የሚቆጣህ ጓደኛ ይኑርህ
የጓደኝነት ትልቁ ፈተና አንዱ ሌላውን መገስጽ መቻሉ ወይም አለመቻሉ ነው፡፡ ሁላችንም እለት ተእለት ኃጢአት እንሠራለን፤ ለራሳችን ሰበብ እየፈጠርን ኃጢአቱ እንዳልተከስተ በማስመሰል ኃጢአታችንንም ላለመመልከት አይናችንን እናውራለን:: በእንደዚህ አይነት ጊዜያት ለኃጢአታችን ዓይኖቻችንን የሚከፍቱ ጓደኞች ያስፈልጉናል።
ራስህን በጓደኛህ ቦታ አስቀምጠው:: የዚያን ሰው ዓይኖች ለመክፈት ፈቃደኛ ነህ? ያሉትን ሰበቦች ውሸት መሆናቸውን ልትነግረው ዝግጁ ነህ? የሰው ልጅ ስለ እርሱ መጥፎ ሲነገረው ቁስሉ እንደተነካ ይጮኻልና የጓደኛህን ቁጣ ለመጋፈጥ ተዘጋጅተሃል? ወይንስ በዝምታ ታልፈዋለህ?
ጓደኞቻችንን በምንመርጥበት ጊዜ፣ ከእኛ ጋር ሀቀኛ ለመሆን ፈቃደኛ የሆኑትን እና አስፈላጊ ሲሆንም ንዴታችንን ለመቋቋም የተዘጋጁትን መምረጥ አለብን፡፡ እንደዚህ ያለ ሐቀኝነት ከሌለ፣ ጓደኝነት ጥልቀት የለውምና ምንም ፋይዳ የለውም::
ለጓደኛህ ትችት መግለጽ ግዴታህ ቢሆን የጓደኛህን ክብር ዝቅ እንዳታደርግ ተጠንቀቅ:: የእርሱን መልካም ነገሮችንም ከወቀሳህ ጋር አብረህ ማንሳትህ ተግሣጽህን ያለስልሳል:: እናም ጓደኛህን የምትገስጸው ከቀናነት እንጂ ከክፋት አይሁን፤ ቃላቶችህም በፍቅር እንጂ በቁጣ አይሁኑ::
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
(ለነፍስህ ቤት ሥራላት በፍሉይ ዓለም የተተረጎመ ገጽ 236)