የመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች
==============
አውሮፕላኑ ተጠልፎ ሊከሰከስ እንደሆነ ታውቋል። ጥቂት ተሳፋሪዎች ስልክ የመደወል እድል ተሰጣቸው። ወዴት የደወሉ ይመስላችኋል? ንግድ አብረዋቸው ወደሚሰሩት ሰዎች? ወደ መስሪያ ቤት አለቃቸው?
በእነዛ ቅፅበቶች ስለመንግስት ወይም ስለተቃዋሚ ያሰበ መኖሩን እኔ'ንጃ! "ፌስቡክ ላይ ገብቼ የተሳሳቱ ሰዎችን በኮሜንት አስተካክላቸዋለሁ" የሚል ሰው ይኖር ይሆን?🤔 ድሮ የተጣሉት ሰውዬ ትዝ የሚላቸው አይመስለኝም። ከጎረቤታቸው ጋር የነበራቸው ቂም matter አያደርግም!
በዚያ ቅፅበት ስለአለባበሱ የተጨነቀ መኖሩን እጠራጠራለሁ። "ክብደቴ ጨምሯል፣ ስፖርት መስራት አለብኝ ያለ ( 'ለ' ላልቶ ነው የሚነበበው) ሰው ያለ ('ለ' ጠብቆ ነው የሚነበበው) አይመስለኝም።
በህይወት ውስጥ ከባድና ወሳኝ የሆኑ ነገሮች ሲከሰቱ የሚያስፈልገው አንድ ነገር ብቻ ነው። ፍቅር። ሰዎች ከመሞታችን በፊት አምስት ደቂቃ ማስጠንቀቂያ ቢሰጠን ቴሌ "እወድሀለሁ!" ወይም "እወድሻለሁ!" በሚሉ መልእክቶች ይጥለቀለቅ ነበር። ችግሩ ሞት በቀጠሮ አይመጣም።
መጨረሻ ላይ እጅግ ወሳኙ ነገር ፍቅር እና የምንወዳቸው ሰዎች ከሆኑ ሳይረፍድ የህይወታችንን ቅኝቱ ማስተካከል ጥሩ ነው። የታክሲ ላይ ጥቅስ የሚፅፈው Golden Boy Biruk ብዙ አሪፍ ጥቅሶች አሉት። አንደኛው "ጭቅጭቁን ትተን ምነው ብንፋቀር፣
ሁሉም ቅርብ ወራጅ ነው ከፈጣሪ በቀር።" ይላል።
ዶ/ር ዮናስ ላቀው
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19