ስሙኝማ…
ልጅነትን ስሸኝ በሀሳብ አድጌ
ከብቸኝነት ጋር ልላቀቅ ፈልጌ
ትዳር ለመወጠን ካሰብኩኝ በኋላ
ያየሁት እሸት ሁል ሆነ 'ማይበላ
የሆነ ቀን ለታ
አንድ አለኸኝ ብላ
ቃል የገባች እንስት
አንድ አለሽኝ ብየ
ቃል የሰጠኋት ሴት
ከብዙ ሁካታ ከጨዋታ መሀል
ከእኔ አስበልጠህ
ሴት አትወድም አይደል?
ብላ ስትጠይቀኝ መሳቄን አቁሜ
በንዴት በግኜ ደግሞም ተገርሜ
"አትሳሳች ውዴ
ካንች እጥፍ ድርብ ውለታ የዋለች
ለእኔ ደስታ ብላ ደስታዋን የሸጠች
እኔ እንደምወድህ ውደደኝ ያላለች
ካንች በበለጠ
ፍፁም ምወዳት ገራሚ ሴት አለች"
ብየ ቃል ሳወጣ
ገደል ግባ ብላ ገፍታ ጥላኝ ሄደች
በዚህ ቃል ተናዳ ከፊቴ ላይ ሳጣት
ፍቅሯን አራግፌ ከልቤ አወጣኋት
ደግሞ ትናንትና
አንድ አለችኝ ያልኋት
የህይወት አጋሬ
"መውደድህ እንዴት ነው
የት ድረስ ነው ፍቅሬ?
አንዴ ቃል አውጣና
በል ንገረኝ ዛሬ"
ብላ ስትጠይቀኝ
በኔ ልብ አዋዋል በፍቅር አደራደር
ከመውደድ ዙፋኔ ከልኬት ማህደር
ቦታ አደላድየ ላሞግሳት ስጥር
የሚከተሉትን ቃላት ብወረውር
"ዚች አለም ስኖር ካገኘኋቸው ሴት
ደስታ ካቋደሱኝ ካለበሱኝ ሀሴት
ደረጃ ሰጠሁሽ በሁለተኛነት"
ብየ ስናገራት
ከእኔ የበለጠ የምትወዳት ካለች
ከርሷ ጋር አብረህ ኑር
ብላ ጥላኝ ሄደች
የምር ጉደኛ ነች😢
ይህን ስትናገር በፍቅር አኩርፋ
ለእርሷ ያለኝ ፍቅር ከእኔ በኖ ጠፋ
እናም
ነገ የማገኝሽ የትዳር አጋሬ
መኖርሽ የምሆን የምትሆኝ መኖሬ
ቀደም አስቢበት በይ ልንገርሽ ዛሬ
ከመንገስሽ በፊት ከልቤ ዙፋን ላይ
ሁለተኛነትሽን በይ አምነሽ ተቀበይ
ወይም
ብቻየን ወድቄ
ሳልቀምሰው ይቅር እንጂ
የትዳርን አለም
አንደኛነትንስ
ከእናቴ አስበልጬ
የምሰጠው የለም
✍ዝምተኛው ፀሀፊ
@belay_HI
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
ልጅነትን ስሸኝ በሀሳብ አድጌ
ከብቸኝነት ጋር ልላቀቅ ፈልጌ
ትዳር ለመወጠን ካሰብኩኝ በኋላ
ያየሁት እሸት ሁል ሆነ 'ማይበላ
የሆነ ቀን ለታ
አንድ አለኸኝ ብላ
ቃል የገባች እንስት
አንድ አለሽኝ ብየ
ቃል የሰጠኋት ሴት
ከብዙ ሁካታ ከጨዋታ መሀል
ከእኔ አስበልጠህ
ሴት አትወድም አይደል?
ብላ ስትጠይቀኝ መሳቄን አቁሜ
በንዴት በግኜ ደግሞም ተገርሜ
"አትሳሳች ውዴ
ካንች እጥፍ ድርብ ውለታ የዋለች
ለእኔ ደስታ ብላ ደስታዋን የሸጠች
እኔ እንደምወድህ ውደደኝ ያላለች
ካንች በበለጠ
ፍፁም ምወዳት ገራሚ ሴት አለች"
ብየ ቃል ሳወጣ
ገደል ግባ ብላ ገፍታ ጥላኝ ሄደች
በዚህ ቃል ተናዳ ከፊቴ ላይ ሳጣት
ፍቅሯን አራግፌ ከልቤ አወጣኋት
ደግሞ ትናንትና
አንድ አለችኝ ያልኋት
የህይወት አጋሬ
"መውደድህ እንዴት ነው
የት ድረስ ነው ፍቅሬ?
አንዴ ቃል አውጣና
በል ንገረኝ ዛሬ"
ብላ ስትጠይቀኝ
በኔ ልብ አዋዋል በፍቅር አደራደር
ከመውደድ ዙፋኔ ከልኬት ማህደር
ቦታ አደላድየ ላሞግሳት ስጥር
የሚከተሉትን ቃላት ብወረውር
"ዚች አለም ስኖር ካገኘኋቸው ሴት
ደስታ ካቋደሱኝ ካለበሱኝ ሀሴት
ደረጃ ሰጠሁሽ በሁለተኛነት"
ብየ ስናገራት
ከእኔ የበለጠ የምትወዳት ካለች
ከርሷ ጋር አብረህ ኑር
ብላ ጥላኝ ሄደች
የምር ጉደኛ ነች😢
ይህን ስትናገር በፍቅር አኩርፋ
ለእርሷ ያለኝ ፍቅር ከእኔ በኖ ጠፋ
እናም
ነገ የማገኝሽ የትዳር አጋሬ
መኖርሽ የምሆን የምትሆኝ መኖሬ
ቀደም አስቢበት በይ ልንገርሽ ዛሬ
ከመንገስሽ በፊት ከልቤ ዙፋን ላይ
ሁለተኛነትሽን በይ አምነሽ ተቀበይ
ወይም
ብቻየን ወድቄ
ሳልቀምሰው ይቅር እንጂ
የትዳርን አለም
አንደኛነትንስ
ከእናቴ አስበልጬ
የምሰጠው የለም
✍ዝምተኛው ፀሀፊ
@belay_HI
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19