💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 157 💙
▶️፩. "ስለ ፍሬው ፋንታ የመላእክትን ምግብ ለሕዝብህ መገብኻቸው" ይላል (ጥበ.16፥20)። "የመላእክት ምግብ" ሲል ምን ማለት ነው? የመላእክት ምግባቸውስ ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ ይህ በሁለት ይተረጎማል። አንደኛው ተመልአከ አለቃ ሆነ ከሚለው ግሥ መላእክት ሲወጣ አለቆች ተብሎ ይተረጎማል። አለቆቹ እነሙሴ የተመገቡትን ምግብ እስራኤላውያን ሕዝቡ መመገባቸውን ያመለክታል። ሁለተኛው ለአከ ላከ ከሚለው መልእክተኞች ይወጣል። ይህ የእግዚአብሔር መልእክተኞች የሆኑ መላእክትን ያመለክታል። ሕዝቡ የመላእክትን ምግብ በሉ ማለት እንደ መላእክት አመሰገኑ ማለት ነው። የመላእክት ምግብ ያለው ምስጋናን ነው።
▶️፪. ጥበ.፲፯፥፱ ላይ "የሚያውከው ነገር ምንም ባያስፈራቸው የሚበርር ተሓዋሲ እንቅስቃሴ እና የእባቦች ጩኸት አባረራቸው" ይላል። ተሓዋሲ ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ ጥቃቅን ደማውያን ፍጥረታትን ተሐዋስያን ይላቸዋል። በእንግሊዘኛ Insects ከሚላቸው ጋር የተቀራረበ ትርጉም አለው።
▶️፫. ጥበ.16፥27 ላይ ፀሐይ ተብሎ የተገለጸው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው? ወይስ ሌላ ነው?
✔️መልስ፦ በምሥጢር ለክርስቶስ ይነገራል። ከሰማይ የወረደላቸውን መና እሳት አያቀልጠውም ነበር። በትንሽ ዋዕየ ፀሐይ ግን ቀልጦ ጠፋ ተብሏል። ፀሐየ ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ በቤተ መቅደስ ተቀምጦ የነበረው መና ቀልጦ ጠፍቷል። አማናዊው መና ክርስቶስ ተወልዷልና። እስመ ፀሐይኒ የኀሥሥ ይምጻእ ኀቤነ ያለው ይህን የበለጠ ያጎላዋል።
▶️፬. ጥበ.16፥17 ላይ "ዓለም የጻድቃን ረዳት ነው" ይላል። ዓለም የራሱ የሆኑትን እንጂ ከዓለም ያይደሉ ጻድቃንን ይወዳል እንዴ? ሲጀመር ዓለም ጻድቃንን የሚጠላቸው ሆኖ ሳለ እንዴት ይረዳቸዋል ይባላል? (ዮሐ.15፥19)።
✔️መልስ፦ በዚህ ጊዜ ጻድቃን ያላቸው እስራኤላውያንን ነው። ዓለም የተባሉትም ከዚሁ የተጠቀሱት እሳትና ውሃ ናቸው። እነዚህ እስራኤላውያንን ረዱ ማለት ነው። ይኸውም ውሃ ጠላቶቻቸውን እነፈርዖንን በማስጠም፣ እሳት ሌሊት እያበራ መንገድ በመምራት ረድቷቸዋልና ይህን ለመግለጽ ነው።
▶️፭. መና እንዴት ነው የእግዚአብሔር ሰማያዊ መልክዕ አርአያ የሚሆነው? ሲጀመር ከሰው ውጭ በእግዚአብሔር መልክዕ እና አርአያ የተፈጠረ ፍጥረት አለን? (ዘፍ.1፥26)።
✔️መልስ፦ ምሳሌ፣ አርአያ፣ መልክዕ የተባሉት አንጻራዊ አገላለጾች እንጂ ፍጹማዊ አይደሉም። ሰው እግዚአብሔርን ይመስላል ስንል መምሰሉ ሙሉ በሙሉ ሳይሆን በጥቂት ነው። ከሰማይ የወረደው መና የእግዚአብሔር መልክና አርአያ አለው መባሉ እስራኤላውያን ያንን በልተው ከረኀብ እንደዳኑ ወልደ እግዚአብሔርም ሰው ሆኖ ሥጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ ይላልና የዚህ ምሳሌ ነው። መመሳሰሉ መናው ረኀበ ሥጋን እንዳራቀ የክርስቶስ ሥጋና ደምም ከረኀበ ነፍስ ያድናልና።
▶️፮. ጥበ.18፥5 ላይ "ያለ ርኅራኄ በብዙ ውኃ አጠፋህ" ይላል። ያለ ርኅራኄ ሲል እንዴት ይተረጎማል?
