💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 76 💙
▶️፩. ፪ኛ ዜና መዋ.፲፭ ÷፫ "እስራኤልም ብዙ ዘመን ያለእውነተኛ አምላክ ያለአስተማሪም ካህን ያለሕግም ይኖሩ ነበር" ይላል። አምላካቸው እግዚአብሔር ነው ካህንም ሌዋውያን ነበሩ ሕግም ሙሴ የሠራላቸው ሕግ ነበር። ታዲያ እንዴት ይህን ሊል ቻለ? ቢብራራልኝ።
✔️መልስ፦ እግዚአብሔር እውነተኛ አምላክ መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ትተው ጣዖትን ስላመለኩ ያለእውነተኛ አምላክ ይኖሩ ነበር ተብሏል። ከእግዚአብሔር የተላኩ የነቢያትን ድምፅ መስማት ሲገባቸው ነገር ግን የካህናተ ጣዖታትን ትምህርት ስለሰሙና በሕገ ጣዖት በመመራታቸው ያለ አስተማሪ ካህንና ያለ ሕግ ይኖሩ ነበር ተባሉ።
▶️፪. 2ኛ ዜና መዋ.12፥15 ላይ የተጠቆሙት የነቢዩ ሰማያ እና ባለራእዩ አዶ መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተካተተ ነው? ካልተካተተ ለምን?
✔️መልስ፦ የሰማያና የአዶ መጽሐፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እንደሆነ አልተገለጸም። ለምን አልተካተተም ለሚለው የተጻፈልን ጥቂቱ ብቻ ነው። ክርስቶስ እንኳ በዚህ ዓለም በሥጋ መጥቶ ያደረገው ሥራ ሁሉ ቢጻፍ ዓለም ባልበቃው ነበረ ተብሏል። ስለዚህ የድኅነትን መንገድ እንድናውቅባቸው ጥቂቶች ብቻ ተጽፈው ስለተላለፉልን ነው።
▶️፫. 2ኛ ዜና መዋ.11፥20 "የአቤሴሎምን ልጅ መዓካን" ይላል። 2ኛ ዜና መዋ.13፥2 ላይ ደግሞ "የገባዖን ሰው የኡርኤል ልጅ ነበረች" ይላል። ይህ እንዴት ይታረቃል?
✔️መልስ፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መካከል ተቃርኖ የለም። ነገር ግን አቆጣጠራቸው እንዴት እንደሆነ መረዳት ይገባል። ለምሳሌ ክርስቶስን የአብርሃም ልጅ ይለዋል። አብርሃም የብዙ አያቱ ሆኖ ሳለ ቀጥታ የአብርሃም ልጅ ተብሏል። መዓካንም የአቤሴሎም ልጅ እንደሆነች ከገለጸ በኋላ የኡርኤል ልጅ እንደሆነችም ገልጿል። ይህ በሁለት ምክንያት ይሆናል አንደኛው የአንድ ሰው ብዙ ስም ስለሚኖረው ሲሆን ሌላኛው በብዙ አያት ቅድመ አያት ወደኋላ ተቆጥሮም ሊሆን ይችላል። የመዓካ በየትኛው ተቅጥሮ እንዲህ እንዳለ ስላልተገለጸ አላወቅሁም። ተቃርኖ እንዳልሆነ ግን መረዳት ይገባል።
▶️፬. በይሁዳና በእስራኤል መካከል በተደረገው ጦርነት 500,000 ሰው ሞቷል። እንዲሁም በከፍተኛ ቁጥር ለጦርነት ይሰለፉ ነበር (2ኛ ዜና መዋ.13፥17)። እና ይህ ቁጥር ትክክል ነው ወይ? ስለ በዛብኝ ነው።
✔️መልስ፦ አዎ ትክክል ነው። በየዘመናቱ ሰው ይወለዳል ይባዛል። በተለያዩ ምክንያቶች ደግሞ ይሞታልና።
▶️፭. "የኢትዮጵያም ንጉሥ ዝሪ አንድ ሚልዮን ሠራዊት ሦስት መቶ ሠረገሎች ይዞ መጣባቸው" ይላል (2ኛ ዜና መዋ.14፥9)። ይህ በእኛ ታሪኮች ይታወቃል? በምንስ ምክንያት ነው ለውጊያ የመጣው?
✔️መልስ፦ መጽሐፍ ቅዱሱ ለውጊያ የመጣበትን ዝርዝር ምክንያት አይገልጽም። በእኛ ታሪክ ይታወቃል ወይ ለሚለው ይህን ጉዳይ የጻፈ ሌላ የታሪክ መጽሐፍ አላነበብኩም። ነገር ግን ከታላቁ መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ እስካለ ድረስ የታሪኩ እውነታ አጠያያቂ አይደለም።
▶️፮. ዳዊትና ሰሎሞን የማን ንጉሥ ነበሩ? የእስራኤል ወይስ የኢየሩሳሌም? ሮብዓምስ?
