አጓጉል ባልንጀርነት
ምናይት አመል ነው እናንተዬ!?
የሆነች ጓደኛ ነበረችኝ። ምንም ነገር ብነግራት ከሌላ ወገን ካላረጋገጠች እኔ በነገርኳት ብቻ አታምንም። ቀድሜ ስላነበብኩት ታሪክ ወይም ገጠመኝ ብነግራት ከቻለች ያነበብኩትን አግኝታ አንብባ ታረጋግጣለች ካልሆነ እኔን ባለማመን ውስጥ ትሰነብታለች። ከእከሌ ጋር ሆነን ስለበላነው ምግብ ሳወራት እከሌን በሆነ አጋጣሚ ስታገኘው
“አብራችሁ በላችሁ አይደል? “
ብላ ትጠይቃለች። የሆነ ቦታ ልንሄድ ነው ስላት አብረውኝ የሚሄዱትን
“ልትሄዱ ነው እንዴ?”
የገዛሁት ልብስ አልሆነኝም ስላት ወደ ልጆቼ ዞራ
“አልሆናትም እንዴ? ትላቸዋለች።
አድራሻ ስነግራት ማፕ አውጥታ ታረጋግጣለች። ይሄ ከተማ የሚገኘው ከዚህኛው ከተማ ቀጥሎ ነው ካልኳት ጉግል አድርጋ ታረጋግጣለች።
ቀድሜ በቲቪ አይቼ ነገ ዝናብ አለ ካልኩ “Siri” ብላ አርተፊሻሏን ትጠይቃለች።
በዝናብ ምክኒያት የሰርግ ቦታና ሰዓት የቀይሯል ስላት ሌላ ሰው ጋር ደውላ መቀየሩን ጠይቃ ታረጋግጣለች።
በቃ ምን አለፋችሁ ምንም ምንም ነው የማታምነኝ እና የምሰጣትን መረጃ በቀጥታ የማትጠቀምበት! ለብዙ ግዜ ግራ እየገባኝም ቢሆን ዝም ነበር የምለው። ይሄ አመሏ ግን እኔ ላይ ብቻ ነው ለሁሉም ሰው ይሆን? ብዬ የራሴን ጥናት ማድረግ ጀመርኩ። ለማመን አረፍተ ነገሩን እስኪጨርስ እንኳን እንደማትጠብቅ አስተዋልኩ።
ማታ በስልክ እንዳመመኝ ነግሬአት በነጋታው “ተሻለሽ ወይ?” ብላ በመጠየቅ ፋንታ “ዛሬ ድነሻል!” ብላ ወሬ ትጀምራለች። አሞኛል ያልኳትን አላመነችም ማለት ነው? እላለሁ ለራሴ። እየቆየሁ ግን ያመኝ ጀመር! ምናልባት ብታሻሽል ብዬ የሆነ ነገር እነግራትና Siriን ጠይቂያት፣ ከእከሌ አረጋግጪ ስላት ባልሰማ ታልፋለች እንጂ ለምን አትለኝም። አንዳንዴ የሆነ ነገር በሰው አስነግራትና የሰማችውን ወዲያው አምና እንዲህ ሆኗል ብላ ለኔ ትነግረኛለች። ቀድሜ የነገርኳት እኔ ብሆን ኖሮ ግን ሌላ ማረጋገጫ ትፈልግ ነበር። አንዴ ደግሞ እነሱ ሰፈር ያለ ስቶር እኔ በጣም የምፈልገው ዕቃ ላይ የአጭር ግዜ ሃይለኛ ቅናሽ አድርጎ በፅሁፍ መልዕክት እባክሽን ከስራ ስትመለሺ እግረ መንገድሽን ይህን ዕቃ አንሺልኝ ብሩን Cash up አደርግልሻለሁ አልኳት። ሁለት ቀን ሲያልፍ ደውዬ ገዛሽልኝ? ስላት
“አይ ገና አልሄድኩም”
ለምን? የምትጠይቂው ሰው በቅርብ ካላገኘሽ ጉግል አታደርጊም ነበር? ካልቻልሽ ደግሞ አልችልም አትይኝም ነበር? አልኳት።
“የባሏን ስም ጠቅሳ እሱን ጠይቄው ነበር ስላልመለሰልኝ ነው” አትለኝም?
እውነት ለመናገር ከሆዴ ውስጥ የተቃጠለ ጪስ በጉሮሮዬ በኩል መውጣት ጀምሮ ነበር። እሺ ችግር የለም! ብዬ ስልኩን ዘግቼ የሰላሳ ደቂቃ መንገድ ነድቼ ሄጄ ለመግዛት ብዬ መኪናዬን አስነስቼ ለማንኛውም ብዬ ወደ ዌብሳይቱ ስገባ እቃው sold out ሆኗል።
በፊቱኑም ያን ያህል ሩቅ ሆኖ ሳይሆን ለሷ ስለሚቀርባት እና በደጃፉ ስለምትመላለስ ዕድሉን ለመጠቀም ነበር። ወዳጄ በገንኩ አይገልፀውም!! ዕቃው ስላመለጠኝ እንዳይመስላችሁ የበገንኩት። የእሷ እኔን ያለማመንን ልክ እና ለዚያ ያደረሳት የደበቀችኝ ምክኒያት ምን ይሆን የሚለው ጉዳይ በጨጓራዬ ውስጥ ጉልቻ ደርድሮ፣ ማገዶ ሰትሮ እሳት ማንደድ መጀመሩ ተሰማኝ። እኔን ያለማመንን በአደራ እንደተቀበለችው ዕቃ ነው የምትቆጥረው። አትጥለውም፣ አታዝረከርከውም፣ ለአፍታ እንኳን አትተወውም።
እየደከመኝ ሄደ? ውስጤ ጓደኝነታችንን ጥያቄ ውስጥ ማስገባት ጀመረ። ማለቴ በየወንዙ እየተማማልን እንዴት ነው የልብ ጓደኛ ሆነን የምንቀጥለው? እያልኩ ማብሰልሰል ያዝኩኝ። ሌላ የማስብበትን ግዜ ተሻማብኝ። ደጋግሜ ሌላ ማረጋገጫ የምትፈልግለትን ነገር እንዳትጠይቀኝ ብነግራትም አልሰማ አለች። ልቤ ምክር ሳይጠይቀኝ እየራቃት ሄደ። አንድ ቀን ግን ተስፋ ቆረጥኩ! አብረን ሆነን አመመኝ። ለባሌ ደውላ
“ታማለች እንዴ?” አለችው!!
ይኸው በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ከተለየሁዋት አምስት አመት ሆነኝ። ደሜ በትክከል መዘዋወር ጀምሯል። 😄አንዳንድ ጉድኝቶች ከጥቅማቸው ጉዳታቸው ያመዝናልና ይፈተሹ ለማለት ነው።
ዛሬ ፎቶ አይቼ ትዝ ብላኝ ነው። ምፅ! 😴😴
አይዳ (ቃል እና ቀለም)
ፉት እያልን☕️
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19