▶️፳፯. መክ.4፥9-10 ላይ "ድካማቸው መልካም ዋጋ አለውና አንድ ብቻ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል። ቢወድቁ አንዱ ሁለተኛውን ያነሣዋልና። አንዱ ብቻውን ሆኖ በወደቀ ጊዜ ግን የሚያነሣው ሁለተኛ የለውምና ወዮለት" ይላል። ይህ ስለ ባል እና ሚስት የተነገረ ነውን? ትርጉሙ ቢብራራ።
✔️መልስ፦ ይህ ስለማንኛውም አንድነት የተነገረ ነው። በብዙ ጉዳዮች ብቻን ከመሆን ሁለት መሆን የተሻለ ነው። አንዱ ቢደክም አንዱ ያበረታዋልና። ይህ ለትዳርም ይተረጎማል። ሴት ወይም ወንድ ብቻቸውን ከሚኖሩ ተጋብተው አንድ ላይ ቢኖሩ ይሻላል። ይህን ለመግለጽ ነው።
▶️፳፰. መክ.፭፥፳ ላይ "እግዚአብሔር በልቡ ደስታ ስለሚያደክመው እርሱ የሕይወቱን ዘመን ሁሉ እጅግ አያስብም" ይላል። እግዚአብሔር አድካሚ ነው እንዴ?
✔️መልስ፦ እግዚአብሔር በኃይሉ ክፉ ሰዎችን፣ አጋንንትን ያደክማል። ስለዚህ ክፉዎችን አጋንንትን የሚያደክም ስለሆነ አድካሚ ተብሎ ሊነገርለት ይችላል። ከዚህ የተጠቀሰው ግን እግዚአብሔር በደስታ ያደክመዋል ማለት በደስታ እስኪደክም (እስኪሸመግል) ያኖረዋል ማለት ነው።
© በትረ ማርያም አበባው
✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።
🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።