ማታ ላይ ከመተኛቷ በፊት ስትኳካል አይተዋት
"ምንድነው በእንቅልፍ ሰዓት እንዲህ የምትቀባቢው?" አሏት።
"አስከሬን እያበጃጀሁ፤ ለገናዦቼ ሥራ እያቃለልኩ ነው " አለች አሉ አንዷ እብድ።
ሰው ማለት ምድር ላይ የሚንቀሳቀስ፣ ቀኑን የሚጠብቅ ሙት ነው። የጊዜ ጉዳይ እንጂ አስከሬን ነው።
የድንገተኛ ሞት መብዛት ነገር ብዙ በእጅጉ ሊያሳስበን የሚገባበት ዘመን ላይ ነን ።
ማታ አልጋ ላይ ተኝተን ጠዋት መቃብር ውስጥ ራሣችንን ልናገኝ እንችላለን።
አስከሬን ነንና ዉዱእ አድርገን፣ በልቦናም ንፁህ ሆነን፣
አዝካሮችን አድርገን፣
የምድር ላይ የመጨረሻ ንግግራችንን አሳምረን እንተኛ።
ቲስበሑ
https://t.me/MuhammedSeidAbx