እንታረቅ 🤝
በቀጠርሽኝ ሰዓት
መድረሱ ተስኖኝ ጊዜሽን ስበላሽ
ጊዜኮ ወርቅ ነው ለምን ትይኛለሽ?
ሰዓትሽን ገድፌ
ቀንሽን ሸራርፌ
ቃሌንም አጥፌ
አውቃለሁ የለሁም
በቀጠርሽኝ ስዓት
ተገርፈሻል አዎ
በመጠበቅ ቅጣት
ግን
በፍቅር ተሸንፎ ወድቆ ለሚታገል
ጊዜ ይቅርና ህይወት ይሰጥ አደል
እያልኩኝ በትቢት ቀንሽን ሳቃጥል
ሰዓትሽን ነጥቄ ቀንሽን ስገድል
"የጊዜን ምንነት ነግሬህ ካልገባህ
ያፈቀረን ሰዓት አይተህ ካልተረዳህ
በጊዜ ልርገምህ ግዜ ይፋረድህ"
ብለሽኝ ስትሄጂ
ያንች ስለት ሰምሮ ግዜ ተፋርዶኛል
የነበረኝ ሁሉ
በደቂቃ ግድፈት ከእጄ ሸሽቶኛል
ዛሬ
በግዜ ስቀጣ ተረዳሁት ጊዜን
ይቅር በይኝና ተቀበይኝ ቃሌን
በደሌን አየሁት
ሁሉን ተቀምቼ ስገረፍ በሲቃ
ማሪያም ጣትሽን ስጭኝ🤙
እንታረቅ በቃ
እንታረቅ🤝
እንታረቅ🤝
🤙🤙🤙🫴🫴🫴🤝🤝🤝
✍ዝምተኛው ፀሀፊ
@belay_HI
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
በቀጠርሽኝ ሰዓት
መድረሱ ተስኖኝ ጊዜሽን ስበላሽ
ጊዜኮ ወርቅ ነው ለምን ትይኛለሽ?
ሰዓትሽን ገድፌ
ቀንሽን ሸራርፌ
ቃሌንም አጥፌ
አውቃለሁ የለሁም
በቀጠርሽኝ ስዓት
ተገርፈሻል አዎ
በመጠበቅ ቅጣት
ግን
በፍቅር ተሸንፎ ወድቆ ለሚታገል
ጊዜ ይቅርና ህይወት ይሰጥ አደል
እያልኩኝ በትቢት ቀንሽን ሳቃጥል
ሰዓትሽን ነጥቄ ቀንሽን ስገድል
"የጊዜን ምንነት ነግሬህ ካልገባህ
ያፈቀረን ሰዓት አይተህ ካልተረዳህ
በጊዜ ልርገምህ ግዜ ይፋረድህ"
ብለሽኝ ስትሄጂ
ያንች ስለት ሰምሮ ግዜ ተፋርዶኛል
የነበረኝ ሁሉ
በደቂቃ ግድፈት ከእጄ ሸሽቶኛል
ዛሬ
በግዜ ስቀጣ ተረዳሁት ጊዜን
ይቅር በይኝና ተቀበይኝ ቃሌን
በደሌን አየሁት
ሁሉን ተቀምቼ ስገረፍ በሲቃ
ማሪያም ጣትሽን ስጭኝ🤙
እንታረቅ በቃ
እንታረቅ🤝
እንታረቅ🤝
🤙🤙🤙🫴🫴🫴🤝🤝🤝
✍ዝምተኛው ፀሀፊ
@belay_HI
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19