✔️መልስ፦ ዳዊትና ሰሎሞን እስራኤልና ይሁዳ ሳይለያዩ በፊት የነበሩ ስለሆኑ የሁለቱም ንጉሥ ነበሩ። በአሥራ ሁለቱም ነገደ እስራኤል ነግሠው ይኖሩ ነበር። በሮብዓም ጊዜ ግን መንግሥት ለሁለት ስለተከፈለ ሮብዓም የሁለቱ ነገድ (የይሁዳና የብንያም/የኢየሩሳሌም) ብቻ ንጉሥ ነበር።
▶️፯. "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ መንግሥትን ለዳዊትና ለልጆቹ በጨው ቃል ኪዳን ለዘለዓለም እንደ ሰጠ በውኑ አታውቁምን" ይላል (2ኛ ዜና መዋ.13፥5)። የጨው ቃል ኪዳን ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ ጨው በብሉይ ኪዳን የቃል ኪዳን ማረጋገጫ፣ የምግብ ማጣፈጫ ሆኖ ያገለግል ነበረ። ስለዚህ በጨው ኪዳን ማለቱ ኪዳኑ ሲደረግ ጨው እንደማረጋገጫ ይቀርብ ስለነበረ ስለዚያ የተነገረ ነው።
▶️፰. 2ኛ ዜና መዋ.12 ላይ ''በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከል በዘመናቸው ኹሉ ሰልፍ ነበር'' ይላል። ምዕራፍ 11 ላይ እግዚአብሔር በኢዮርብዓምና በእስራኤል ላይ ሰልፍ እንዳያደርጉ ከልክሎ አልነበረም ወይ? በልጁ አብያና በኢዮርብዓም መካከል እንዲኹ ነበር። ታድያ እግዚአብሔር መልሶ ፈቅዶ ነው?
✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ቢከለክልም ሕዝቡ ግን ዐማፂ ስለነበር እግዚአብሔርንም ሳይቀር ክዶ ጣዖትን እስከማምለክ ደረሰ። ስለዚህ እግዚአብሔር ፈቅዶ ሳይሆን ሰዎች ነጻ ፈቃዳቸውን ተጠቅመው በራሳቸው ሥልጣን ነው ከእግዚአብሔር ሕግና ሥርዓት አፈንግጠው እርስ በእርሳቸው ይገጥሙ የነበሩት።
▶️፱. 2ኛ ዜና መዋ.13 ላይ አብያ ኢዮርብዓምንና እስራኤልን አሸንፎ ወደከተማዎቻቸው ገብቶ ከነበረና እግዚአብሔር ኢዮርብዓምን ቀሥፎት ከነበረ እንዴት እስራኤልን ኹሉ ወደ መንግሥቱ አልመለሰም?
✔️መልስ፦ የተጣላ ኢዮርብዓም ብቻ ሳይሆን ሕዝቡ ሁሉ ነበረ። ስለዚህ ኢዮርብዓም ቢሞትም ሕዝቡ ስላልሞተ እስራኤልን ወደ ይሁዳ መንግሥት መመለስ አልቻለም።
▶️፲. 2ኛ ዜና መዋ.15 ላይ ሕዝቡ አምላካቸውን እግዚአብሔርን የማይፈልግ ታናሽም ታላቅም ወንድም ሴትም ይገደል ብለው ተማምለው ነበር። የአሳ እናት መዓካን ግን ለጣዖት ሰግዳ ነበር። ታድያ ተገድላለች ወይስ አሳ ያጠፋው ጣዖቱን ብቻ ነው?
✔️መልስ፦ እውነት ነው ለጣዖት የሰገደን ለመግደል ተማምለው ነበር። ነገር ግን በተማማሉት መሠረት የአሣን እናት ይግደሏት አይግደሏት የተገለጸ ነገር የለም። ጣዖቶቿን አጥፍተው ገድለዋት ይሆን ወይም ትተዋት ይሆን አልተገለጸምና።
▶️፲፩. 2ኛ ዜና መዋ.14፥9 የኢትዮጵያውያንን ታሪክ በዚህ መልኩ ማንበቤ አዲስ ሆኖብኛል። በታሪክ የማውቀው ኢትዮጵያውያን ፍትሕ አወቂ፣ ጽድቅን ጠባቂ በሚለው እንጂ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ይነካሉ ብዬ አላስብም ነበር። ሽንፈትን ጨምሮ። ታዲያ የሚነገረን መልካም እና የአሸናፊነት ታሪክ ሐሰት ነው ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ደግ ደጉን ታሪካችንን ብቻ ማንጸባረቅ ስለምንወድ እንጂ እስከ ቅርብ ጊዜ (እስካሁን) በሀገራችን ብዙ ግፎች ተደርገዋል። እየተደረጉም ይገኛሉ። በተጻፈው ታሪካችን እንኳ ብዙ ክፉ ታሪኮች አሉን። ነገር ግን በአንጻሩ ደግሞ ብዙ ምጡቅ ኅሊና የነበራቸው አስተዋይ ሰዎች፣ ቅዱሳን፣ ደጋግ ነገሥታት ነበሩን። ብዙ በጎ ታሪክም አለን። የሽንፈት ታሪክም አለን፣ የድል ታሪክም አለን። የሽንፈት ታሪካችን ከዚህ ከታላቁ መጽሐፍ ቅዱስ ተገልጿል። ተወዳጅ ሀገር እንደነበርንም በዚሁ መጽሐፍ ቅዱስ ተገልጿል። "የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር" እንዲል (አሞ.9፥7)።
▶️፲፪. 2ኛ ዜና መዋ.11፥21 "ሮብዓምም ከሚስቶቹና ከቁባቶቹ ሁሉ ይልቅ የአቤሴሎምን ልጅ መዓካን ወደደ። ዐሥራ ስምንትም ሚስቶችና ስድሳ ቁባቶች ነበሩት ሃያ ስምንት ወንዶችና ስድሳ ሴቶች ልጆችን ወለደ" ይላል። ብዙ ሚስት የሚያገቡት ሕዝበ እግዚአብሔርን ለመጨመር ነው? ከአንድ በላይ ማግባት ክልክል ካልሆነ አታመንዝር የሚለው ከሚስቶቹ እና ከቁባቶቹ አንጻር እንደት ይታያል?