💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 132 💙💙
▶️፩. ኢዮ.40፥19 የእግዚአብሔር የፍጥረቱ አውራ (ዋና) ሰው አይደለም ወይ? የፍጥረቱ መጀመሪያም ቢል ሰማይ ምድር አይደለም ወይ? እንዴት ብሔሞት ይላል?
✔️መልስ፦ የፍጥረቱ አውራ የሚለው አገላለጽ አንጻራዊ አገላለጽ ነው። አውራነቱም አንጻራዊ ነው። ከፍጡራን ሁሉ እግዚአብሔርን በመምሰል ሰው የላቀ ነው። ከዚህ ምዕራፍ ግን መሥፈርቱ እግዚአብሔርን መምሰል ሳይሆን ግዙፍነት ነው። ከተፈጠሩ ሥጋውያን ፍጥረታት ሁሉ በጣም ግዙፉ ብሔሞት ነው። የፍጥረቱ አውራ የተባለም በዚህ አግባብ ነው።
▶️፪. “ከሰሜን ወርቅ የሚመስል ጌጠኛ ብርሃን ይወጣል። በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያስፈራ ግርማ አለ” ይላል (ኢዮ.37፥22)። ከሰሜን የሚወጣው ጌጠኛ ብርሃን ማን ነው?
✔️መልስ፦ ከሰሜን የሚወጣ ደመና ብሩህ ነው። ጌጠኛ ብርሃን ያለው ደመናውን ነው። ደመናት በመጠናቸው ብርሃን አላቸውና። ከሰሜን የሚወጣ ጌጠኛ ብርሃን የተባለ ጸጋ እግዚአብሔር (ዕውቀት) ነው።
▶️፫. ኢዮ.41፥17 ትርጓሜው ዲያብሎስን ምግባረ ነቢያት ድል አይነሳውም ብሎ ይተረጉመዋል። ብዙዎች በምግባራቸው (ጸጋው ተጨምሮበት) ድል ነስተውት የለምን?
✔️መልስ፦ በብሉይ ኪዳን ምንም እንኳ ቅዱሳን ነቢያት ብዙ መልካም ሥራን ቢሠሩም ሲኦልን አስከፍተው ድኅነተ ነፍስን ማሰጠት አልቻሉም። ወኮነ ጽድቅነ ከመ ጸርቀ ትክቶ እንዲሉ ጽድቃቸው ለክብረ ነፍስ ለድኅነተ ነፍስ የማያበቃ ስለነበር መተርጉማን ዘመኑን አስበው ለዘመኑ ሰይጣንን ምግባረ ነቢያት ድል አልነሣውም ብለዋል። ክርስቶስ ተሰቅሎ በመስቀል ድል ካደረገው በኋላ በሐዲስ ኪዳን ግን ጻድቃን ድል የሚነሡት ሆነዋል። አይቴ ቀኖትከ ሞት ወአይቴ መዊኦትከ ብለው የሚሳለቁበትም ሆነዋል።
▶️፬. ኢዮ.42፥16 የልጅ ልጆቹ ለኢዮብ አራተኛ ትውልድ ናቸው እንዴ?
✔️መልስ፦ ከልጅ ልጅ በኋላ የሚወለዱትን ሁሉ የልጅ ልጅ እያለ መጥራት የተለመደ ስለሆነ እንጂ የልጅ ልጅ ለኢዮብ ሦስተኛ ነው። ለምሳሌ እግዚአብሔር ለአዳም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሀለሁ ሲለው በሦስተኛ ትውልድ አድንሀለሁ ለማለት አይደለም። ሦስትና ከዚያ በላይ ያለውን ትውልድ ሁሉ የልጅ ልጅ ብሎ ስለሚጠራው ነው እንጂ።
▶️፭. ኢዮ.42 ላይ የኢዮብ ሀብት በእጥፍ እንደተመለሰለትና አሥር ልጆች እንደተወለዱለት ይጠቅሳል። የኢዮብ የመጀመሪያ ሚስቱ የተቀሠፈችው መች ነው? ልጆችንስ እግዚአብሔር የቀድሞዎቹን በሕይወት አሰነሥቷቸው ወይስ ሌሎች 10 ልጆችን ወልዶ?
✔️መልስ፦ ልጆቹ የቀድሞዎችን አስነሥቷቸው ሳይሆን እንደ አዲስ የተወለዱ ሌሎች ልጆች ናቸው። የመጀመሪያ ሚስቱ ተቀሠፈች የሚል አላገኘሁም። መጨረሻዋ ምን እንደነበረ የሚገልጽ ነገር ከመጽሐፈ ኢዮብ አላገኘሁም።
▶️፮. "በውኑ ወደ በረዶው ቤተ መዛግብት ገብተሃልን? የበረዶውንስ ቅንጣት ቤተ መዛግብት አይተሃልን? ይኸውም ለመከራ ጊዜ ለሰልፍና ለጦርነት ቀን የጠበቅሁት ነው" ይላል (ኢዮ.38፥22-26)። የዚህ ንባብ ትርጓሜው ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ ይህን ቃል የተናገረው እግዚአብሔር ለኢዮብ ነው። መካነ በረድ (የበረዶን ቦታ) እንኳ የማታውቅ ሆነህ ሳለህ ለምን ብዙ ትናገራለህ ለማለት የተናገረው ነው። ለመከራ ጊዜ ለሰልፍና ለጦርነት ቀን የጠበቅሁት ነው ማለቱ በትዕቢተኞች በረዶ በማምጣት ስለሚቀጣበት ነው። እንደነፈርዖን ማለት ነው።
▶️፯. መጽሐፈ ኢዮብ ምዕራፍ 41 ሰለማን ነው የሚያወራው?
