"የኢትዮ ቴሌኮም ሠራተኞች፣ በኩባንያው ውስጥ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ የሠራተኛ የደረጃ ዕድገትና ዝውውር የሚፈጸመው ሕግን ባልተከተለ መንገድ ነው"ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
"የሠራተኛ ዕድገትና ዝውውር ይፋዊ ማስታወቂያ ወጥቶ በውድድር መሆኑ ቀርቶ፣ በሃላፊዎች ውሳኔ ብቻ እየተፈጸመ እንደሆነ ሠራተኞቹ ነግረውኛል" ብሏል ራዲዮው። "በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኝ አንድ የተቋሙ ቅርንጫፍ የሚሠራ ሠራተኛ ለደረጃ ዕድገት ከተማዋ ውስጥ ባለ ሌላ ቅርንጫፍ መወዳደር የማይችልበት ሁኔታ እንደተፈጠረም" ሠራተኞች ለራዲዮው ገልጸዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የኩባንያው የሠራተኛ ማኅበር ፕሬዝዳንት ካሳሁን ሰቦቃ ማብራሪያ እንዲሰጡ በራዲዮው ተጠይቀው "ማብራሪያ ለመስጠት በቅድሚያ የሥራ አስፈጻሚው ውሳኔ ያስፈልጋል" ሲሉ መልሰዋል።
ዋዜማ ራዲዮ እንደዘገበው