንቺ ጨዉነት ነዉ
አዛኝቷ ስሚኝ በአንቺ ጨዉነት ነው /2/
አዝ.......
አንቺ የሌለሽበት ማዕዴ ባዶ ነዉ
ሥምሽን ቃልጠራሁ ጣፋጭ መራራ ነዉ
በእጄ ከጨበጥኩት የመሶብ እንጀራ
ማርያም የሚለዉ ሥም ጣፋጭ ነዉ ሲበላ/2/
አዝ........
ተስፋ ያደረገ አንቺን በሕይወቱ
ስለሆንሽለት ነዉ ለተማሪ ራቱ
እኔም እልሻለሁ የኑሮ ጣዕሜ
ከሞት ወደ ሕይወት መሸጋገሪያዬ /2/
ቢያበሉኝ ቢያጠጡኝ ፈትፍተዉ ቢያጎርሱኝ
ያሻኸዉን ዉሰድ ሁሉ የአንተ ነዉ ቢሉኝ
እኔስ እንደ ሥሟ የጣፈጠ አጣሁኝ
እኔስ እንደ ሥሟ የጣፈጠ አጣሁኝ /2/
አዝ...........
የእዚህ ዓለም ነገር ባዶ ሆኖብኛል
ዛሬ የበላሁት ነገ ይርበኛል
መራራው ሕይወቴ ጣፋጭ የሚሆነው
እመቤቴ ስሚኝ በአንቺ ጨዉነት ነዉ
አዛኝቷ ስሚኝ በአንቺ ጨዉነት ነው /2/
አዝ.......
አንቺ የሌለሽበት ማዕዴ ባዶ ነዉ
ሥምሽን ቃልጠራሁ ጣፋጭ መራራ ነዉ
በእጄ ከጨበጥኩት የመሶብ እንጀራ
ማርያም የሚለዉ ሥም ጣፋጭ ነዉ ሲበላ/2/
አዝ........
ተስፋ ያደረገ አንቺን በሕይወቱ
ስለሆንሽለት ነዉ ለተማሪ ራቱ
እኔም እልሻለሁ የኑሮ ጣዕሜ
ከሞት ወደ ሕይወት መሸጋገሪያዬ /2/