✔️መልስ፦ ከመጀመሪያው ጀምሮ እስከ መጨረሻው እግዚአብሔር ለኢዮብ የተናገረውን ቃል የያዘ ምዕራፍ ነው።
▶️፰. ኢዮ.42፥19 መጽሐፈ ኢዮብ በSyrriac ቋንቋ ነው የተጻፈ?
✔️መልስ፦ የመጀመሪያው መጽሐፈ ኢዮብ በምን ቋንቋ እንደተጻፈ ታሪካዊ ማስረጃ ማቅረብ አልቻልኩም። መጽሐፍ ቅዱሱም በዚህ ዙሪያ የገለጸው ነገር የለም።
▶️፱. "ሰዎች ሁሉ ተመልክተውታል። ሰውም ከሩቅ ያየዋል" ይላል (ኢዮ.36፥25)። ሰውም ከሩቅ ያየዋል ሲል ምን ለማለት ነው?
✔️መልስ፦ እግዚአብሔርን ሰዎች ሁሉ ተመልክተውታል መባሉ በዘፈቀደ ለሁሉ ስለተገለጠ ነው። ሰውም ከሩቅ ያየዋል መባሉ ከሩቅ ያለ አካል በግልጽ እንደማይታወቅ ሁሉ እግዚአብሔርም በባሕርይው እንደማይታወቅ ያመለክታል።
▶️፲. "በዚያን ጊዜ ተወልደኽ ነበርና የዕድሜኽም ቍጥር ብዙ ነውና። በእውነት አንተ ሳታውቅ አትቀርም" ይላል (ኢዮ.38፥21)። በእውነት አንተ ሳታውቅ አትቀርም ሲለው ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ይህ ፍና ተሳልቆ ነው። ስለዚህ በአሉታ ይተረጎማል። ትርጉሙም በዚያን ጊዜ አልተወለድክም ነበር። የዕድሜህም ቁጥር ትንሽ ነው። በእውነት አንተ ያንጊዜ የነበረውን አታውቅም ማለት ነው።
▶️፲፩. "እግዚአብሔር በድምፁ ድንቅኛ ያንጎደጉዳል። እኛም የማናስተውለውን ታላቅ ነገር ያደርጋል" ይላል (ኢዮ.37፥5)። በድምፁ ድንቅኛ ያንጎደጉዳል ሲባል ምን ለማለት ነው? እኛ የማናስተውለው ታላቅ ነገርስ ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ ማንጎድጎድ ማለት ከፍ አድርጎ ማሰማት ማለት ነው። ምሥጢሩ ከነጎድጓድ የተወሰደ ነው። ድንቅኛ ማለት በአስደናቂ ሁኔታ፣ በሚገርም ሁኔታ፣ በሚያስፈራ ሁኔታ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። እኛ የማናስተውለው ታላቅ ነገርም ይደረጋል ማለት እግዚአብሔር እኛ የማናውቃቸው ታላቅ ታላቅ ሥራዎችን ይሠራል ማለት ነው።
▶️፲፪. "ሰው ሁሉ ሥራውን ያውቅ ዘንድ የሰውን ሁሉ እጅ ያትማል" ይላል (ኢዮ.37፥7)። የሰውን ሁሉ እጅ ያትማል ሲል ምንን ለመግለጽ ነው?
✔️መልስ፦ የእግዚአብሔርን ከሃሊነት፣ መጋቢነትና ጠባቂነት ለመግለጽ ነው።
▶️፲፫. "አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ የእግዚአብሔርም ልጆች ሁሉ እልል ሲሉ መሠረቶቿ በምን ላይ ተተክለው ነበር?" ይላል (ኢዮ.38፥6-7)። አጥቢያ ኮከቦችና የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉ ምንድን ናቸው?
✔️መልስ፦ ከዚህ ላይ የአጥቢያ ኮከቦችም፣ የእግዚአብሔር ልጆችም የተባሉ ቅዱሳን መላእክት ናቸው።
▶️፲፬. ስለ ሰጎን ሲገልጽ "እግዚአብሔር ጥበብን ከእርሷ ከልክሏልና። ማስተዋልንም አልሰጣትምና" ይላል (ኢዮ.39፥17)። በእውኑ ስለ ሰጎን የተነገረ ቃል ነው ወይስ ምሳሌ ነው?
✔️መልስ፦ ቀጥታ ስለሰገኖ ተፈጥሮና አኗኗር የተነገረ ነው። ነገር ግን ለሚያስተውል ሰው ከሰገኖ ሕይወትም መማር ይቻላልና ተጽፏል።
© በትረ ማርያም አበባው
✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።
🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።