ጊዜ ሃያል ነው ። የከበደን ይቀላል ፣ ግራ የገባን መስመር ይይዛል፣ የምንፈራውን ስናየው ሳቅ ይታገለናል።
አሻግረን ብርሃን እናያለን ፤ጠንክረን እንሰራለን ፤ ያሸነፍን ሲመስለን አንታበይም ፤ በወደቀ ላይ አንፈርድም ፤በትንሽ በትልቁ አንማረርም ፤በረባው ባረባው አንቀደድም ፤ላለው አናሽቃብጥም ።
ስንገሰፅ እንሰማለን ፤ ቅር ያለንን እናሳያለን ፤ ስንወድ መውደዳችንን አንደብቅም ፤ ስናደንቅ አድንቆታችን ለሚገባው ሰው እንሰጣለን ።
ድክመት ድክመት ላይ አንመሰጥም ፤ ውድቀታችንን ጠቅልለን አናላክክም ፤ ይሉንታ ቢስ አንሆንም ።
ግፍን እንፈራለን ፤ ያዘነ ላይ አንስቅም፤ የጉብዝና ወራታችን ወቅት አንመፃደቅም ። መስገብገባችንን አደብ አናሲዘዋለን ፤ ውድድራችን ከራሳችን ትላንት ጋ ነው፤ ትግላችን ከህልማችን ጋ ነው።
ከትላንታችን እንማራለን ፤ ታላላቆቻችን እንሰማለን ታላላቆቻችን በምክንያት እንሞግታለን ፤ አድናቆታችን አምልኮት የለበትም ፤ ስኬታችንን በመርሃችን እንለካለን ፤ እራሳችንን እንገዛለን ።
የማይነጋ ጨለማ የለም... ይነጋል ፣ የጠወለገው ይለመልማል ፣ የጎደለው ይሞላል ።
አሜን ❤🙏
Adhanom Mitiku
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19