ለብጦበት ከሰሎሞን በኋላ የተነሡ 28 ነገሥታትም አንድ አንድ ብር ለብጠውበት ይኖሩ ነበር። የኋላ ሰዎች ብሩን ለይሁዳ ሰጥተው በእንጨቱ ጌታን ሰቅለውታል። ከንግሥተ ሳባ በፊት ኢትዮጵያ በሕገ ልቡና እግዚአብሔርን ታመልክ ነበረ እንጂ በሕገ ኦሪት አትመራም ነበረ። ከእርሷ በኋላ ግን በሕገ ኦሪት የምትመራ ሆናለች። በሕገ ኦሪት ለመመራት መነሻዋ የሰሎሞን ልጅ ቀዳማዊ ምኒልክ ከእስራኤላውያን ጋር መምጣቱ ነው።
▶️፲፫. "ሰሎሞንም የእግዚአብሔር ታቦት የገባበት ስፍራ ቅዱስ ነውና ሚስቴ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤት አትቀመጥም ሲል የፈርዖንን ልጅ ከዳዊት ከተማ ወደ ሠራላት ቤት አወጣት" ይላል (2ኛ ዜና መዋ.8፥11)። ቤተመቅደሱ ሌላ የዳዊት ቤት ሌላ ሆኖ እያለ "የእግዚአብሔር ታቦት የገባበት ስፍራ ቅዱስ ነውና ሚስቴ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤት አትቀመጥም" ሲል አልገባኝም ቢብራራልኝ።
✔️መልስ፦ ቤተ መቅደስ ከዳዊት ከተማ አቅራቢያ ስለነበረ እንዲህ ብሏል። በቤተ መቅደሱ አካባቢ ሌላ አማኝ መኖር የለበትም ነበርና።
▶️፲፬. "የሳባም ንግሥት የሰሎሞንን ዝና በሰማች ጊዜ በግመሎች ላይ ሽቱና ብዙ ወርቅ የከበረም ዕንቍ አስጭና ከታላቅ ጓዝ ጋር ሰሎሞንን በኢየሩሳሌም በእንቆቅልሽ ትፈትነው ዘንድ መጣች" ይላል (2ኛ ዜና መዋ.9፥1)። በዋናነት በእንቆቅልሽ ልትፈትነው ነው ግን የመጣችው ወይስ ሌላ የፈለገችው ነገር ይኖር?
✔️መልስ፦ እንግዲህ በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጸው እንቆቆልሽ ልትጠይቀው እንደሄደች ነው። ሌላ የፈለገችው ነገር እንደነበረ የተገለጸ ነገር የለም።
▶️፲፭. 2ኛ ዜና መዋ.9፥4 "የብላቴኖቹንም አቀማመጥ፥ የሎሌዎቹንም አሠራር አለባበሳቸውንም፥ ጠጅ አሳላፊዎቹንም አለባበሳቸውንም በእግዚአብሔርም ቤት የሚያሳርገውን መሥዋዕት ባየች ጊዜ መንፈስ አልቀረላትም" ይላል። መንፈስ አልቀረላትም ሲል ምን ለማለት ነው? መንፈስ በዚህ ጊዜ ትርጉሙ ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ መንፈስ ስሜትን ያመለክታል። መንፈስ አልቀረላትም ማለት ከደስታ የተነሣ ደነገጠች፣ ተጨነቀች፣ ስሜቷ ተረበሸ ማለት ነው። የደስታ ጭንቀት ነው።
▶️፲፮. "የተርሴስ መርከቦች ወርቅና ብር የዝሆንም ጥርስ ዝንጀሮና ዝጕርጕር ወፍም ይዘው ይመጡ ነበር" ይላል (2ኛ ዜና መዋ.9፥21)። በወቅቱ ዝንጀሮ እንደ ስጦታ ይሰጥ ነበር ማለት ነው?
✔️መልስ፦ አዎ በወቅቱ እነዚህ ነገሮች እንደከበረ ስጦታ ይታዩ ነበር።
▶️፲፯. "አባትህ ቀንበር አክብዶብን ነበር። አሁንም አንተ ጽኑዉን የአባትህን አገዛዝ በላያችንም የጫነውን የከበደውን ቀንበር አቅልልልን እኛም እንገዛልሃለን ብለው ተናገሩት" ይላል (2ኛ ዜና መዋ.10፥4)። አባቱ ሰሎሞን በጥበብ እስራኤልን እንዳላስተዳደረ ሕዝቡ ለምን እንዲህ አሉ በእውኑ ተጨቁነው ነበር?
✔️መልስ፦ ሰሎሞን በጥበብ ሕዝቡን እንዳስተዳደረ ቢገለጽም ሕዝቡ ደግሞ አገዛዝ እንደጸናባቸው ተሰምቷቸው ይህን ተናግረዋል።
▶️፲፰. "ንጉሡም ሰሎሞን የሚጠጣበት ዕቃ ዅሉ የወርቅ ነበረ። የሊባኖስ ዱር በተባለውም ቤቱ የነበረው ዕቃ ዅሉ ጥሩ ወርቅ ነበረ። በሰሎሞን ዘመን ብር ከቶ አይቈጠርም ነበር" ይላል (2ኛ ዜና መዋ.9፥20)። ብር ከቶ አይቈጠርም ነበር ሲባል ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ብር ከቶ አይቆጠርም ነበር ማለት ብዙ ወርቅ ስለነበረ ብር የተናቀ ነበር ለማለት የተነገረ አገላለጽ ነው።
▶️፲፱. "የሳባም ንግሥት የሰሎሞንን ዝና በሰማች ጊዜ በግመሎች ላይ ሽቱና ብዙ ወርቅ የከበረም ዕንቍ አስጭና ከታላቅ ጓዝ ጋራ ሰሎሞንን በኢየሩሳሌም በእንቆቅልሽ ትፈትነው ዘንድ መጣች። ወደ ሰሎሞንም በገባች ጊዜ በልቧ ያለውን ዅሉ አጫወተችው" ይላል (2ኛ ዜና መዋ.9፥1)። እንቆቅልሾቹ ምን መጽሐፍ ላይ ይገኛሉ?
✔️መልስ፦ እንቆቅልሹ ምን እንደነበረና የት መጽሐፍ ላይ እንደሚገኝ መጽሐፍ ቅዱሱ ስለማይገልጽ አላውቀውም።
▶️፳. "አኹንም አቤቱ አምላክ ሆይ ከኀይልኽ ታቦት ጋራ ወደ ዕረፍትኽ ተነሣ። አቤቱ አምላክ ሆይ ካህናትኽ ደኅንነትን ይልበሱ። ቅዱሳንኽም በደስታ ደስ ይበላቸው" ይላል (2ኛ ዜና መዋ.6፥41)። ወደ ዕረፍትኽ ተነሣ ሲባል ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ወደዕረፍትህ ተነሣ ማለት ረድኤትን ወደምታድልበት መቅደስ ግባ ማለት ነው። ይኸውም ረድኤትህን ስጥ ማለት ነው።
© በትረ ማርያም አበባው
🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።
🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።