✔️መልስ፦ ይህ የእግዚአብሔርን ፈታሒነት ይገልጻል። እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ጥፋቱ መጠን ልክ ይፈርድበታል። ያለ ርኅራኄ ማለት በፍርድ ጊዜ ፊት ሳያደላ፣ በደለኛውን ሳይምር እንደበደሉ አጠፋው ማለት ነው። በኋላም በምጽአት ጊዜ ኃጥኣንን ሑሩ እምኔየ ሲላቸው ፍርዱ ስለሆነ ራርቶ ወደ መንግሥተ ሰማያት ይመልሳቸዋል አንልም። በትክክል ፈራጅነቱን ለመግለጽ ያለ ርኅራኄ ተብሏል።
▶️፯. ጥበ.16፥22 እሳት እና በረድ ሳይጠፋፉ የነበሩት መቼ ነው?
✔️መልስ፦ እሳትና በረድ ሳይጠፋፉ የተባለው እግዚአብሔር በግብፃውያን ላይ መቅሠፍት ሲያመጣ በአንድ ወቅት እሳት፣ በረድ፣ ዝናም ቀላቅሎ አዝንሟልና ይህን ለመግለጽ ነው።
▶️፰. ጥበ.16፣4 ላይ "በእነዚህ ላይ ፍርድ ያለርህራሄ ይወርድ ዘንድ ግድ ነው" ይላል። በእስራኤላውያን ላይ ነው? በግብፃውያን ላይ ነው?
✔️መልስ፦ በግብፃውያን ላይ ነው።
▶️፱. ጥበ.16፣18 "የእሳት ነበልባል በዝንጉዎች ላይ የተላኩ እንስሳትን እንዳያቃጥል ለማዳን ሆነ" ይላል። ዝንጉዎች እና እንስሳት ተብለው የተገለፁት እነማንን ነው ቢብራራልኝ?
✔️መልስ፦ ከዚህ ላይ ዝንጉዎች የተባሉ ግብፃውያን ናቸው። እንስሳት የተባሉ እስራኤላውያን ናቸው። በዝንጉዎች ግብፃውያን የመጣው መከራ እስራኤላውያንን እንዳይጎዳ ማለት ነው።
▶️፲. ጥበ.፲፯፥፫ ላይ "የበደሉትን ዐስበው በውስጡ ብርሃን በሌለበት ቤት ውስጥ ከዝንጋዔ መጋረጃ በታች ተሰወሩ። እጅግም እየተደነቁ በድንጋጤ ቀለጡ። በምትሀትም ታወኩ" ይላል። ከዝንጋዔ መጋረጃ በታች ተሰወሩ እና በምትሐትም ታወኩ ሲል ምን ማለቱ ነው?
✔️መልስ፦ ከዝንጋኤ መጋረጃ በታች ተሠወሩ ማለት በዝንጋኤያቸው ምክንያት ጠፉ ማለት ነው። በምትሐትም ታወኩ ማለት ራሳቸው የግብፅ ጠንቋዮች ባሳዩዋቸው ምትሐት ታወኩ ማለት ነው።
© በትረ ማርያም አበባው
✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።
🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።