ንቅሳት የካንሰር ተጋላጭነትን እንደሚጨምር አዲስ ጥናት አመላከተ።
በደቡብ ዴንማርክ እና በሄልሲንኪ ዩኒቨርሲቲዎች የተደረገው ጥናት የንቅሳት ቀለም ለቆዳ ካንሰር እና ሊምፎማ ካንሰር ያለን ተጋላጭነት እንደሚጨምር አረጋግጠዋል።
የምርምር ቡድኑ የንቅሳት ቀለሞች ከተወጉበት አካባቢ በተጨማሪ ወደ ሌሎች የሰውነት አካባቢዎች እንደሚሰራጩም የተመለከተ ሲሆን ቀለሞቹ ሰውነትን ሊጎዱ ከሚችሉ ንጥረ ነገሮች ለመጠበቅ ወደ ሚረዱት እና ሊምፍ ኖድ ወደሚባሉ የሰውነት ክፍል ማለትም በአንገት፣ ብሺሺት፣ ብብት፣ ደረትና ሆድ አካባቢ በዕብጠት መልክ እንደሚቀመጡ ተመራማሪዎቹ ጠቁመዋል።
በዚህም ምክንያት የተከማቸው ዕብጠት ያልተለመደ የሕዋስ እድገትን ሊያስከትል እንደሚችል የተገለፀ ሲሆን በጊዜ ሂደት ወደ ካንሰር ሊያመራ እንደሚችል እና ንቅሳቶች መጠናቸው በተለቀ እና ቆታቸው በጨመረ ቁጥር በሰውነት ውስጥ ብዙ ቀለም እንዲከማች ያደርጋሉ ሲሉ አብራርተዋል።
መጠኑ ትልቅ የሆነ ንቅሳት ያላቸው ግለሰቦች ምንም ንቅሳት ከሌለባቸው ሰዎች ጋር ሲነጻጸሩ የካንሰር ተጋላጭነቱ በሦስት እጥፍ ከፍ ያለ እንደሆነም በጥናቱ ተመላክቷል።
via @breakthecurse