ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር ያሳለፍኩት ምሽት!
ትላንት ምሽት በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ computing and informatics students association ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ልምደን ለማካፈል እድል አግኝቼ ነበር። ወደ ሁለት ሰዓት በፈጀው በዚህ ዝግጅት ላይ ወደ 200 የሚጠጉ ተማሪዎች ተገኝተው ተከታትለዋል።
በቆይታችንም ዘርፉ ስለሚፈልገው ቁርጠኝነት፣ ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ እንዲሁም ስኬታማ የሶፍትዌር ደቨሎፐሮች ለመሆን ምን ማድረግ እንዳለባቸውና ከተማሪነት እስለ ባለሙያነት ሂደት ላይ ያተኮሩ ጠቃሚ ሃሳቦችን ለማካፈል ሞክሬያለሁ። በተለይም የሚከተሉት ነጥቦች ላይ ትኩረት ሰጥተን ተወያይተናል፡
* በሙያቸው ያላቸውን ፍቅርና ቁርጠኝነት ማዳበር፡ ተማሪዎቹ በኮምፒውተር ሳይንስ ዘርፍ ለምን እንደተሰማሩ እና እንዴት ለሙያቸው ጠንካራ ስሜት ማዳበር እንደሚችሉ ተወያይተናል።
* ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም፡ በተለይም በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ጊዜያቸውን በአግባቡ ተጠቅመው ለስኬታማነታቸው እንዴት መሠረት መጣል እንደሚችሉ ጠቃሚ ምክሮችን ሰጥቻቸዋለሁ።
* የሶፍትዌር ደቨሎፐር ለመሆን የሚያስፈልጉ ክህሎቶችና ልምዶች፡ አንድ ስኬታማ የሶፍትዌር ገንቢ ምን ዓይነት ችሎታዎች ሊኖሩት እንደሚገባ እንዲሁም በተግባር ልምድ ለማዳበር ምን መንገዶችን መከተል እንዳለባቸው በስፋት ተወያይተናል።
በጣም በሚገርም ሁኔታ ተማሪዎቹ ለውይይቱ ያላቸው ተሳትፎ ከፍተኛ ነበር። ጥያቄዎቻቸውና አስተያየቶቻቸውም የነበራቸውን የትምህርት ፍላጎትና ባለሙያ ለመሆን ያላቸውን ቁርጠኝነት በግልጽ ያሳዩ ነበር። ይህን የመሰለ ድንቅ ጊዜ ካሳለፍኩባቸው ተማሪዎች ጋር በመገናኘቴ በጣም ደስ ብሎኛል። ለወደፊቱም እንደዚህ አይነት እድሎች እንደሚኖሩኝ ተስፋ አደርጋለሁ።
ይህንን ፕሮግራም ስላዘጋጁልኝ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የኮምፒውተር ሳይንስ፣ የሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ እና የኢንፎርሜሽን ሲስተም ተማሪዎች ማህበር ላመሰግናቸው እወዳለሁ። ለተማሪዎቹም ለወደፊት የትምህርት እና የሥራ ሕይወታቸው መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ።
#ሐረማያዩኒቨርሲቲ
#የኮምፒውተርሳይንስ #የሶፍትዌርኢንጂነሪንግ #የኢንፎርሜሽንሲስተም #ተማሪዎች #ልምድማካፈል@birhan_nega