🌻 መዝሙረ ዳዊት ክፍል 8 🌻
🌻መዝሙር ፯
ንጉሥ ዳዊት በእርሱ ላይ ክፉ ምክር ይመክር ነበረውን የአኪጦፌልን ምክር ለውጣት እያለ ይጸልይ ስለነበር መልካሙ የኵሲ ምክር ደረሰው፡፡ ይህ መዝሙር 7 ዳዊት ልጁ አቤሴሎም ባሳደደው ጊዜ ከወይራ ስር ሆኖ የጸለየው መዝሙር ነው፡፡ እግዚአብሔር በአሕዛብ ይፈርድባቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ልብ ያሰበውን ኵላሊት ያጤሰውን መርምሮ ያውቃል፡፡ ቅን ልቡና ያላቸውን ሰዎች የሚያድናቸው እግዚአብሔር በእውነት ይረዳኛል፡፡ እግዚአብሔር ፈታሒ በጽድቅ ኰናኒ በርትዕ ነው፡፡ ኃያል ነው ታጋሽም ነው፡፡ አኪጦፌል ራሱ በመከረው ክፉ ምክር ጠፋ፡፡ ልዑል ለሚሆን ለእግዚአብሔር ምስጋና አቀርባለሁ፡፡
🌻መዝሙር ፰
ዳዊት ኢየሱስ ክርስቶስን ሕፃናት በሆሣዕና ሲያመሰግኑት ጊዜው ሳይደርስ ተገልጾለት እግዚኦ እግዚእነ ጥቀ ተሰብሐ ስምከ በኵሉ ምድር አለ፡፡ አቤቱ ከሕፃናት አንደበት ምስጋናን ተቀበልክ፡፡ ዲያብሎስ ለ5500 ዘመን የሰውን ልቡና እንደ ዙፋን ሰውነቱን እንደ ድንኳን ፍትወታት እኩያት ኃጣውእን እንደ አጥር እንደ ቅጥር አድርጎ ይገዛ ነበር፡፡ ጌታ ሰው ከሆነ በኋላ ግን እየወጣ ሄዷል፡፡
© በትረ ማርያም አበባው
🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።
🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።