ምድራችን ባለ ሁለት ጨረቃ ሆነች።
ሳይንስ እንደሚለው ምድራችን ለብዙ ሚሊዮን አመታት አንድ ጨረቃ ብቻ ነበረቻት። ይህችንም ጨረቃ ሁሌ ወደ ሰማይ ስናንጋጥጥ እናያታለን። ነገር ግን ሰሞኑን ምድራችን አንድ ተጨማሪ ጨረቃ እንዳገኘች የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ጣቢያ ናሳ አሳውቋል።
መስከረም 29 በምድራችን አቅራቢያ ስታልፍ የነበረች Asteroid የመሬት የስበት ሃይል እንደያዛትና በ4.5 ሚሊዮን ኪሎሜትር ርቀት በመሬት ዙሪያ እየተሽከረከረች እንዳለች ተገልጿል።
2024 PT5 የተባለችው ይህቺ አስትሮይድ የArjuna Asteroid ስብስብ አባል ስትሆን ይህ የአስትሮይዶች ስብስብ ፀሃይን በ150 ሚሊዮን ኪሎሜትር ርቀት ይሽከረከራል።
ከዚህ ስብስብ ያመለጠችው ይህቺ አስትሮይድም በምድራችን ዙሪያ ለተወሰኑ ሳምንታት የምትሽከረከር ሲሆን ከመስከረም 29 እስከ ህዳር 25, 2024 ድረስ ተሽከርክራ ከመሬት ስበት በማምለጥ ቀጣይ ጉዞዋን ትቀጥላለች።
አስትሮይዷ ከጨረቃን 300ሺ ጊዜ የምታንስ በጣም ትንሽ ስለሆነች በአይን ለማየት አስቸጋሪና በምድራችን ላይም ምንም አይነት ተፅዕኖ እንደማይኖራት ናሳ አሳውቋል።
source: Earth.com, space.com
©️@bighabesha_softwares